ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Sunday, January 22, 2012

በረከቴን የትም አልጥልም

Read in PDF     
ከአንድ የሠፈሬ ልጅ ጋር
  የቅዱስ ሚካኤል ታቦት ልናስገባ በአካባቢያችን ወዳለው ጎላ ሚካኤል ሄድን ፡፡ ‹‹ እኔ የምልህ እገሌ ለምን ከእኛ ጋር አይመጣም? ›› ብዬ ጠየኩት፡፡በእርግጥ ልጁ ፕሮቴስታንት ነው፡፡ ነገር ግን ብዙ ግዜ ሲጨንው. . . ሲከፋው. . .. መገኛው ልደታ ወይ ጊቢ ገብርኤል አንዳንዴም ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ይህን የምናውቅ ልጆች አንድም ቀን ለምን እንዲ ታደርጋለህ ብለነው አናውቅም፡፡ ምክንያቱም ሠላም የት እንደሚገኝ እራሱ ስለሚያውቅ፡፡
‹‹ ባክህ እሱ  ግራ የገባው ነው፡፡›› አለኝ ‹‹ እንዴት ?›› ጠየኩ፡፡
‹‹ አይደለም እሱ ሁሉም በዚህ ሠዓት ግራ ገብቷቸዋል››  አሁንም ግራ  ገባኝ አገላለፁ፡፡ አልመለሰልኝም ፡፡ ስለጥምቀት በዓሉ ማውራት ጀመረ፡፡ እኔም ብዙ አላሳሰበኝም ነበርና አጥብቄ አልጠየኩትም፡፡

