ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡
Showing posts with label እንተዋወቅ. Show all posts
Showing posts with label እንተዋወቅ. Show all posts

Monday, February 20, 2012

ስብሐት ( ስብሐት ለአብ ) ገብረ እግዚአብሔር

Read in PDF
    በ1928 ዓ.ም በትግራይ ጠቅላይ ግዛት፣ አድዋ አውራጃ፣ እርባ ገረድ በተባለች መንደር ከአባቱ ከቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከወይዘሮ መአዛ ወልደ መድኅን ተወለደ። ትምህርቱን በስዊድን ሚሲዮን፣ እንዲሁም በ1952 በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከታትሎ በትምህርት አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል። 1953 ደግሞ በቤተ መጽሃፍት ሳይንስ ትምህርቱን ሊከታተል ወደ አሜሪካ ተጉዞ ሳይጨርስ ተመልሷል።
በአስፋ ወሰን ትምህርት ቤት በእንግሊዝኛ መምህርነት ለ2 ዓመት አገልግሏል። በመቀጠልም ከየተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፤ ሳየንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ባገኘው የትምህርት እድል አማካይነት ወደፈረንሳይ (ኤክስ አን ፕሮቫንስ) በመሄድ ከ1962-1964 ቆይቷል። የሄደበትን ትምህርት አጠናቆ ምስክር ወረቀት ባይቀበልም ቆይታው ከአውሮፓ ባህል እና ስነ-ጽሁፍ እንዲተዋወቅ በጣም እንደረዳው ይናገራል። ወደ ፈረንሳይኛ «Les Nuits d'Addis-Abeba» ተብሎ በፍራንሲስ ፋልሴቶ የተተረጎመውን የልብ-ወለድ ድርስቱን «ሌቱም አይነጋልኝ»ን ብዙውን ለመጻፍ የበቃው እዚያው በፈረንሳይ እንደሆነም ይናገራል። ይኸው ድርሰቱም ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ የተተረጎመ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ልብ-ወለድ ነው።

ሌቱም
አይነጋልኝ በውቤ በረሃ በ1957 ዓ.ም. ተጀምሮ

Tuesday, August 2, 2011

እንተዋወቅ

እንተዋወቅ
በዚህ ዓምድ ሠዎች ሊያውቋቸው ይገባል የምላቸውን ግለሠቦች ማለትም አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ዓለም ላይ የራሳቸውን ታሪክ የሠሩትን ታዋቂ ሰዎች ከውልደታቸው ጀምሮ አሁን እስካሉበት ደረጃ ለአንባቢያን የሚቀርብበት ነው፡፡

በዚህ ብሎግ ላይ ሲለሚወጡ ጽሁፎች አጭር ማብራሪያ፡-



መልዕክት
ይህ ክፍል ዋና አዘጋጁ (ብስራት ገብሬ) ያለውን እና የሚሰማውን ሃሳብ በዋነኛነት የሚያስተላልፍበት እና አንባቢያን ሊረዱት ወይም ሊያውቁት ይገባል ብሎ የሚያስበውን ሃሳብ በመልዕክት መልክ የሚያስተላልፍበት መድረክ ነው፡፡ ይህ መድረክን  ማንኛውንም የአንባብያን ጥያቄ መልስ ከአዘጋጁ የሚመለስበት የአቋም እንዲሁም የእይታ ማንጸባረቂያ ነው፡፡

እንተዋወቅ
በዚህ ዓምድ ሠዎች ሊያውቋቸው ይገባል የምላቸውን ግለሠቦች ማለትም አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ዓለም ላይ የራሳቸውን ታሪክ የሠሩትን ታዋቂ ሰዎች ከውልደታቸው ጀምሮ አሁን እስካሉበት ደረጃ ለአንባቢያን የሚቀርብበት ነው፡፡

እይታ