ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Monday, March 19, 2012

ከአንዱ አቅጣጫ ሲሸነፍ ከሌላ አቅጣጫ ይነሣል


በዳንኤል ክብረት 
 ከዳንኤል እይታዎች ተወሰደ

     ወደ
 ዝቋላ አያሌ ወጣቶች ከአዲስ አበባ፣ ከደብረ ዘይት እና ከናዝሬት በመጉረፍ ላይናቸው፡፡ የእነዚህ ወጣቶች ወደ ቦታው መንቀሳቀስ ቢያንስ እሳቱን ወደ ገዳሙ ዘልቆበመነኮሳቱ መኖርያ እና በአብያተ ክርስቲያናቱ ላይ አደጋ ከማድረስ ታድገውታል፡፡ ወደወንበር ማርያም ከተጓዙት የውኃ ቦቴዎች በወጣቶች ኃይል በማጓጓዝ፣ እሳቱ በመጣበትአቅጣጫ የሚገኙ የተወሰኑ ዛፎችን በመቁረጥ እና ሣሩን በማንሣት እሳቱ እንዳይተላለፍ አድርገውታል፡፡ ወደ አሥራ አንድ ሰዓት አካባቢ ተግ ካለ በኋላ በአሁኑ ሰዓት እሳቱ አጣብቂኝ እየተባለከሚጠራው ቦታ እስከ ዓርብ ረቡዕ ድረስ ባለው ቦታ ላይ ማምሻውን እንደገና የመጣሲሆን ወደ ገዳሙ እንዳዘልቅ ለማድረግ በአካባቢው የደረሱት ወጣቶች ነቅተው በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡በአካባቢው የሚገኙ የአደጋ ተከላካዮች እንደሚገልጹት እሳቱ አንድ ጊዜ እየቆመ ሌላ ጊዜካልታሰበበት አቅጣጫ ይመጣል፡፡ ይህም የመከላከሉን ሥራ ከባድ ያደረገው ሲሆን እሳቱጠፍቷል የሚል መረጃ እንዲሠራጭም አድርጓል፡፡

የገዳሙ መነኮሳት እንደገለጡልኝ አሁን ችግሩን ለመቋቋም ሁለት ዓይነት ተግባራትያስፈልጋሉ፡፡ በአንድ በኩል ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡት በጎ ፈቃደኞች መጥ ረቢያ፣አካፋ እና መቆፈርያ እየያዙ ቢመጡ የመከላከሉን ሥራ የተቃና ያደርገዋል፡፡ በተለይምአቅና የሚባለው የመቆፈርያ ዓይነት ለዚህ ሥራ አመቺ በመሆኑ ይህንን መሣርያ ይዘውእንዲመጡ ጥሪ አድርገዋል፡፡
ሁለተኛው ደግሞ በሚቻለው ፍጥነት ሁሉ እሳት የማጥፋቱን ተግባር በአውሮፕላን ወይንምበሄሊኮፕተር ለማገዝ እንቅስቃሴ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህ ተግባርም የመንግሥትን ድጋፍማፈላለግ ያለበለዚያም በግል ተነሣሽነት ወጭውን በመሸፈን የእሳት ማጥፊያ አውሮፕላንወይንም ሄሊኮፕተር ወደ ቦታው እንዲሄድ ማድረግ ወሳኝ መሆኑን በቦታው የሚገኙትየአደጋ ተከላካዮች ገልጠዋል፡፡
ከተለያዩ ከተሞች ወደ ገዳሙ የዘለቁት ምእመናን ሌሊት እና ቀን ያለ ዕረፍትየሚያደርጉትን ተጋድሎ ምግብ እና ውኃ በማቅረብ፣ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ እና በጸሎትእንድናግዛቸው ጥሪ ቀርቧል፡፡
በእግዜአብሔር እርዳታ፣ በአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም አማላጅነት፣ በሁላችንም ትብብርአደጋውን መቀነስ ተችሏል፡፡ እሳቱ ግን ገና ፈጽሞ አልጠፋም፡፡ እናም ይበልጥ ተረባርበን ችግሩን እንዳይመለስ አድርገን መፍታት አለብን፡፡ እያንዳንዷ ሰዓት የራስዋ ዋጋ አላትና፡፡

No comments:

Post a Comment