ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Wednesday, August 22, 2012

ለመማር ጊዜው አሁን ነው!


        ይኸው የጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ሕልፈተ ህይወት በመገናኛ ብዙሀን ከሰማን ቀናት መቆጠር ጀምረዋል፡፡ ሁሉም የሚዲያ አካላት የሀገር መሪ ስለሞተ በሚል አትኩሮታቸው እዚሁ ጉዳይ ላይ ነው፡፡ ሀሳቡ የሚደገፍና መልካም ነው፡፡ ለሀገር ለፍተዋል እንዲሁም ደክመዋል ተብሎ ሲታሰብ ማሰብ፣ ማወደስ ትክክል ነው፡፡ የትላትናው( ነሀሴ 15, 2004) ዕለት ምን አልባት በኢትየጵያ ታሪክ ብዙም ታይቶ የማይታወቅ እና የመጀመሪያ ልምዳችን ስለሆነ ብዙዎቻችን የመደናገጥና የመረበሽ ስሜት ነበረን፡፡ ድንጋጤው የመጣው አንድም የኢትዮጵያ መፃዒ ዕድል ገምተን ወይንም ደግሞ ፈጣሪ አንዳች ነገር በእዚች ሀገር ላይ ሊያደርግ ፈልጎ ከሆነ ብለን ነው፡፡
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ መፃዒ ሁኔታ አለማወቅ ያልነው በትክክልም ሊያሳስበን የሚገባን ነገር ነው፡፡ ይህም የሚለካው የቀድሞዎቹም ሆኑ አሁን ያየናቸው መሪዎች የሠሩልን እና የሠሩብን ነገር ስለማንረሳና ስለምናስታውስ ይህ ተፅዕኖ ቶሎ ስለማይለቅ ነው፡፡ ይህም ለመጪም ግዜ በጭንቀት እንድናስብ ያደርገናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ በጣም ከማከብራቸውና ጥሩ ስሜት ካለኝ ጥቂት የሀገሬ ሰዎች ውስጥ እመድባቸዋለሁ፡፡ በመልካምም ይሁን በሌላ መንገድ ሀገራችንን ለረጅም አመታት መርተዋታል፡፡ ለዚህም አክብሮቴ ትልቅ ነው፡፡

