ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Sunday, July 24, 2011

ግዕዝ

 Ge'ez

                     በአፍሪካ ቀንድ በኢትዮጵያና በኤርትራ በጥንት የተመሠረተና ሲያገለግል የቆየ ቋንቋ ነው። በአክሱም መንግሥትና በኢትዮጵያ መንግሥት መደበኛ ቋንቋ ነበር። ዛሬ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥነ-ስርዓት እንዲሁም በኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና በቤተ እስራኤል ሥነ-ስርዓቶች እስከ ዛሬ ድረስ ይሰማል።

ቋንቋው የሴማዊ ቋንቋዎች አባል እየሆነ በደቡብ ሴማዊ ቅርንጫፍ ውስጥ ይከተታል። ደቡብ ሴማዊ በመባሉ ግዕዝ የሣባ ቋንቋ ቅርብ ዘመድ ነው። ግዕዝ የተጻፈው በግዕዝ ፊደል አቡጊዳ ነው። ይህም ፊደል ደግሞ ዛሬ ለአማርኛ ለትግርኛ ለሌሎችም ቋንቋዎች ይጠቀማል። በመላውም የአፍሪቃ አህጉር ውስጥ የመጀመሪያውና ብቸኛ አፍሪቃዊ የራሱን ፊደላት የያዘ ቋንቋ ሲሆን፣ በዓለምም ላይ ዋናና የስልጣኔ አራማጅ ከሚባሉት ቋንቋዎች አንዱ ነው።
በግዕዝ ጽሕፈት 26 ፊደላት ብቻ ይጠቀሙ ነበር፤ እነርሱም፦
ሀ፣ ለ፣ ሐ፣ መ፣ ሠ፣ ረ፣ ሰ፣ ቀ፣ በ፣ ተ፤ ኀ፣ ነ፤ አ፣ ከ፣ ወ፣ ዐ፣ ዘ፣ የ፣ ደ፣ ገ፣ ጠ፣ ጰ፣ ጸ፣ ፀ፣ ፈ፣ ፐ
ናቸው።
                   ሊቁ ሪቻርድ ፓንኩርስት እንደሚጽፍ፣ አንድ ተማሪ በመጀመርያው አመት ፊደሉን ከተማረ በኋለ፣ በሚከተለው አመት መጀመሪያይቱ የሐዋርያው የዮሐንስ መልእክትን ከአዲስ ኪዳን በግዕዝ ከትዝታ ለመጻፍ መማር ነበረበት። በሦስተኛው ደረጃ የሐዋርያት ሥራ በአራተኛውም መዝሙረ ዳዊት በግዕዝ ማስታወስ ነበረበት። ይህንን ከጨረሰ ታላቅ ግብዣ ይደረግና ልጁ ጸሐፊ ይሆን ነበር።
በብሪቲሽ ላይብሬሪ (የእንግሊዝ አገር ብሔራዊ በተ መጻሕፍት) ውስጥ 800 የሚያሕሉ የድሮ ግዕዝ ብራናዎች ኣሉ።
በኢ.ኦ.ተ.ቤ. ትምህርቶች ዘንድ፣ ግዕዝ የአዳምና የሕይዋን ቋንቋ ነበር። ፊደሉን የፈጠረው ከማየ አይኅ አስቀድሞ የሴት ልጅ ሄኖስ ነበረ። ከባቢሎን ግንብ ውድቀት በኳላ፣ ከአርፋክስድ ወገን የዮቅጣን ልጆች ቋንቋውን እንደ ጠበቁት ይባላል። የዮቅጣን ልጅ ሣባ ነገዶች ከዚያ ቀይ ባሕርን አሻግረው ወደ ዛሬው ኢትዮጵያ ያስገቡት ይታመናል። እንዲሁም ካዕብ እስከ ሳብዕ (አናባቢዎችን ለመለየት) ወደ ፊደል የተጨመረበት ወቅት በንጉሥ ኤዛና ዘመን እንደ ነበር ይባላል።
1 comment: