ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Sunday, December 11, 2011

‹‹ ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞና የእርዳታ ጥሪ ››

      
    ይህ የምትመለከቱት ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ክልል በከምባታና ሀዲያ ጉራጌ በምሻ ወረዳ የሚገኝ የጢኒቃ እየሡስ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን ከተመሰረተ ከአስር (10) ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡ በአካባቢው ካለው ህዝብ የሚበዛው ነዋሪ የሌላ እምነት ተከታዮች ስለሆኑ ያለው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ጥቂት ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ የመናፍቁ ኃይል ስለሚበዛ ቤተክርስቲያኑ በምንም መንገድ ገቢ የማያገኝ  ከመሆኑም ባሻገር  ቤተክርስቲያኑ እስከ አሁን ድረስ በመቃኞ ይገኛል፡፡ ይህንንም በማየት ጥቂት በጎ ፈቃደኞች አዲስ ህንፃ ቤተክርስቲን እያስገነቡ ይገኛል፡፡
እግዚአብሔር ከፈቀደ ፅላቱን ጥር 6 ቀን 2004 ዓ.ም አዲስ ወደተሠራው ቤተ ክርስቲያን ለማስገባት ስለታሰበ ለዚሁ ማስፈፀሚያ የሚሆን የአቅማችሁን ብትለግሱን እያልን በእግዚአብሔር ስም እንለምናለን፡፡
ጥር 6,2004 ለሚካሄው ታላቅ በዓል ሚደረገው መንፈሳዊ ጉዞ ለመሳተፍ ለምትፈልጉ ምዝገባውን ጀምረናል፡፡               የታሰበውን ህንፃ ቤተክርስቲያን ሙሉ ለሙሉ ፈፅመን  ለአገልግሎት ይበቃ ዘንድ አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ አሜን፡፡
                ‹‹ መልካም ሥራን ለመስራት አንታክት ›› ገላ.6፤4
ለተጨማሪ መረጃ በሞባይል 0911-116552 እንዲሁም 0913704501 ይደውሉ፡፡
   
 እግዚአብሔር ያክብርልን፡፡

5 comments:

  1. Yekidusan Amlak ke'enante gar yihun

    ReplyDelete
  2. Egziabeher Yerdachehu Feqadu khone kberektu lmesatef Asebalhunge.

    ReplyDelete
  3. GOD Bless you and your Family

    ReplyDelete
  4. GOD Bless you and Your Family
    Bible says Menfes one new Ye Tsega Gift Gin Liyu Liyu new Yelal ena Be Tsegah Eskemechereshaw Tsenteh Yemitagelegil hun

    ReplyDelete