እኛ ሀገር ያሉ ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ በስራ አጋጣሚ ከማገኛቸው የውጭ ሀገር አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ጋር እንዲሁ ሳወራ የተረዳሁት ነገር ብዙዎቹ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ያላቸውን አክብሮትና አድናቆት ጥሩ የሚባልና ሁሉም ማለት በሚቻል ሁኔታ የሚገርም አዕምሮ ያላቸው መሆኑን ነው የገለፁልኝ፡፡ አውቃለሁ ሁሉም መሪዎቻችን ከሀገር ውጪ የተከበሩና ዝናቸው ከፍ ያለ መሆኑን፡፡ ይህ እውነት  መንፈሳዊ አባቶታችንንም ይጨምራል፡፡ ከላይ እንዳልኩት ለጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ያለኝ አድናቆትና ክብር በተለይ እስከ 1997 ምርጫ ድረስ ትልቅ ነበር፡፡ በእርግጥ ሀገር መምራት ትምህርት ቤት እንደመምራት ቀላል ላይሆን ይችላል፡፡ ብዙ ችግሮችና ውስብስብ ጉዳዮች ሊያጋጥሙ ይችላሉ፤ በተለይ እንደ እኛ ደሀ ለሆነች ሀገር መሪ መሆን ፈተናዎቹ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆኑ መረዳት ከባድ አይደለም፡፡ ትልቁን የሰው ነፍስ እስከማጥፋትም ሊዘልቅ ይችላል፡፡ ይህን ስል መግደል መገዳደል አንዱ የስራው አካል ነው እያልኩ አይደለም፡፡ መሆን አለበትም ተብሎ አይታሰብም፡፡
ድህነት የሚመጣው መልካም መሪ እንዲሁም ቅን ህዝብ ሳይኖር እና ሲቀር እንጂ በሌላ ምክንያት እንዳልሆነ እረዳለሁ፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን. . . . አሁን አሁን እንጂ ኢትዮጵያ የቅን ህዝቦች መሰብሰቢያ እና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው ህዝቦች መገኛ ምድር ነበረች፡፡ አብዛኛዎቹ ዲያስፖራዎችና ሁሉም መጤ ሀይማኖቶችም ይህንን ሁኔታ እንደማስቀጠል ሆዳምነትን እራስ ወዳድነትን ብቸኝነትን በሀገሪቱ አንሰራፉ፡፡ ይህም ኢትዮጵያነት እያደከመና ጥንካሬዋን እየወሰደ ያላትም ለዛ እየለቀቀ እንዲመጣ አድርጓል፡፡ መረዳዳት መከባበር የሚባሉ ዉበቶቻችን ጠፍተው በምትኩ እራስ ወዳድነት፤ አለመተዛዘን፣ ንቀት፣ ብልግና አምባገነንነት እየተስፋፋ መጥተዋል፡፡
እንግዲህ መንግስትም ይሁን መሪዎች የሚቀረፁት እና የሚወለዱት ከዚሁ የተበላሸ ህዝብ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ድሮ ኢትዮጵያ በስልጣኔ አንቱ ከሚባሉና ከሚከበሩ ሀገራት አንዷ ነበረች፡፡ እስከ ንጉስ ኃይለ ስላሴም ድረስ ተፅዕኖዋ ትልቅ የሚባል ነበር፡፡ የደረግ ስርዓትም የሚታወቀው በወታደራዊ ጥንካሬው እና እንዲሁ በባዶ ኢትዮጵያ ትቅደም በሚል መርዑ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ይበልጥ ህዝቡ በፍርሃት ወደ ቤተክርስቲያን እንዲያመራ ሲያደርግ በተቃራኒው መንግስቱ ደግሞ ኃይል በጦር፣ በጉልበት፣ በድፍረት እንጂ በፀሎት አይደለም በማለት ለቤተክርስቲያን፣ ለቅርስ ለታሪክ ቦታ አይሰጥም ነበር፡፡ ቤተክርስቲያን ሳይከበር ሀገርን ወደዱ ማለት ጉም እንደመጨበጥ ነው፡፡ የነገስታት ንጉስ የጌቶች ጌታ ተዘንግቶ ስለስልጣን ማውራት የዋህነት ነው፡፡ መሪን የሚሠጥ አምላክ ነው፡፡ ማንም ፈጣሪውን ማመን አለበት፡፡ እዚህ ላይ እንኳን ኢትዮጵያ ‹‹ሀጥያት›› ተንሰራፍቶባታል የምትባለው አሜሪካ እንኳን ‹‹ IN GOD WE TRUST ›› (በእግዚአብሄር እናምናለን) ብለው ገንዘባቸው ላይ በፅሑፍ አስፍረዋል፡፡ እኛ ግን በየህንፃው ላይ ‹‹ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ›› ከሚል ኃይለ ቃል በዘለለ ለሀገራቸው ቀን ከሌት የሚማልዱ አባቶችና እናቶች የሞሏት ቅድስት ሀገር ነው ያለችን፡፡ ሀገርን መውደድ፣ ሀገርን ማክበር ይህን ያህል ይሄዳል፡፡ ለምነውት የማይነሳ ጠይቀውት የማይረሳ አምላክ፤ ሲርበውም ሲጠማውም ከፀብ ይልቅ ‹‹ እግዚአብሔር የወደድከውን አድርግ ›› በማለት ሁሉን አሳልፈው ወሳኔውን የሚሰጡት ህዝቦች ወድቀው አይወድቁም፡፡ ምድሪቷን እንደተባረከች ትቆያለች
አፄ ቴዎድሮስ ለስልጣናቸው ማጠርና ለህይወታቸው ማለፍ በዋነኛነት የሚጠቀው ከቤተ-ክርስቲያን አባቶችና እናቶች ጋር አላስፈላጊ ፀብ ውስጥ መግባታቸው ነው( በቅርቡ አፄ ቴዎድሮስና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የሚል ፅሑፍ በቅርቡ በዚሁ ድረ ገፅ ይጠብቁ) ፡፡ የብዙዎቹን የኢትዮጵያ መሪዎች ታሪክ ብናይ ከሀይማኖትና እምነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሀይማኖትና መንግስታዊ ስርዓት ተያያዥነታቸው ጠንካራ ነው፡፡ ይህም የሆነው ሀገሪቷ መሰረቷ ቤተክርስቲያን ስለሆነ ነው፡፡ ብዙዎች ይህ ሲገባቸው እና ሲጠነቀቁ አይታም፡፡