ታቦተ ህጉ በተለምዶ ‹‹መንዲዳ›› ከሚባለው ማደሪያው  ተነስቶ ጉዞ ጀምሯል፡፡ የአካባቢው ወጣቶች አካባቢውን ድምቀት ሰጥተውታል፡፡ ሁሉም ይዘምራል፣ይጨፍራል. . . ደስታና እልልታ በአካባቢው ነግሷል፡፡ ሁሉም ታቦተ ህጉን ያስባል፡፡ ይጨነቃል፣ይፈራል፣ክብር ይሰጣል፡፡ ክብር ለእግዚአብሔር ይላል፡፡ ለኔ ወጣቱ ምንም ያድርግ ለእግዚአብሔር ማደሪያ ለሆነው ታቦት ክብር ይስጥ እንጂ፡፡ ሌላው ይደርሳል፡፡ ታቦት ግን መፈራት መከብር አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡ የአካባቢ ልጆችም ይህን ነበር ሲያሳዩን የነበሩት፡፡ የተባረኩ ልጆች፡፡ የአዲስ አበባ ነዋሪ ቤቱን ጥሎ የወጣ እስኪመስል
የከተማው  ጎዳናዎች በምዕመን ደምቋል፡፡ እንኳን አደረስከኝ ብዬ ታቦተ ህጉ ስር ሰግጄ ተሳልሜ ከበረከቱ ተቋደስኩ፡፡ እንዴት ደስ ይላል፡፡ አዲስ አበባም ተባረከች የፀናች ተዋህዶም ከበረች፡፡
ሰዓቴን ሳየው 8፡00 ሠዓት ይላል፡፡ 9፡00 ሠዓት ላይ አንድ ሠርግ ላይ ተጠርቼ መሄድ ስለነበረብኝ እየቀፈፈኝ ፕሮግራሙን  አቋርጬ የአመት ሠው እንዲለኝ ተማፅኜ  ወደ ሠርግ ቦታው ሄድኩ፡፡ ጥሪው (ግብዣው) የኔ ከምለው ሰው ስለመጣ መቃወም አልቻልኩም፡፡ እየደበረኝ ሄድኩኝ፡፡
እነሱ ቤተ ክርስቲያን ነው አሉኝ ለኔ ግን ከአዳራሽነት የዘለለ ምንም አላየሁበትም ፡፡ እንበል ከተባለ የእኛ ቤት ቤተ-ክርስቲያን ይመስላል፡፡ ‹‹YOU GO CITY CHURCH›› ብለውታል እነሱ፡፡  እውነትም
‹‹YOU GO CITY CHURCH›› ፡፡ ለኔ YOU ‹‹GO CITY CHURCH›› ከሚሉት ‹‹YOU GO CITY MALL››  ቢሉት እመርጣለሁ፡፡  መግቢያው ላይ በግራ በኩል በትልቁ ‹‹I BELONG TO JESUS›› ይላል፡፡ በቀኝ በኩል ደግሞ ‹‹ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ››  ይላል፡፡ አሜን አልኩ በውስጤ ፡፡  በዛሬው የጥምቀት ዕለት ብቻ ጎዳናዎች፣ መንደሮች፣ እግዚአብሔርን ሲያስቡ ታቦታት ነግሰው ከብረው ነው የዋሉት፡፡ እግዚአብሔርም  ኢትዮጵያን ይባርካታል፤ባ
ርኳታልም፡፡መመኘት መልካም ቢሆንም በየጥሻው በየዋሻው ለሁሉም ቀንና ለሊት የሚፀልዩ አባቶችና እናቶች የሞሏት የቅዱሳን ደሴት ናት፡፡በተጨማሪም የኢትዮጵያ ህዝብ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረበትና ልበ ቀናሂ ነው፡፡
ወደ ውስጥ ስገባ ሁሉም ይዘላል፡፡ ከመድረኩ ላይ በዛ ያሉ የኢትዮጵያ ን ሀገር ልብስ የለበሡ ዘማርያን(በነሱ) በጣም እየጮሁ ሁለት እጃቸውን ወደ ላይ አድርገው ይዘላሉ፡፡ ከአንዳንድ ቦታም. . .  የሆነ ያላጣራሁት ጩኸት ይሰማል፡፡  ‹‹ቡና›› እና ‹‹ ጊዮርጊስ›› እግር ኳስ የሚጫወቱ ነው የመሰለኝ፡፡ ውስጤ  ሰላም አጣ፡፡ ልዑል እግዚአብሔር በእንዲህ አይነት መልክ ሲከበር ይጨንቃል፡፡ እንኳን እሱ ታላቁ ንጉስ ቀርቶ እኔ ተራ የሆንኩትም አልተመቸኝም፡፡ መንፈሳዊነት ሳይሆን የግል ስሜት ይንጸባረቅበታል፡፡ ምናልባትም በገንዘብ ቢሆን ኖሮ የገባሁት አብሬያቸው እደንስ ነበር፡፡  ልክ ዝላዩ ሲያልቅ በጣም ያስደነገጠኝን ነገር መፈፀም ጀመሩ፡፡ እኛ መለያችን አርማችን የምንለው ምስጢረ  ተዋህዶ የሚንፀባረቅበትን ፣በታቦታት ፊት አባቶች የሚይዙትን ትልቂን ባለግርሚ ሞገሱን መስቀላችንን ከነ ሶብሉ አንዱ ተሸክሞ አመጣና መድረኩ መሐል ቆመ፡፡  መስቀሉስ እሺ ብል ሰበኑን ግን ለምን እንዳደረጉበት ግራ ገባኝ ፡፡ መቼም የኢ.ኦ.ተ.ቤ. ከመስቀል ላይ የምታስረው ጨርቅ ወይም መገንዟ(በቤተ-ክርስቲያን አጠራር ሰበን ይባላል) ከብዙ ትርጉም ሰጥታው ነው፡፡ በዋናነት መስቀልና እመቤታችን  ቅድስት ድንግል ማርያም ያላቸውን ተያያዥነት ለማሳየት ሲሆን፤ የጨርቁ (የሰበኑ) ትርጉም ደግሞ እናታችን እመቤታችን  ቅድስት ድንግል ማርያም በምታርግ ጊዜ ይህን የተመለከተው ብቸኛው ሐዋርያ ቶማስ ለተቀሩት ሐዋርያት የተመለተውን ተአምር ለመመስከርና እንዲያምኑት የተገነዘችበት መገንዘ ጨርቅ ይዞላቸው መሄዱንና እነሱም ይህን መገንዘ ጨርቅ ሲያዩ የድንግልን ማረግ ተረድተዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም የድንግልን ማረግ ለማስታወስ ለማክበር፣ በምሳሌነትም ለማስተማር፣ በሚያምሩና ቆንጆ መዓዛ በተቀቡ ውብ ጨርቆች (ሰበን) እያደረገች መስቀሎቿን ታስራለች፡፡ ያለ ድንግል መስቀልን ማሰብ ስለሚከብድ ማለት ነው፡፡
እውነት ይህ መስቀል የማን ነው?


