ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Sunday, May 27, 2012

ይድረስ ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን!

CLICK HERE FOR PDF

     አደይ ኢትዮጵያ… ል አስመራ


 …መች ነው የምንገናኝ ከምወዳት እህቴ

አልቆልኝ የማየው የአምሳ ዓመት ናፍቆቴ፡፡        

                                               [ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል 1937 ዓ.ም]
                                                          በፍቅር ለይኩን፡፡

                                                                                
       ለዚህ መጣጥፍ መነሻ የሆነኝ ከዛሬ ሰባ ዓመት ገደማ በፊት በ1937 ዓ.ም ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል ‹‹የሐማሴን ድምፅ›› በኋላም ‹‹የኤርትራ ድምፅ›› በተባለው ጋዜጣ ላይ ያወጧት ግጥም ናት፡፡ ይህች ጋዜጣ ለኢትዮጵያና ለኤርትራ አንድነት የሚታገሉ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ድምፃቸውን የሚያሰሙባት መድረክ ነበረች፡፡ በአጋጣሚ ለታሪክ ምርምርና ጥናት ሥራዬ በእጄ የገባችው ይህች ጋዜጣ ስለ ትናትናዎቹ ሁለቱ ሀገራት ወደኋሊት በታሪክ ሰረገላ ተጉዤ በጥልቅ እንዳስብ አስገደደኝ፡፡ ይህን በኅሊናዬ እያወጣሁ እያወረድኩ ሳለሁም በቴዲ አፍሮ የተዜሙት ሁለቱ ዜማዎች ‹‹ዳህላክና ፊዮሪና›› በአእምሮዬ መመላለስ ያዙ፤ እናም በዚሁ መንፈስ የክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል ግጥም፣ የቴዲ አፍሮ ፊዮሪና ዜማና የትናንት ታሪካችን እውነት በውስጤ ያጫረው ስሜት ይህን አጭር መጣጥፍ ሊወልድ ቻለ፡፡ በቅድሚያ ግን በከፊል በዚህ ጹሑፍ ውስጥ ያካተትሁትን የዶ/ር ከበደ ሚካኤልን ግጥም እነሆ ልበል፡-


እንደነ ኡጋዴን ደግሞ እንደነ ባሌ
ሐማሴን ደሜ ነች ሥጋዬን አካሌ
ይህን ጉልህ ነገር ማነው የሚል አሌ፡፡
የእሷና የእኔ ቤት ምሰሶው አንድ ነው
አትተዋወቁም የሚለው ሰው ማነው፡፡
ዘላለም ምን ጊዜም ከዱሮ ከጥንት
በሁለተናችን የለም ልዩነት፡፡
አንድ አካል መሆኑን የእኔም የእስዋም ገላ
ዶጋሊ ላይ መልካም መስክሯል አሉላ፡፡
መች ነው የምንገናኝ ከምወዳት እህቴ
አልቆልኝ የማየው የአምሳ ዓመት ናፍቆቴ፡፡ 
      

በክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል በዘመናቸው መቼ ነው ምንተያየው ‹‹ከምወዳት እህቴ›› ብለው በናፍቆት ቃል የጠሯትን ሐማሴንን/ኤርትራን ከብዙ ዓመታት በኋላም በታሪክ አጋጣሚ በወጣቱ ከያኒ በቴዲ አፍሮ ዜማ ዳግመኛ በናፍቆትና በስስት እየተነሳች፣ እየተጣለች ነው፡፡ በክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል እና በቴዲ አፍሮ መካከል ያለውን የዘመን ልዩነትና በሁለቱ ሀገራት የተከሰቱት በርካታ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ለውጦች እንዳሉ ሆነው ግን ሁለቱ አባትና ልጅ በግጥማቸው ያነሷቸው አሳቦች ቢዛመዱብኝና ስሜታቸውን ብጋራቸው ይህችን የታሪክ ሕያው ምስክር የሆነችው በክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤልን የተጻፈውን ግጥም ለጹሑፌ መነሻ በማድረግ በቴዲ አፍሮ ‹‹ፊዮሪና›› ዜማ ውስጥ ታሪካችን ምን እውነት ይነገረናል በማለት አጭር ቅኝት ለማድረግ ወደድሁ፡፡

