Showing posts with label መልዕክት. Show all posts
Showing posts with label መልዕክት. Show all posts
Tuesday, August 21, 2012
ለሁላችንም መፅናናትን ይስጠን፡፡
መደብ
መልዕክት
Monday, August 6, 2012
አደራ ኢትዮጵያን ፡ ለስም ሳይሆን ለባንዲራ ሩጡ
የለንደን ኦሎምፒክ ከተጀመረ ቀናቶች ተቆጥረዋል፡፡ ኢትዮጵያውያንም ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን ለመወጣት በቦታው ተገኝተዋል፡፡ ዛሬ ላተኩር የፈለኩት ሀገራዊ ግዴታ በሚለው ላይ ነው፡፡
እስቲ ከመክፈቻው ልጀምር በዚህ ውድድር ላይ የመጀመሪያው
ጥያቄ የመክፈቻው ስነ-ስርዓት ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ለዓለም የቀረቡት ጥቂት ሰዎች ላይ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች እራሳቸውን በታሪክ
መዝገብ ላይ ማስፈራቸው ዕድለኛ ያስብላቸዋል፡፡ ለነገሩ ካልተሳሳትኩ ሁሌም የሚታዩት እነዚሁ ናቸው፡፡ ነገር ግን እዚህ ላይ መነሳት
አለበት ብዬ የማምነው በእንደዚህ ዓይነት የመክፈቻ በዓል ላይ ሁሉም አትሌትና አብረው የተጓዙ አካላት በሙሉ የዚህ ክብር ፣ ታሪክ
ተቋዳሽ መሆን አለባቸው ብዬ ነው፡፡ ምክንያቱም በደንብ ካሰብነው
በስነ-ስርዓቱ ላይ መሳተፍ በራሱ ጥቅሙ ብዙ ነው፡፡ በዋነኛነት
ግን በእንዲህ ዓይነት የመክፈቻው ስነ-ስርዓት ላይ አዳዲሶቹን ልጆቻችንን ማሳተፍ በራሱ የሚያመጣው የአሸናፊነት
ስነልቦና በተጨማሪም የማሸነፍ ተነሳሽነትን መጨመሩ ነው፡፡
Sunday, August 5, 2012
ኢትዮጵያዊነት ከወርቅም በላይ ነው
ለኔ ኢትዮጵያዊነት ከወርቅም በላይ ነው፡፡ ማንም አትሌት ኢትዮጵያን እስከወከለ ድረስ ለማሸነፍ መሆን አለበት የሚሮጠው፡፡ የሮጠ ሁሉ ሀገርን ለማስጠራት ነው ብሎ ማሰብ ደግሞ ስህተት ነው፡፡ ስለአትሌቱ ብቃት፣ ስለ ጉዳቱ ወይም ስለ ሰራው ታሪክ እዚህ ጋር ማውራት አያስፈልግም፡፡ ካላቻለ አልቻለም ነው፤ መወቀስ ይኖርበታል፡፡ ጥሩ ከሰራም ጎበዝ፣ ጀግና ከማለት ባለፈ ታሪክ ሲያወሳው ይኖራል፣ ሲከበር ይኖራል፡፡ ‹‹ለኔ›› አይደለም የሚሮጠው ለሀገሩ እንዲሁም እራሱን በታሪክ መዝገብ ላይ ለማስፈር እንጂ፡፡
የትኛውም አትሌት የሀገር ስም ከፍ እንዲያደርግ ነው ሀገራዊ አደራ የተሰጠው እንጂ በደከመ ሰዓት ወይም በተሸነፈ ጊዜ ከዚህ ቀደም የሰሩትን ታሪክ እያነሳን ማወደስ ለግለሰቡ እንጂ ለሀገር አለማሰባችንን ነው የሚያሳየኝ፡፡ ሁሉም ያልፋሉ ሀገር ግን፤ ኢትዮጵያ ግን ሁሌም ትኖራለች፡፡ ባንዲራችን ዝቅ ብሎ ሲውለበለብ ለምን ብሎ መጠየቅ ተገቢና ሀገሩን ከሚወድ ሰው የሚጠበቅ ነው፡፡ ሌላ ምንም ትርጉም የለውም፡፡ ለሀገር እንጂ ለግለሰብ አንቆርቆር!! ቀልድ የለም ሀገሬ ከወርቅም በላይ ናት፡፡

ድል ለኢትዮጵያ!