ልጁም የማይሳለመውን ፣ የማይስመውን መስቀል ከነሰበኑ (መግነዟ) ይዞ እንደቆመ ነው፡፡ ምን ሊያደርገው ነው ብዬ ግራ ገባኝ፡፡  እርግጠኛ ነኝ የያዘው ሚስቱን ወይም ፍቅረኛውን ቢሆን ደጋግሞ በሳመ ነበር፡፡ ጌታው የተሠቀለበትን  ለሱ ሲል የሞተበትን መስቀል ታቅፎ ከመቆም የዘለለ ግን ሊስመውና ሊሳለመው  ፍቃደኛ አይደለም፡፡ አህምሮ ሲታወር እንዲህ ነው እንዲሉ፡፡ ይዞት የያዘው የማይገባው ፡፡

ብቻ ምን እየተደረገ እንዳለ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ውስጤ መረበሹ ቀጥሏል፡፡ ሠርገኞቹም ይኸው 9፡00 ደረሱ ብለውን እነሱ ሳይመጡ የውሃ ሽታ ሆነዋል፡፡ 10፡30 እንደቀልድ ሆነ፡፡ ይሄ እንኳን  ጠቅላላ የአበሻ ሰርገኛ ችግር በመሆኑና ጥዬ እንዳሌድም የጓደኛዬም ግብዣ በመሆኑ የማደርገው ጠፋኝ፡፡ መስቀሉና እያየሁ ወይ እግዚአብሑር ምንድነው የምታሳየኝ አልኩ በውስጤ፡፡ ለራሴ ሳኩኝ  ነገ ምን ሊሆን እንደሚችል ሳስብ ፡፡ ቋሚ መገለጫና የራሳቸው ነገር ባለመኖሩ በየጊዜውና በየወቅቱ ስርዓታቸውን ስለሚቀያረሩ ዛሬ መስቀል ከያዙ ነገ ደግሞ ይሳለሙታል፤ይስሙታል፡፡ በዚህ ደግሞ እርግጠኛ ነኝ፡፡ምክንያቱም  ዘመናዊነት የሚለው ያን ስለሆነ (adjust your self based on the time that u have on your hand) ፡፡እነሱ ደግሞ የዘመናዊነት አቀንቃኞች ናቸው፡፡