ጥበብን አፍቃሪው ቴዎድሮስ ካሣሁን ከሰባት ዓመታት በፊት ‹‹ያስተሰርያል›› በሚለው አልበሙ የሀገራችን የዘመናት የመውደቅና የመነሳት ታሪክ፣ ወቅታዊ የሆኑ ፖለቲካዊ ትኩሳቶችንና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችንና የማኅበረሰባችን የሺህ ዘመናት እሴቶችና የሕይወት ዋጋዎች ላይ በሙዚቃው ባነሳሳቸው ትላልቅ ቁም ነገሮች የተነሳ የብዙዎችን ቀልብ የገዛና ኪነ ጥበብ የሕዝብ ብሶትና የልብ ትርታ አንደበት የመሆን ሚናዋንና አንድምታዋን ገና በአፍላ ዕድሜው ያለ ፍርሃትና ሥጋት ጥበብ የጣለችበትን አደራ ለመፈጸም የሚታትር የፍቅርና የጥበብ ምርኮኛ መስፍን መሆኑን በሥራዎቹ እያሳየን ያለ ይመስለኛል፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያ፣ በመሪዎቻችን፣ በፓርቲዎችና በፖለቲከኞቻችን፣ በሃይማኖት አባቶችና ተቋማት እንዲሁም በእኛና በሕዝባችን መካከል ሊሰፍን ስለሚገባው ፍቅር፣ ሰላም፣ አንድነትና የይቅርታ መንፈስ በሙዚቃዎቹ ድምጹን ከፍ አድርጎ ያሰማው ቴዲ አፍሮ፣ ይቅርታንና ፍቅርን ከመስበክ ባሻገርም በደም፣ በሃይማኖት፣ በባሕልና በቋንቋ ስለተሳሰሩት ዛሬም ድረስ በተለይ በቀደሙት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ዘንድ ማይደበዝዝ ትዝታ የታተሙትን የሁለቱን ሕዝቦች የናፍቆት ስስት እነሱን ሆኖ ይሄን ናፍቆታቸውንና ብሶታቸውን ለመግለጽ የዘመኑ የፖለቲካ ፍርሃት ቆፈን ደማቸውንና ወኔያቸውን ላቀዘቀዘው ወገኖቻችን ድምጽ በመሆን ቴዲ አፍሮ ‹‹ዳህላክና ፊዮሪና›› በሚል ዜማው ለሁለቱ ሀገራት ሰላምንና አንድነትን አጥብቆ ሲለምንና ሲመኝ እንሰማዋለን፡፡

ዛሬም ዳግመኛ ‹‹በጥቁር ሰው›› አልበሙ ቴዲ በናፍቆት ሰለሚቃጠልላትና በደሙ ውስጥ የሰረጸች ስለምትመስለው ኤርትራ ‹‹ፊዮሪና›› በሚለው ዜማው አስመራን ያንቆለጳጵሳታል፣ በሰሰቀቀን ያስባታል፣ በናፍቆት ቃልም ይጠራታል፡፡ ያስገረመኝ እኔ እስከማውቀው ቴዲ አፍሮ ኤርትራን በመንፈስ ካልሆነ በአካል ሄዶ እንዳላያትና እንዳልኖረባት እርግጠኛ ነኝ፡፡ ግን እንዲህ አንጀቱ እስኪንሰፈስፍና በትዝታና በናፍቆት ራብ እንዲህ እንደ ሽንብራ እየተንገረገበ ስለ ውቧ አስመራ ማዜሙ ለአንዳንዶች እንቆቅልሽና ጥያቄን የሚያጭር ሆኗል፡፡ እንደውም አንድ ወዳጄ ምናልባት ቴዲ በልጅነቱ ወይ በሰፈራቸው አሊያም በትምህርት ቤቱ በጣም የሚወዳት ኤርትራዊት አሁን ግን በሁለቱ ሀገሮች በተፈጠረው መለያየት የተነሳ ተለይታው የሄደች አንዲት ውብ አስመራዊት ቆንጆ ‹‹ፊያሜታ›› ሳትኖር አትቀርም በቴዲ ልብ ውስጥ እንዲህ ተሰንቅራ እረፍት የነሳችው በማለት ፈገግ አሰኝቶኛል፡፡