እዚህ ላይ ኢህአዲግም ወደ ስልጣን ሲመጣ ይህ ነገር የገባው በሚመስል መልኩ ቤተክርስቲያን ላይ መድረስ አይገባም የሚል አቋም ያንፀባርቅ ነበር፡፡ እርግጥ ነው አቡነ መርቆሪዮስ እያሉ ሌላ አቡን መምጣታቸው፤ እንዲሁም ሌሎች ቅሬታዎች ሊኖሩ ቢችሉም እስካሁን ግን ሁሉን ቻይ የሆነው ምዕመን ሁሉን ለእግዚአብሔር ትቶ የሚመጣውን ይጠብቅ እንደነበር ግልፅ ነው፡፡ ይህን ባህል ከጥንትም የነበረ መሆኑን ታሪክ እና የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ፤ በግልፅም የሚታይ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን በሀይማኖት ምክንያት መንግስታቸው ለመቃወም ተነስተው የሚያውቁት በጣም ለሚቆጠሩ ጊዜያት ነው፡፡ የለምም ለማለት ያስደፍራል፡፡ እዚህ ላይ ስለኑሮ ውድነት ተቃውሞ አይደለም የማወራው ፡፡ በቅርቡ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በመንግስት ላይ ጥያቄ ወይም ተቃውሞ አንስተው ነበር ይህ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ልጆችን አይወክልም፡፡ የተቻለው ውይይትና ጥረት ከተደረገ በኋላ የሚሰማ ወይም እሺ ባይ ሲጠፋ እንባውን ወደ ሚመለከተው ገዳም ወይም ቤተክርስቲያን በመሄድ ያፈሳል፡፡
በቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ ይህ መንግስት ‹‹ህዝበ ምዕመኑ›› ጋር በዋልድባ የስኳር ልማት ጉዳይ የማይገባ ውዝግብ ውስጥ በመግባቱ በሁለቱም አካላት መካከል ውጥረቶች እየጨመሩ ሄደዋል፡፡ ይህ ማንንም አይጠቅምም፡፡ ለእግዚአብሔር ቤት ያሰበ እንጂ የሚያሸንፈው ጉልበታም የሆነ አይደለም፡፡ ለመናገር በሚከብድ ሁኔታ ፍፁም እግዚአብሔርን መፍራት እየጠፋ እንደሆነ በአካባቢው ይታያል፡፡ ከመነሻዬ ያልኩትም የአቶ መለስ ዜናዊ  እንዲሁም የአቡነ ጳውሎስ ህልፈተ ህይወታቸው መከታተሉ ያስጨነቀን ቀጣዩ ሁኔታችንስ የሚለው ያሳስባል፡፡ ኢትዮጵያ ዘውትር እጆቿን የምትዘረጋላት እና ጠባቂ እረኛዋ የሆነው ፈጣሪ ምን ሊያደርገን እንደፈለገ ይበልጥ ፍርሃታችንን ከፍ ያያደርገዋል፡፡ ወቅቱ የፆም ነው፤ ልመናዎች ሁሉ በአንድ ላይ የሚቀርቡበት፡፡ በዚህ ወቅት ስለሀገር ሰላም፣ ስለ መንግስታችን ፅናት ስለፍቅር፣ የበደሉንን ይቅር ስለማለት፣ ስለመባረክ. . . .የሚፆምበት የሚቀደስበት ፈታኝ ወቅት ነው፡፡ የሚፈሰው እንባ ፅዋውን ሞልቶ የፈሰሰ ጊዜ የሚነሳው የቁጣ ወይም የበረከት በትር አስፈሪ ነው፡፡ አሁንም ይህ የማይገባቸው ምስኪኖች ይኖራሉ፡፡  ከኛ የሚጠበቀው ተግቶ መፀለይ ነው፡፡
ይኸው አባታችን አቡነ ጳውሎስ አረፉ፤ ጠቅላይ ሚኒስትራችንም ተከተሉ፡፡ የሚማር ይማር፤የማይማርም አይማር፡፡ ጊዜ አለው የመማሪያ፡፡ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረውም መንግስት ቀድሞ ከሆነው፤ አሁንም ከሚሆነው ወደፊትም ከሚሆነው ቅጣት የሚማሩበት ትክክለኛ ወቅት አሁን ነው፡፡ ላለፉት ሀያ(20) ዓመታት ከድህነት ለመላቀቅ የተቻለው እየተሞከረ እንዳለ ይገባኛል፡፡ ዕድገትን ቶሎ ለማምጣት ሲታሰብ አብሮም ‹‹እንዴት›› የሚለውን በደንብ ማሰብ ይኖርብናል፡፡ ስኳር ስለለማ ሀገር አታድግም፡፡ መልማቱን ይልማ ግን እንዴት? መታሰብ አለበት፡፡ ጉዳዩ የምዕንድስና ጉዳይ አይደለም፤ ጉዳዩ መሬቱ ለም ነው አይደለም አይደለም፡፡ አዎ ህዝብ እግዚአብሔርን መንግስት ህዝብን ካልፈራ ተያይዞ መደፋት ነው፡፡ ስኳሩም መዘዝ ይዞ ነው የሚመጣው፡፡
አሁንም ጊዜው አልረፈደም፡፡ የመማሪያ የመለወጫ ጊዜ አለን፡፡ ገዳማትን ረብሸናል፤ ቤተ-ክርስቲያናትን አንገት አስደፍተን አዋርደናል፡፡ ሁሉን ሞክረን ጉልበታችንን ለማሳየት ጥረናል፡፡ ሁሌም የምንዘነጋው ጠባቂ ግን ከላይ ሆኖ ያያል፡፡ ከማየት አልፎ ሲገስፅ ግን ግሳፄውን ማንም አይቆመውም፡፡ እጅን አጣምሮ አርፎ ከማየት ያለፈ መጠየቅ እንኳን አይቻልም፡፡ ሁሉንም ነው የሚቀጣው፡፡ ምህረቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ እሺ ይቅር ማለት አሸናፊነት እንጂ ትንሽ መሆን አይደለም፡፡ በፓለቲካውም ቢሆን እሺ ማለትን የመሰለ ነገር የለም፡፡ የጥንቶቹ የኢትዮጵያ መሪዎች ፈጣሪን ፈርተው ሀይማኖት፣ባህል፣ ስነምግባር ቅርስ፣ታሪክ አስቀምጠውልን ከማለፋቸውም በላይ ቤተክርስቲያንን ለመገንባት፣ ቅርሶችን ለመጠበቅ ለማብዛት እጅግ ይለፉ ነበር፡፡ ውበታችን እነዚህ ናቸው፡፡ አትንኳቸው ከተቻለ የራስን አሻራ ልክ እንደቀድሞዎቹ ለማኖር መጣር ወይም እነሱ የተውልልን መጠበቅ ፣ማስከበር ለትውልድ ማቆየት ትልቅነት ነው፡፡ ታሪክ ማጥፋት የታሪክ ተወቃሽ ያደርጋል እንጂ ጀግና አያስብልም፡፡ የፃድቃንን ክብር መንካት፣ የአባቶቻችንን ልፋትና ድካም መና ለማስቀረት መጣር መጨረሻው ግልፅና ግልፅ ነው፡፡