እርግጥ ነው የኔ የሚለው የሌለው የጎረቤቱን ጓዳ ይመለከታል ፡፡ እነሱም እያደረኩ ያሉት ያንን ነው፡፡ በሁሉ የተሟላችውን ተዋህዶን  ባይመለከቱ ነበር የሚገርመው፡፡ አንዳንዴ ሙስሊሞች በዚህ ሳያሻሉ አይቀሩም፡፡ የበዛ የማንነት ቀውስ የለባቸውም ፡፡የተሳሳተ ቢሆንም የራሳችን የሚሉትና የሚራመዱበት መንገድ አላቸው፡፡ እነዚህ ግን አሁን አሁን ዘመናዊነትን ከኢትዮጵያነት ጋር ለማያያዝ በመጣር ላይ ናቸው፡፡ እየተሳሳቱት ያለው ግን ምንም ለውጥ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ በተለይ በዚህ ሠዓት ከኢ.ኦ.ተ.ቤ. ስርዓትና አስተሳሰብ ውጪ አይሆኑም፡፡ አሁን አሁን የታዘብኩት የያዙት ያስኬደናል ያሉት ስንቅ እያለቀባቸው እንደሆነ ነው፡፡
‹‹ ሁሉም በዚህ ሠዓት ግራ ገብቷቸዋል›› አሁን ነው የጓደኛዬ ንግግሩ ግልፅ የሆነልኝ(ከላይ የጠቀስኩት)፡፡ ሙሉ ለሙሉ እንዳይወረሱ መሳቂያ ይሆናሉ በራሳቸውም እንዳይሄዱ በአንዳንዶች መሰላቸት እየታየ ነው፡፡ እንደገባኝም ግራ ሳይገባቸው አልቀረም፡፡ ነገረ ስራቸው በሙሉ የእኛን የኦርቶዶክሶችን እየመሰለ መቷል፡፡ የኛን መምሰል፡፡ ቀባ ቀባ ማድረግ፡፡ ምናልባትም ሌላኛው ዘዴ ሳይሆነ አይቀርም እራሳቸውን ትንሽ ቆየት(survive) ለማድረግ፡፡ እስቲ በርቱ ከማለት ሌላ ምን ማለት ይቻላል፡፡ ሠው እንዴት ያለምንም አተካሮና ጭቅጭቅ ጦርነትና ግብግብ ይሸነፋል? የሚገባኝ  ክርስትና ያለ ድንግል ማርያም እንደማያታሰብ ሁሉ መሰረት የሌለው ነገር በሙሉ ፣ በሠዎች ፍላጎትና(interest) አስተሳሰብ የሚቀያየር ፣የሚታደስ( modify) የሚደረግ ነገር በሙሉ ቀን ከቆጠረ እንጂ መፍረሱ አይቀርም ፡፡ ይብላኝ እንጂ አውቀውም ይሁን ሳይውቁ እግዚአብሔርን ያገኙ መስሏቸው በውስጡ ለተጠለሉ፡፡ አንድም ቀን እረፍት ለሌላቸውና ለሚባዝኑ፡፡
ወደጉዳዬ  ስመለስ መስቀሉን እንደነገሩ የያዘውን ልጅ ዘማርያኑ (በነሱ) ግራና ቀኝ  ከበቡት፡፡ በሁለት በሁለት እረድፍ ተሰለፉ፡፡ ከመድረኩ ጀርባ አንድ ልጅ ብዙ መቋሚያና ፅናፅል ተሸክሞ  ወጣና ለሁሉም አደላቸው፡፡ በድንጋጤ አይኔ ፈጦ ጣቴን በጥርሴ ነከስኩት፡፡  ‹‹ ወረብ ሊያቀርቡ ነው እንዴ? ›› ብዬ አጠገቤ ያለቸውን ጠየኳት፡፡ ‹‹ አዎ ›› ነበር መልሷ ፡፡ መቋሚያ አያያዛቸው  ፅናፅል አያያዛቸው የኛን ነው የሚመስለው፡፡ ‹‹ እውነትም የሚያደርጉት ጠፍቷቸዋለው››ማንን እንደሚሸውዱ አላወቁም፡፡  ምንም ላምን አልቻልኩም፡፡ አይቀርምና መወረቡን ተያያዙት፡፡ ታዳሚው ካሜራውን ደቀነ፡፡ ምን ያድርጉ ጊታርና ኪቦርድ ሲሰለች ከጎረቤት መስረቅ ትንሽ ቀየር ተደርጎና አዲስ ለዛ ተፈጠሮ ካዩ ስለሌላው ምን ያስጨንቃቸዋል፡፡ ዘና ፈታ ማለት ከተቻለ-አንድ ዘፈን ትዝ አለኝ ‹‹ ብንጨፍር ብንዘል ምን ይለናል እኛ! ምንም!! ›› በግ እንደመሩት እንዲሉ ልክ እንደራሳቸው በደስታ ባህር ሰመጡ፡፡ ምናልባትን የእናት አባታቸው ኦርቶዶክሳዊነት ትዝ ብሏቸው በተዘዋዋሪ ያገኙት መስሏቸው ይሆናል፡፡የራሳቸውን ነገር ለማየት ናፈኩኝ፡፡ የራስ የሆነ ( originality) አጣሁባቸው፡፡
ፅናፅሉን መፀነፅ ጀመሩ. . . . ከበሮውን መደለቅ ቀጠለ፡፡ ሲቀጥል ቅዝቅዝ ያደርጉታል፤ከዛ ጩኸት፣ዝላይ ፡፡ እኔ ትዕግስቴ ተሟጠጠ፡፡
የራሳችን የሚያኮራ ቤት አለን፡፡በማዕሌት እና 
ቅዳሴ የደመቀች፣ጥልቀትና ሚስጢራት የሞ፣ የወረቡ መንፈስ አዳሽነት ፣ የዝማሬው መንፈሳዊነት. . . ብዙ ሊባል ይችላል፡፡ በበረከት የተሞላች በሁለት እግሮቿ የቆመች ሙሉ ጊዜዋን እግዚአብሔር ች እና እግዚአብሔር የምትሠብክ ፍፁም ሠማያዊት ቤት አለን፡፡ ክብር ይግባው ግራ የሚያጋባ እምነት የለኝም፡፡