በእኔ እሳቤ በእርግጥ እንዲህ ውስጥን በሚንጥ ትዝታና ናፍቆት ውብ አስመራን/ኤርትራን ለማሰብ የግድ እንደ በዓሉ ግርማ በኤርትራ የተፈጥሮ ውበትና የተራሮቿ ግርማና ሞገስ መመሰጥ፣ በሐማሴን፣ በሰራኤና በመንደፈራ እናቶች ፈገግታ፣ እንግዳ ተቀባይነትና ጨዋነት ልብ እንዲጠፋ፣ በአስመራ ከተማ ውበት መዋኘትና በዝንባበባዎቿ መካከል መንሸርሸር፣ አሊያም በዳህላክ ደሴቶችና በምጽዋ ባሕር ዳር በነፋሻማ አየር በአሸዋው ላይ መራመድና በደስታ መቦረቅ፣ መፈንጠዝ አለበት/አለብን ብዬ አላስብም ቴዲ አፍሮም ሆነ እኛ፡፡ ትዝ የሚለኝ ከዚህ ጋር በሚመሳሰል ሁናቴ ቴዲ አፍሮ ‹‹ያስተርያል!›› አልበሙን ባወጣ ሰሞን ከሸገር ራዲዮ የጨዋታ ፕሮግራም ላይ ባደረገው ቃለ መጠይቅ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ አንድ ጥያቄ አንስታለት ነበር እንዲህ በማለት፡- ‹‹ቴዲ አንተ ገና ወጣት ነህ በዘፈንህ ውስጥ ደግሞ ስለ ኃይለ ሥላሴ ልክ በዘመናቸው የነበርክና ለዛና ጣእማቸውን የምታውቅ ያህል በስሜት ውስጥ ሆነህ ዘፍነህላቸዋል ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ…›› ቴዲም ሲመልስ፡-

‹‹… በእርግጥ ትክክል ነሽ የእንኳን ኃይለ ሥላሴን ለዛና ጣዕም ለማወቅ ቀርቶ በእርሳቸው ዘመን እንኳን ገና አልተወለድኩም፣ አልታሰብኩም ነበር፡፡ ግን ለምሳሌ እኔም አንቺም ክርስቲያኖች ነን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ደሙን አፍስሶ ቤዛ ስለሆነን ክርስቲያኖች/የእግዚአብሔር ልጆች ለመባል በቅተናል፤ ግና ጌታችን ኢየሱስ ስለ እኛ የከፈለውን ታላቅ የፍቅር ውለታ ለማሰብም ሆነ ክርስቲያን ተብሎ ለመጠራት የግድ የዛሬ ሁለት ሺ ዓመት መወለድ ያለብን አይመስለኝም እናም ኃይለ ሥላሴን ለማወደስና ለመዘከር ለእኔ ሥራቸው ከበቂ በላይ ምስክር ይመስለኛል ››
በማለት በጥበብ የተሞላ ምላሽን ለተወዳጇ ጋዜጠኛ ለመዓዛ ሰጥቷት እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡

ስለሆነም ቴዲ አፍሮ ስለ አስመራ ለመዝፈን የግድ አስመራን በአካል ሊያውቃት ይገባል የሚል ጭፍን ተከራካሪ ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ በቴዲ በልቡ፣ በነፍሱና በደሙ ውስጥ ዘልቃ የገባቸው አስመራ እንዲሁ በድንገት ደርሳ በቴዲም ሆነ በሌሎቻችን ኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ አልሰረጸችም፡፡

በበኩሌ ለረጅም ዘመናት በመከላከያ ሚ/ር በመኮንንነት በኤርትራ የተለያዩ ግዛቶችና በአስመራ በውትድርና መስክ ለብዙ ዓመታት የቆየው አባቴ ሁሌም ስለ አስመራ ቢናገር የማይሰለቸው እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ የሕዝቡ ሃይማኖተኝነት፣ እንግዳ ተቀባይነት፣ ውብ የሆኑት የአስመራ ከተማ ዝንባባዎች፣ ለጤና ተስማሚ የሆነ አየሯ፣ ማታ ማታ በነፋሻዋማ የአስመራ መንገዶች፣ መዝናኛዎችና በምጽዋ የባሕር ዳርቻ የሚጠጡት የአስመራ መሎቲ ቢራ፣ የምጽዋና የዳህላክ ደሴት የባሕር ዳርቻ የአሸዋው ላይ የተፈጥሮ መኝታና የቀይ ባሕር ላይ የሚታየው የጀንበር መጥለቅ ልዩና መሳጭ የተፈጥሮ ትእይንት ለአባቴ ከልቡ የማይጠፉ ትዝታዎቹና ሁሌም በልዩ አድናቆት ተሞልቶ የሚያወራልን ትዝታው እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡

የቴዲንም ያህል ባይሆን በአባቴ ልብ ውስጥ በትዝታ ነግሳ ሁሌም በአፉ የማትጠፋው ጓል አስመራ በእኔ የልጅነት ልብ ውስጥም ሚጢጢዬ የጉጉትና የናፍቆት ኮረብታን ለመስራት ችላ እንደነበር ትዝ ይለኛል፣ ከዛም ደግሞ ልጅነቴ አልፎ በሥራና በትምህርት አጋጣሚ በኢትዮጵያ ታሪክና ቅርስ፣ በአፍሪካውያንና በአፍሪካ አሜሪካውያን የነጻነት የፖለቲካ ትግል የማደርጋቸው ጥናቶችና ምርምሮች የሀገራችን የረጅም ዘመን ስልጣኔ፣ አኩሪ የነፃነት ተጋድሎ ታሪክና የአድዋ ድል በአፍሪካና በጥቁሩ ዓለም ያላቸውን ታላቅ ክብር የሚዘክሩ ያጋጠሙኝና የመረመርኳቸው ታሪካዊ ሰነዶችና መዛግብቶች ደግሞ ይበልጡን ስለ ትናንት እኛነታችን እና ማንነታችን ለመፈተሽ በውስጤ ልዩ ስሜትን አጫሩብኝ፡፡ ‹‹የአደይ ኢትዮጵያ… ጓል አስመራ…!›› መጣጥፍ ውልደትም ውሉ የተመዘዘው በሥራዬ አጋጣሚ ከተፈጠረብኝ ከዚሁ የታሪክ እውቀት ፍቅርና ምርምር የተነሳ ይመስለኛል፡፡

ስለሆነም በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የነበረውና አሁንም ያለው ጥብቅ የሆነ ታሪካዊ ትስስር እንደ ድልድይ የቆሙት በደማቸውና በአጥንታቸው ለሀገራቸው አንድነት መስዋዕት የሆኑት የእነ አውአሎም፣ የእነ ዘርዓይ ደረስ፣ የእነ ሞገስ አስግዶምና አብርሃ ደቦጭ፣ የእነ ብላታ ሎሬንዞ ታእዛዝ፣ የእነ ብላታ ኤፍሬም ተወልደ መድኅን፣ የእነ ፊታውራሪ ገ/መስቀል ወልዱ፣ የእነ ዶ/ር ተስፋዬ ገ/እግዚእ፣ የጥቁር አንበሳ መስራቾች መካከል በኋላም በጣሊያን ፋሽስት ከአይሮፕላን ላይ ተወርውሮ እንዲሞት የተደረገው የሌ/ኮረኔል በላይ ኃይለ አብ …ወዘተ ለቁጥር የሚበዙ በርካታ የሁለቱ ሀገራት ጀግኖች በኢትዮጵያና በኤርትራ ምድር በደማቸው የፃፉት ታሪክና የለኮሱት የነፃነትና የአንድነት ቀንዲል በብዙዎቻችን ልብ ውስጥ በታሪክ ቅብብሎሽ ቦግ እልም ስለሚልና በልባችን ጽላት በደም ስለተጻፈ እንጂ መቼም እንዲሁ በድንገት ደርሰን አይመስለኝም ስለ ኤርትራ ሲወራ ደማችን የሚሞቀው፣ መንፈሳችን የሚሸፍተው፡፡

እናም ቴዲ ይህ የታሪክ እውነት በልቡ ተሰንቅሮ እረፍት አልሰጠው ብሎ ይመስለኛል ከአድማስ ማዶ ያለችውን  ኤርትራን ዘንድሮም ‹‹በጥቁር ሰው አልበሙ በፊዮሪና ዜማው›› አስመራን እንዲህ የተቀኘላት፡-