ክብር ለእግዚአብሔር
ክብር ለኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!

6 comments:

  1. huletum kemaychlut gar tgl getemu witetu yihe hone besga.Benfsachws? beteley Abune Pawlos begochen thebek wey? teblo siteyek mn yimels yihone Begasaw kehone beg sayhon tekula new. dngl tamldwot edallwot bekidsnawo erswo endemibetuwat slemisbu ayaskedm.gn Abune Pawlos ngstitu yale tnte abso benigusu kegn kuma stayat mn alk?I'm waiting your answer.

    ReplyDelete
  2. ታሪክ ማጥፋት የታሪክ ተወቃሽ ያደርጋል እንጂ ጀግና አያስብልም፡፡

    ReplyDelete
  3. Both of them were dictators and under their administration, most Ethiopians suffered. To mention few, under Meles Zenawi order more than 200 Ethiopians were massacred and no one were brought to justice. Most mothers and fathers cried because they lost part of their family,but the dictator was celebrating his daughter graduation from high school at Sheraton Addis. Under Abune Paulos leadership, our church was divided in to two Synodos, the church was fallen under corruption, Abune Paulos did nothing about Waldeba Gedam rather he was celbrating his 20 years for about one month with our poor church money. Both these dictators die unexpectedly and never believed they will be facing justice from God. I hope they will get what they deserve.

    ReplyDelete
  4. i have a question to Biserat, pls tell me why u have big respect for Mellse zenawi ??? can u tell me ur reason?
    tnx

    ReplyDelete
  5. Bimaru tiru neber, ahunim gin be waldeba gedam yasemarwachewn polisochachewen kalyazu gena yalkalu. Hizbum hone gedamawyanu enbawen wedefetari mafses kejemere koye. Egziabher bete Christianen ena lehager lewegen yimitselyu menaniyanen yitebkelen. Betun ledefere tageso, tageso kutawen siametaw ersu yawkebetal Ena enante andand Federal polisoch bitarfu tiru new.

    ReplyDelete
  6. These are really wonderful ideas in concerning blogging.
    You have touched some good points here. Any way keep up wrinting.
    Check out my web page - car insurance quotes

    ReplyDelete