መደብ
መልዕክት
Sunday, April 22, 2012
በማደግ ላይ ያለ
አዲስ ዓይነት ይዘት፣ በቀለማት ያሸበረቀና በማደግ ላይ ያለ አዲስ ዓይነት የግል ድረ ገፅ- ‹‹የብስራት
እይታ›› ከብዙ አንባቢያን በደረሰኝ አስተያየት ድረ ገፁ ከሚነበቡና ከሚታዩ ነገሮች በተጨማሪ የሚሰሙ ነገሮች ቢኖሩ ጥሩ እንደሚሆንና ተመራጭ
ሊያደርገው እንደሚችል ነው፡፡ ይህንን በማየት በድምፅና በምስል የተቀረፁ መንፈሳዊ መዝሙሮች በድረ-ገፁ ላይ መጫኑንና ማዳመጥ
የምትችሉ መሆኑን በትዕትና እገልፃለሁ፡፡
![]() |
| ‹‹የብስራት እይታ›› መለያ( Logo) |
ይህ ብቻ ሳይሆን ከመዝሙር በተጨማሪ ዘፈኖችን ማዳመጥ ለምትሹ ቆየት ያሉና ተወዳጅ ናቸው ያልኳቸውን ዘፈኖችንም እንዲሁ አካትቻለሁ፡፡ አሁን ‹‹የብስራት እይታ ››የሚያነቡት ብቻ ሳይሆን የሚያዩት የሚሰሙትም ሆኗል፡፡ የፈለጉት ያንብቡ የፈለጉትን ያዳምጡ፡፡
እዚህ ላይ ከአንዳንድ አንባቢያን በሚደርሰኝ አስተያየት ድረ ገፁ የሚያተኩረው መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ እንደመሆኑ ሌላ ዓለማዊ ነገር ሊኖረው እንደማይገባ ነው፡፡ ነገር ግን እውነታው እንደዛ አይደለም፡፡ ይህ ድረ ገፅ ሲቋቋም እንደዓላማ አድርጎ የተነሳው ሁሉንም ዓይነት ይዘት እንዲኖረው ተፈልጎ ነው፡፡ ከመዝናኛነት አንስቶ እስከ መረጃ መለዋወጫነት፣ ትምህርት ሰጪነት ድረስ እንዲሄድ ነው፡፡ጥቂትና የተወሰኑ አንባቢያን ብቻም ሳይሆን ሁሉም ሊያነበውና ሊሳተፍበት የሚችል ማድረግ ነው፡፡
ይህንንም ለማድረግ ጥረት በመደረግ ላይ ነው፡፡ በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ የሚያተኩር ሆኖ የገፁ እይታ እንዲጠብ አይፈለግም፡፡
መደብ
መልዕክት
Saturday, April 14, 2012
መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁንላችሁ፡፡
መደብ
መልዕክት
Tuesday, April 10, 2012
ጉዞ ወደ ‹‹ ዝቋላ አቦ ›› ልዩ የጉዞ ማስታወሻ 2 ??
‹‹ጉዞ ወደ . . . ዝቋላ አቦ ልዩ የጉዞ ማስታወሻ 1 ›› በሚል እየፃፍኩ የነበረውን የጉዞ ማስታወሻ አንብባችሁ ቀጣይ ክፍሉን በጉጉት ለምትጠብቁ አንባቢያን አንዲት መልዕክት ላስተላልፍ ፈለኩ፡፡
የአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክብረ በዓል እጅግ በጣም ማራኪና የአባታችን ተአምራት በዐይን የሚታይበት አስገራሚና ውብ
ክብረ በዓል ነው፡፡ የእውነትም ክርስቲያን መሆን በራሱ ኩራት የሚሆንበትና እምነትን የሚያፀና የበረከት ቦታ ነው፡፡ በተጨማሪ በዓሉን
ለማክበር ወደ ቦታው ሲኬድ ያለው ጉዞ እንዲሁ ድንቅ ሊባል የሚችል ነው፡፡ከሁለትና ሶስት ሠዓት በላይ የሚፈጀው ይህ ጉዞ የእምነት