የቅዱስ ሚካኤልን ታቦት ተሳልሜ ፣ ተከትዬ ፣ሸኝቼ  የዓመት ሠው በለኝ ብዬ  ተማፅኜ ያገኘሁትን በረከት የማይገባኝ ቦታ ተገኝቼ ማጣትና አባቴን ማሳዘን አልፈለኩም፡፡ ከድንግል እናቴ መጣላት ፈፅሞ አልሻም፡፡ ምንም ሀጥያተኛ ብሆንም በዚህ ግን. . . . ‹‹በፍፁም›› አልኩ በውስጤ፡፡ ከዚህ በላይ መታገስ አልቻልኩም፡፡ መንፈሳዊነት የማይነበብበት አዳራሽ ውስጥ ሲጨፈርብኝ አላይም፡፡እግዚአብሔር  ትህግስተኛ አባት ነው፡፡ እኔ ግን ትዕግስት የለኝም ፡፡ ማን እንደሚመለክ ግራ ተጋባሁ፡፡ መልስ አጣሁ፡፡ ጥዬ  ብወጣስ? ሠላሜን ከማጣ . . . . . .ሠርጉን ትቼ ልውጣ፡፡ ብዬ ተነሳሁና አዳራሹን ለቅቄ ወጣሁ፡፡ በመውጣቴም  የሚከፋው ካለ ይቅርታ አልጠየቅም፡ የመልአኩ ሚካኤልን በረከት የትም ጥዬ አልመጣም ፡፡ታጥቦ ጭቃ መሆን አልፈልገም ፡፡ ሠርገኞቹ ሳይመጡ ገባሁ መምጣቴን ሳያውቁ አዳራሹን ለቅቄ ወጣሁ፡፡እፎይይይ. . . .  . .እንዴት እንደቀለለኝ፡፡ ዳግመኛ እንዲህ አይነት ቦታ ለመሄድ እግሬን የማነሳ አይመስለኝም ፡፡ ምናልባትም  በአንድ ቀን ብዙ ነገር ያስተማረኝ ለበጎ ነው ፡፡ ለተጋቢዎቹ  መልካም ጋብቻ እንዲሆንላቸሁ እመኛለሁ፡፡ 
ፈሪሃ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን የድንግል ማርያም ጥበቃ አይለየን፡፡ አሜን፡፡

20 comments:

  1. ደግ የሆነ አተያይ ንው።
    ዘርዓያቆብ

    ReplyDelete
  2. keep it up!! berta...Egziabher kante gar yehune!!