ከዓይኔ ያራቀሽ መንገድ ያ ጎዳና

ወስዶ ቢነጥልሽ ጓል አስመራ

ጋራው ቢከልለን ያ ተራራ

አትወጪም ከሐሳቤ ጓል አስመራ፡፡

ቴዲ እነዚህ ሁለቱ የተለያዩ ልቦች የተራራቁ በናፍቆት ትዝታ እየተንገበገቡ ያሉ ነፍሶች አንድ ቀን እንደሚገናኙና ያን ቀንም በተስፋ፣ በስስትና በናፍቆት እንደሚያስበው ይነግረናል እንዲህ ሲል፡-

ዘመን አልፎ ዘመን እስኪታደስ

ቀኑ ቢመስልም የማይደረስ

በፍቅር ሲቃና መሰረቱ

ደሞ እንደ አዲስ አንድ ይሆናል ቤቱ፡፡

ምን ዓይነት እምነት፣ ምን ዓይነት ጽኑ ተስፋ እንዴት ያለ ተማጽኖ ነው ቴዲ አፍሮ እየተማጸነ ያለው በዚህ ሁሉ ተማሕጽኖውና ጭንቅት ውስጥ ደግሞ ቴዲ የዘመን ፖለቲካ፣ የዘመን ውጥንቅጥ ከልቡና ከአካሉ የለያትን ፍቅሩን ጓል አስመራን አንድ ቀን እንደሚያያት በጽኑ ድፍረትና እምነት ሲናገር ይህ ሰው ምን ታይቶት ነው አያሰኝም ትላላችሁ… አሊያም ይህ ልጅ ነቢይ ይሆን ወይንስ ወልይ ሊሆን ይቃጠዋል እንዴ በማለት ራሳችሁን አልጠየቃችሁም ክቡራን አንባቢዎቼ፡፡

በጹሑፌ ማጠቃለያ ላይ ጥቂት ነገሮችን ለማለት እወዳለሁ፤ ይህን ጹሑፍ ለመጻፍ የተነሳሁበት ዋንኛው ምክንያት በእነዚህ ሁለት ሀገራት ሕዝቦች መካከል ያለው ከብረት የጠነከረና የጋራ የሆነ ታሪካዊ ትስስር፣ ቋንቋ፣ ባሕልና ሃይማኖት መሠረት በማድረግ ለጋራ ሰላም፣ እድገትና ብልጽግና የአብሮነት መንፈስና ትብብር እንዲሰፍን የበኩሌን የብዕር መዋጮ ለማድረግ ከሚል ቅን መንፈስ በመነሳሳት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ የብዙዎቻችን ምኞትና ጸሎት እንደሆነ አስባለሁ፡፡

እንደማስታውሰው በአሜሪካና በአካባቢው በሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ትብብር ግንቦት 7 ቀን በ2001 እና ከመጋቢት 3-5 2002 ዓ.ም በአሜሪካ ካሊፎረኒያ ግዛት በሳን ሆዜ ‹‹የኢትዮጵያና የኤርትራ የወዳጅነት ጉባኤ›› በሚል የሁለቱ ሀገራት ምሁራን ሰፋ ያሉ ጥናታዊ ጹሑፎች ያቀረቡበትና በቀረቡትም ጥናታዊ ጹሑፎች ላይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ተወላጆች በንቃት የተሳተፉበት ጉባኤ ተካሂዶ እንደነበር ከመረጃ መረብ ላይ ማንበቤብ አስታውሳለሁ፣ በጊዜውም ደስታ ተሰምቶኝ ነበር፡፡

በእነዚህ ሁለት ስብሰባዎች ላይ የጥናት ወረቀታችን ካቀረቡት መካከል ኤርትራዊው ፕ/ር ተስፋ ጽዮን መድኃኔና ኢትዮጵያዊው ምሁር ፕ/ር ዳንኤል ክንዴ ይጠቀሳሉ፡፡ በተለይም ፕ/ር ዳንኤል ክንዴ በሁለቱ ጉባኤዎች ባቀረቧቸው ጹሑፎች ‹‹የኢትዮጵያና የኤርትራ ፌዴሬሽን አስፈላጊነት›› እና ‹‹ኢትዮጵያና ኤርትራ ከየት ወደየት›› በሚል ርዕሶች ያቀረቧቸው ጹሑፎች ለሁለቱ ሀገራትም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የወደፊት መፃኢ እድል፣ ሰላምና እድገት ተስፋ ፈንጣቂ የሆኑ እሳቤዎች የተንጸባረቁበት ጥናታዊ ጹሑፎች እንደነበሩ አሁን ከዓመታት በኋላ የጥናት ወረቀቶቻቸውን ሳገላብጥ መገንዘብ ችያለሁ፡፡