ብርታት ጥንካሬ የሚለካበት ህብረቱ፣ሳቁ፣ ጨዋታው፣ መከባበሩ ድካሙ ሁሉም የሚታዩበት ነው፡፡ በዓለ ንግሱም ፍፁም መንፈሳዊና ውብ
ነው፡፡ መሳጭ ታሪክም አለው፡፡

ሁሌም የሚያስገርመኝ በቅዳሴ ሰዓት እርኩስ መንፈስ የተፀወታቸው (ያዛቸው) በሙሉ መሄጃና ማምለጫ ስለሌላቸው ዛፍ ላይ በመውጣት ነው እንደአውሬ የሚጮኹት፡፡
ወደ ጉዳዬ ስመጣ ይህንም ጉዞ ‹‹ ጉዞ ወደ. . . ዝቋላ አቦ- የጉዞ ማስታወሻ ›› በሚል ርዕስ ስለቦታው ቅዱስነት እንዲሁም
ስለ በዓሉ ይዘት በማስታወሻ መልክ ማቅረብ ጀምሬ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ክፍል አንዱ ላይ ያሰፈርኳቸው ግለሰቦችና አባቶች የጉዞ
ማስታወሻው ውበትና የ ታሪኩን ፍሰት የሚጠብቁልኝ ነበሩ፡፡ እዚህ ላይ እንድታውቁልኝ የምፈልገው ገዳሙ ውስጥ ያሉ አባቶችና እናቶችን
ለእናንተ ለማቅረብና ለማስተዋወቅ ያለኝን ፍላጎት ነው፡፡ ብዙ አስገራሚ ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡ ይህንን ነበር በጉዞ ማስታወሻዬ
ላይ ላቀርብላችሁ የነበረው፡፡ ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ታሪኩ ሲያልቅ ታሪካቸው ለህዝብ የሚወጣባቸው አባቶችና እናቶችን አሉ፡፡ ይህንን
የሚያውቁ ሠዎች ደግሞ ፅሁፉን ካነበቡ በኋላ በስልክም በአካልም አግኝተውኝ አውርተን ነበር፡፡ እርግጥ ነው ፅሑፉን ስጀምረው የሚመለከታቸውን
ጠይቄና አስፈቅጄ እንዲሁም ስለታሪኩ አቀራረብ አውርቼ ነበር፡፡

ሁሌም የሚያስገርመኝ በቅዳሴ ሰዓት እርኩስ መንፈስ የተፀወታቸው (ያዛቸው) በሙሉ መሄጃና ማምለጫ ስለሌላቸው ዛፍ ላይ በመውጣት ነው እንደአውሬ የሚጮኹት፡፡
Sunday, March 25, 2012
ክቡር ‹‹ ቤተ ክህነት ›› በግጥም
ቤ
|
ቤታችን ማረፊያ ሆኖ መጠጊያችን፣
ሀያት ቤቶች ልማት ማንም ሳይሰራልን፡፡
ዝማሬ መላዕክት ውዳሴ ቅዳሴው፣
የመቅደሱ ሽታ ዕጣኑ ከከርቤው ፣
ከህሊና ጓዳ ፍፁም የማይጠፋው፣
ፍቅር የሞላበት በረከተ አበው፡፡
የአቡነ አረጋዊ የአባ ሳሙኤል፣
ታሪክ ተፈፅሞ ተሰርቶበት ገድል፡፡
ሀያት ቤቶች ልማት ማንም ሳይሰራልን፡፡
ዝማሬ መላዕክት ውዳሴ ቅዳሴው፣
የመቅደሱ ሽታ ዕጣኑ ከከርቤው ፣
ከህሊና ጓዳ ፍፁም የማይጠፋው፣
ፍቅር የሞላበት በረከተ አበው፡፡
የአቡነ አረጋዊ የአባ ሳሙኤል፣
ታሪክ ተፈፅሞ ተሰርቶበት ገድል፡፡
ተ
|
ተከቦ በእሳት
የአባቶች ክብር እዚያና እዚህ ወድቆ፣
በክቡሩ ህሊና መንፈሳዊነት ርቆ፡፡
እነሱ ሳይደሙ ሳይቆስል ገላቸው. . .
ክብራቸውን ይዘው ቆመው ሳይፀልዩ አንዲት ሳይፈይዱ፣
ለምዕመን ሊመክሩ አንዳች ሊፈይዱ፡፡
በክቡሩ ህሊና መንፈሳዊነት ርቆ፡፡
እነሱ ሳይደሙ ሳይቆስል ገላቸው. . .