    ReplyDelete
  3. www.betepawlos.comላይ ያገኘሁት ነው ብሥራት ደስ ስላለኝ ነው!

    ጥምቀት

    ዘመነ አስተርእዮ
    ጥር 11 2004 ዓ/ም
    ኤጲፋንያ በማለት በግሪክ ቋንቋ የሚጠራው በግዕዝ ቋንቋችን አስተርእዮ ተብሎ ተተርጉሟል። ትርጓሜውም መገለጥ ማለት ነው። ይህ የያዝነው ወር ዘመነ አስተርእዮ ወይም የመገለጥ ዘመን በመባል ይጠራል። ዘመነ አስተርእዮ የተባለውም፡-

    1. አምላክ ሰው ሆኖ ከድንግል በመወለዱ
    2. በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጠመቁ
    3. የመጀመሪያውን ተአምር በቃና ዘገሊላ ፈጽሞ ሥራውን በመጀመሩ ነው።

    እግዚአብሔር አምላክ ከጥንት ጀምሮ ራሱን በብዙ ዓይነትና መንገድ ሲገልጥ ነበረ። በአረጋዊ አምሳል ለአብርሃም፣ በንጉሥ አምሳል ለኢሳይያስ ተገልጧል(ዘፍ. 18፡1፤ ኢሳ. 6፡1)። እነዚህ ሁሉ መገለጦች እግዚአብሔር ወዳጆቹን ያበረታበትና ያስተማረበት ነበሩ። በጌታችን ሰው መሆን የተገለጠበት መገለጥ ግን አቻ የሌለው ነው። (ዕብ. 1፡1-3) ይኸውም የእኛን ሥጋ ለብሶ ከእኛ ጋር የተዛመደበት፣ የመለኮትና የሥጋ ተዋሕዶ ዘላለማዊ በሆነ መጠን የእኛና የእግዚአብሔርም ኅብረት ዘላለማዊ የሆነበት ትልቅ መገለጥ ነው። ስለዚህ ጌታችን የተወለደበት ዘመን የመገለጥ ዘመን ተብሎ መጠራቱ ተገቢ ነው። አማኑኤል እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ተብሎ የተጠራው በመወለዱ ነው (ማቴ. 1፡23)። በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር እንደነበረ ራሱ ብዙ ጊዜ ተናግሯል። በልደቱ አማኑኤል መባሉ ግን የተለየ ነው። ይኸውም እርሱ በብሉይ ኪዳን ከሕዝቡ ጋር የነበረው በረድኤት፣ በተአምራት ነበረ። አሁን ግን ከሥጋችን ሥጋ፣ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ በማይፈታ ዝምድና እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ። ለዚህ ነው የአገራችን ባለ ቅኔ በመጓደድ ስሜት እንዲህ ያለው፡-

    አብ ካልሰጠኝ ብዬ ምነው መናደዴ
    ለወልድ አልነግርም ወይ ለሥጋ ዘመዴ

    ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ሠላሳ ዘመኑ ተሰውሮ እንደ ኖረ እናነባለን። በሠላሳ ዓመቱ ግን በጥምቀት አማካይነት ተገለጠ። እስከ ሠላሳ ዓመቱ የት ነበረ? ስንል በሥጋ የወለደችውን እናቱን ድንግል ማርያምን ሲያገለግል ነበረ። ከሠላሳ ዓመቱ በኋላ ደግሞ ሰማያዊ አባቱን ሊያገለግል ተገለጠ። ምድራውያን ወላጆቻችንን እንዲሁም በመንፈሱ የወለደንን ሰማያዊ አምላክን እንዴት ማገልገል እንደሚገባን ጌታችን በሕይወቱ አስተምሮናል። ጌታችን ራሱን የገለጠበት ጥምቀቱ አስተርእዮ ወይም መገለጥ መባሉ እውነት ነው።