ይህ የወዳጅነት ጉባኤ እስከአሁንም ቀጥሎ ይሁን ይቋረጥ መረጃው የለኝም፤ ግና በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ሀገራት እንዲህ ዓይነቶች ጉባኤያትና ውይይቶች መልካም ግንኙነቶችንና ሰላምን የሚያሰፍኑ ጉባኤዎችና የስብሰባ መድረኮች መልካም እንደሆኑ የዚህ ጹሑፍ አቅራቢ በእጅጉን ያምናል፡፡ በተጨማሪም የሁለቱም ሀገራት የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን የጀመሩትን ጥረት አብልጠው ይገፉበት ዘንድ በግሌ አደራ ለማለት እወዳለሁ፡፡ በተጨማሪም እኔና ትውልዴ የትላንትናውን የሀገሮቹን ታሪክ ወደኋላ በመጓዝ በማጥናትና በመመርመር መቀራረብና በወንድማማችነት መንፈስ ማውራት የምንችልበት ዕድል ይፈጠር ዘንድ የበኩላችን ጥረት ማድረግ ይገባናል እላለሁ፡፡

ዓለም ስለ አንድነት በሚያወራበት በግሎባላይዜሽን ዘመን እንደገና ልዩነቶቻችንን ማስፋት ጠቃሚ መስሎ አይታየኝም፡፡ ለትምሕርት በደቡብ አፍሪካ ቆይታዬ ያየሁትና የታዘብኩት የደስታ ስሜትን ያጫረብኝ አንድ ገጠመኝ አለ፤ ይኸውም በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በአንድነት አምልኮተ እግዚአብሔር የሚፈጽሙበት የአንድነትና የወንድማማችነት መንፈስ ነው፡፡ እንዲሁም ፕሪቶሪያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ኤርትራውያን ወጣቶች፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ሰራተኞች በየሳምንቱ እየተሰባሰቡ በቋንቋቸው እርስ በርሳቸው ሲማማሩና በቤተ ክርስቲያናቱ ዓመታዊ በዓሎችና መንፈሳዊ ጉባኤዎችም ላይ በትግሪኛ ቋንቋ መዝሙር ሲያቀርቡ በማየቴ በጊዜው ልዩ ስሜትን አጭሮብኛል፡፡

እንዲህ ዓይነቶቹን ፍቅርና አንድነት የሞላባቸውን ግንኙነቶች በማጠናከር በኩል የሃይማኖት አባቶች በሕዝብ ዘንድ ያላቸውን ትልቅ ተቀባይነትና ተሰሚነት በመጠቀም በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለው ሰላምና ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው ይቀጥሉበት ዘንድ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ያግዛቸው ለማለት እወዳለሁ፡፡ በማይበጠስ ታሪክ፣ ባሕል፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋና ደም የተሳሰርን እኛ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ሕዝቦች ለፍቅር፣ ለሰላምና ለእድገት እጅ ለእጅ የምንያያዝበት ጊዜው አሁን ይመስለኛል፡፡ የእኔን አበቃሁ እስቲ ሌሎችም በዚህ ጉዳይ ላይ ጻፉና በጨዋነትና በቅንነት መንፈስ እንወያይ ለማለት እወዳለሁ…!!!

ሰላም! ሻሎም! 

15 comments:

  1. huletegna amet tejemere ande negre lemesiker ante bizu yemesrat akim alek kaliteganene kezi behula bizowoch yemyanebut yanite yihonale betelye image crativitik yemegrem new bizuwochun ayehulik batam gobez endehonek ena leleloch tsehafiwoch ariaya tihonalek betinish negre bizu negre megilets endemichale ena melikt masetalalfe endemichal. betriu huneta jemerekawal keeeeeeeeep goin

    ReplyDelete
  2. Thank you this is what we need for your reference pls find on the following websites photos of ASmara
    http://www.ethiopianreview.com/forum/viewtopic.php?t=2591