ክብራቸውን ይዘው ቆመው ሳይፀልዩ አንዲት ሳይፈይዱ፣
ለምዕመን ሊመክሩ አንዳች ሊፈይዱ፡፡
ክ
|
ክርስቲያን ነን
ብለው… ካህናት ተብለው፣
ይሰበሠባሉ ቤተ ክህነት ብለው፡፡
አረ ማን ባላቸው . . .ማን ባሳወቃቸው፣
ቤታቸው የክህነት ስራቸው ክህደት እንደሆነባቸው፡፡
ይሰበሠባሉ ቤተ ክህነት ብለው፡፡
አረ ማን ባላቸው . . .ማን ባሳወቃቸው፣
ቤታቸው የክህነት ስራቸው ክህደት እንደሆነባቸው፡፡
Thursday, March 22, 2012
ውሀ ያስፈልጋቸዋል!!
ይህች ሳምንት በኢ.ኦ.ተ.ቤ. ታሪክ ታልቅ ታሪክ የተሰራበት፤ ምን ያህልም እምነታችንን፣ ሀይማኖታችንን፣ ታሪካችንን እንደምንወድ እንደምናከብር እንዲሁም ህይወታችንን አሳልፈን ለመስጠት እንደማንሳሳ የታየበት ወቅት ነው፡፡ መከራ ይምጣ ባይባልም፤ ችግር ይፈትነን ባይባልም በአንድም በሌላ መንገድ ሊያስተምረን፣ ሊያስጠነቅቀን፣ ምን ያህል ለእምነታችን እንደምንቆም መፈተኛም ሊሆን ይችላል፡፡ የነበረውን ህብረታችንን እንውደደው፤ ከበረታንም አንድ የምንሆንበትን ሁኔታ እናመቻች፡፡ እርግጥ ነው አንድ ነን፤ይህም በዚህ ታሪካዊ ሳምንት መታየት ችሏል፡፡
ይኸው ቀናቶች ገፉ የዝቋላ ደንም እፎይ ማለት ጀምሯል፡፡ ሰላማዊ አየርም ይነፍስ ጀምሯል እናቶቻችን አባቶቻንን መረጋጋት ጀምረዋል፡፡ ይህ ስሜት አዲስ አበባም ፣ ባህር ዳርም፤ ናዝሪትም በሁሉም ቦታዎች በትንሹም ቢሆን እየመጣ ነው፡፡ እርግጥ ነው በገዳሙ ስራ ተጀመረ እንጂ ገና አላለቀም፡፡ አሁንም ብዙ ሰዎች አካባቢውን ማየት ወደ ቦታውም መሄድ ይሻሉ፤ ማድረግ ያለባቸውንም ለማድረግ አቆብቁበዋል፡፡ በወቅቱ ወደ ቦታው የተመመው ህዝብም ተልዕኮውን ፈፅሞ ቀጣዩን ስራ ደግሞ ለሚቀጥለው ተተኪ ትቶ መመለስ ጀምሯል፡፡ እንኳን ደህና መጣችሁ እላለሁ ነገር ግን አሁንም አካባቢው ላይ ያሉ ታላላቅ አባቶቻችንና እናቶቻችን ለደረሰባቸው ድንጋጤና መረበሽ አይዟችሁ የሚላቸው ያስፈልጋል፡፡ አሁን እየታየ ያለው ሁሉም እራሱን ለማረጋጋት ሲሞክር ነው፡፡ ይህ መልካም ነው እግዚአብሄር ያበርታችሁ ብያለሁ፡፡ እንደተነገረኝ በዚህ ወቅት ችግር እየሆን ያለው በቂ የሆነ የሚጠጣ ውሀ ማጣት ነው፡፡ ቦታው ላይ ያሉ አባቶች እንዳሉት ሁሉም ነገር እየተረጋጋ ቢሆንም አሁን ወደ ቦታው ለሚሄዱ ሠዎችም እንዲተላለፍ የፈለጉት በተቻለ አቅም የውሀ አቅርቦት ከፍ እንዲልላቸው ነው፡፡ ውሀ ያስፈልጋቸዋል!! ስለሆነም አይደለም ዉሀ ሌላም ቢታዘዝ ወደኋላ የማይለው ምዕመን ይህንን ችግር አይቶ አስቸኳይ ምላሽ ይሰጥ ዘንድ በትዕትና እጠይቃለሁ፡፡
በመጨረሻ በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ ወደ ዝቋላ በመሄድ እርዳታችሁን ልታደርጉ የተዘጋጃችሁ ካላችሁ በ 0922-123458 ደውሉልኝና መረጃውን ለህዝብ እናሳውቅ ፡፡

Subscribe to:
Posts (Atom)