    ጌታችን ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊት ጾሞ ከተመለሰ በኋላ በቃና ዘገሊላ የመጀመሪያውን ተአምር በማድረግ ራሱን ገልጧል። ይህ ቀን የታላቅ አገልግሎት መክፈቻ ብቻ ሳይሆን የታላቅ መከራም መክፈቻ ቀን ነው። ስለዚህ ይህ ተአምርም አስተርእዮ ወይም መገለጥ ተብሎ ይጠራል። ቃና ዘገሊላም ጥር 12 ቀን ይታሰባል፡፡

    ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በሠላሳ ዓመቱ ሲሆን የተጠመቀውም በባሪያው በዮሐንስ እጅ ነው። ሠላሳ ዓመት የታላላቅ ውሳኔዎች ዘመን ነው። የልጅነት ዘመን አልፎ፣ የወጣትነት ጭፍንነትም በርቶ ሰከን የሚባልበት ሠላሳ ዓመት የፍሬ ዘመን ብለን የምንጠራው ነው። እስከዚህ ዓመት ድረስ የነበሩት ሩጫዎች ሁሉ ዘር ናቸው። አሁን ግን የመኸር ወይም የፍሬ ዘመን ነው። ዕውቀትን፣ ወዳጆችን፣ ልምዶችን ሁሉ እስከ አሁን እንሰበስባለን። ከሠላሳ ዓመት በኋላ ግን ዕውቀታችንን በጥበብ፣ ወዳጆቻችንን በቃል ኪዳን፣ ልምዳችንን በማስተዋል የምንተገብርበት ነው። ዕውቀቴ ለአገር ጥቅም፣ ለእግዚአብሔር ክብር ሊሆን ይገባዋል፣ ለትዳር ከመረጥኳት ወይም ከመረጥኩት ጋር አብሬአቸው እኖራለሁ፣ እስከ ዛሬ ካልተለዩኝ ወዳጆቼ ጋር እስከ ሞት እቀጥላለሁ፣ ልምዴን እያካፈልኩ የሌሎችን ልምድ እቀስማለሁ የምንልበት ዕድሜ ነው። አገር ለመምራት፣ ለጋብቻ፣ ለምንኩስና ከሠላሳ ዓመት በላይ መሆን ይገባል። ጌታችን በሠላሳ ዓመቱ ተጠመቀ።

    ጌታችን በሠላሳ ዓመቱ ብቻ ሳይሆን በባሪያው እጅ ተጠመቀ። እኛ የምንጠመቀው በጸጋና በመንፈሳዊ መዐርግ በሚበልጡን አገልጋዮች እጅ ነው። ጌታችን ግን በባሪያ እጅ ተጠመቀ። ምሁራን፣ ነገሥታት፣ ባለጠጎች ብንሆን የእግዚአብሔርን አገልጋዮች እንዳንንቅ ሊያስጠነቅቀን ጌታችን በባሪያው እጅ ተጠመቀ። ከምድራዊ ሥልጣንና ኃይል የአገልጋዮች ጸጋ ይበልጣልና!