    ReplyDelete
  3. Bisrat, cher neger endinisema egziabiher yirdan!! Beterefe yih netsana kin yehone akerarebih....beliyunetachin endinketil yemifeligin wegen enkuan kom bilo endiasib sayadergew yikeral bileh new ....lemehonu beliyunetina betorinet min yigegnal? lezih degmo kegna ke Ethiopiawian ena Eritrawean yebelete misikir ayinorim...and yemawkatin nebar ababal libelina labka....Torinet ketewagiwochu wogenoch sost (3) negerochin yishal 1) werk ( Gold) 2) werk (Gold) 3)werk (GOLD)....sitaked, bewigiaw mehalina kewigiaw (ketorinetu) behuala malet new....Tadia yanin bakagn werk...lehibret, leginbata, le menfasawi timret binawilew....min yahil yaderejen ..min yahil yagolebiten yihon?? BIsrat bekenanetih berta...Egziabiher yibarkih!!!!

    ReplyDelete
  4. ብስራት በዚህ ጥሁፍህ ምስላቸውን አስቀምጠህ ስለተነሳህባቸ ሁለቱ ሀገሮች ይልቅ አድናቆትህ ያደላው ስለ አዝማሪው ነው። አድናቆትም በአንድ ዓይነት አገላለጥ በድግግሞሽ ስለሆነ የጽሑፉን ዋጋ አወረደብኝ ። እኔ የማቅህ በመንፈሳዊ ጋዜጣ ጽሑፎችህ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ አዝማሪ ቤት ማምሽት ጀመርክ መሰልኝ አያያዝህ አላማርኝ ።በመንፈስ መጀመር በሥጋ መጨረስ ማለት እኮ ይሄ ነው ።
    ከሀገረ አሜሪካ !

    ReplyDelete
    Replies
    1. teru Akerarebe newoe Sele hager temelekete Ye Tedy Afro yelekena Yesetane(Evil Song ) be noreme mesematena sele selame be negere Teru newoe
      Dear the blogger @Bisrate go head its good Article so appreciate
      K Addis Ababa

      Delete
    2. before you write sth stupid look who wrote the article frist

      Delete
  5. Wow, thank you Bisrat this is our dream! this is what we want and hopefully comes in the near future.

    ReplyDelete
  6. a day will come .......................

    ReplyDelete
  7. ye AZMARIWOCHN hasab lemetenten kebad ymeslegnal.negeru lehuletu hzb selam kehone cher engdih! negeru gn Eritrean ke Ethiopia 1 lemadreg kehone gn ANTE SEW AHUNS YEDEM TMAT ALEBH ENDIE lemalet edefralehugn;

    ReplyDelete
  8. እባብ ሔዋንን በውዳሴ ከንቱ እና ምንም አይደለም በሚል ሰበብ ነው የገባው ስለዚህ ብስራት ተጠንቀቅ፡፡ ሁሉ የራሱ ህግና ስርዓት አለው፡፡ የቀሳርን ለቀሳር የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር አይደል መፅሐፉ የሚለው፡፡

    ReplyDelete
  9. it is one side love as usual and it is from ethiopia to eritrea. it takes two to tango and eritreans have always failed to join the unity tone.

    ReplyDelete
  10. GOOD GOOD I ALSO LOVE ERTRYA I CONTACT WITH SOME ERTRIANS ON FACEBOOK, GENERALLY PLEASE TRY T ODESIGN UR BLOG IN A GOOD MANNER IT IS 1/2 HOWR WORK

    ReplyDelete
  11. ውይ ኣቃጣሪ ጠላን ቴዲ እውነት ልክ ቢሆን በዘመኑ ያየውን እውነት ለምነ ኣይመሰክርም መብራቱ ውሃው የ ማይደፈረውን ኣባይ የደፈረ መሪን ክቡር ጠቅላይ ምኒሰተር ለምን ኣልመሰከረላቸውም ደሞ ድንቁርናው ከ እየሱስ ክርስቶስ ያመሳስላል እንዴ እየሱስ ክርስቶስ ለ ኣለም ህዘብ የከፈለለው መስዋእተ እኮ በ መፃፍ ቅዱስ አና በተለያዩ ተኣምራቶች ማዎቅ ይቻላል እና ኣሁን ተዴ ስለ ሃይለስላሴ ከ የት ነው መረጃወ ያገኘው ከ ሃይለስላሴ ደጋፊዎች የተፃፈ እና እራሱ የጨመረበት ነው

    ReplyDelete