    «ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ዮሐንስ ግን፡- እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር። ኢየሱስም መልሶ፡-አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት። ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤ እነሆም፡- ድምጽ ከሰማያት መጥቶ፡- በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ» (ማቴ 3፡13-17)፡፡
    ይቀጥላል

    በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ጥምቀት በየዓመቱ ጥር 11 ቀን ይከበራል። ዋዜማው ወደ ወንዝ የሚወረድበት የሚፈሱ ወንዞች ለጥምቀቱ የሚከተሩበት ስለሆነ «ከተራ» ይባላል። ከተራ ማለት ውኃን መገደብ ወይም በቁሙ መከተር ማለት ነው። የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት የሚከበር ትልቅ በዓል ነው። ጌታችን ወደ ባሕረ ጥምቀት ወርዶ የእኛን ጥምቀት የቀደሰበትን የሮም ካቶሊክ ታከብራለች። የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም ወደ ወንዝ በመውረድ ውኃውን ባርከው መስቀሉን በባሕሩ ላይ በመጣል ወጣቶች መስቀሉን ዋኝተው ለጳጳሱ በመስጠት ያከብሩታል። እኛም ጥምቀትን ከባሕል ይልቅ በሃይማኖታዊ ምሥጢሩ ልናስበው ይገባናል፡ ደስታችንንም በመንፈሳዊ ዝማሬና አምልኮ ልንገልጥ ይገባናል። የበረከት በዓል ያድርግልን!

    ReplyDelete
  4. gobeze beserat.kiduse mikail tadegohal.

    ReplyDelete
  5. berate berta .yemetetefachewen eyayehu new.musica eyeseman yemenanebewen gen musicawen wed mezemure lewetelen. tg from canada

    ReplyDelete
  6. ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!! ብስራት በርታ!! በስው ስራሹ ገንዘብ ጥቅም ህይማኖት የሚካድበት ዘመን ስለሆነ በህይማኖትህ ጽና፣፣ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

    ReplyDelete
  7. Ijig girum tsihuf, zemenun yemiwaj. Kale hiwot yasemalin

    ReplyDelete
  8. Replies
    1. You said so. They lost their true Identity. That is why the difference is always visible. However, don't underestimate them, they are very strategical even more than the EOTC. They have strong capacity to take additional innocent people from EOTC. EOTC should care for her believer. Our Religious father have take this responsibility. But the fact is not. Pray for our fathers..... My brother please pray for them..... We lost our brothers....... we lost our sister..... We lost. You know why half of my family is protestant, I know their strategy... They are very cynical... We lost them due to greedy religious leaders... Oh my God....

      Delete
  9. Bisrat gena bizu enayalen. Ahun ahunema mehateb (mateb) madereg gemerewal. Gera gebtuachew gera yagabalu.

    ReplyDelete
  10. Kale Hiwot yasemale Dingle Mariam Kene lejuwa tetebekeh. Ewnetem Bereketene Yetem metale

    ReplyDelete
  11. እግዚአብሄር ያበርታህ!
    kp it up!

    ReplyDelete
  12. እግዚአብሄር ያበርታህ!
    kp it up!

    ReplyDelete
  13. Ewnet naw .....Hulum beleyem marefiyaw netsehit kedest wede honechew tewahedo naw....Egzihabeher tagashe naw..Enesu amelknaw yalut amlaken eyesedebu....sele kedusan keber saygebachew, netset selehonech enatachen dengel mariyam keber amalajenet,enatenet,Redehetuan saykemesu eskemech yezelkut yehone....Le hulum gize alew endetebale hulum Ye cherenet,Ye fiker,ye Yekerta amlak yehonaw amlakachen leoul egziahbeher Lebonawen melesolachew wedezi leben mulu wedemiyadereg emnet endimetu melkam fekadu yehunelen...

    ReplyDelete
  14. Thank you, I have also a similar experience and decided not to attend such kinds of ceremony!

    ReplyDelete
  15. በርታ ግሩም ሂደት ነው:: እኛም አንባብያን ድካምህን ለፍሬ እንዲለው እንፀልይ አለን::

    ReplyDelete
  16. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ለዘለአለም ትኑር።

    ReplyDelete
  17. endetesasatu gebtuachewal lalemeshenef new, keman yisheshal

    ReplyDelete
  18. thank you brother.god bless ethiopia

    ReplyDelete