ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Tuesday, August 2, 2011

በዚህ ብሎግ ላይ ሲለሚወጡ ጽሁፎች አጭር ማብራሪያ፡-



መልዕክት
ይህ ክፍል ዋና አዘጋጁ (ብስራት ገብሬ) ያለውን እና የሚሰማውን ሃሳብ በዋነኛነት የሚያስተላልፍበት እና አንባቢያን ሊረዱት ወይም ሊያውቁት ይገባል ብሎ የሚያስበውን ሃሳብ በመልዕክት መልክ የሚያስተላልፍበት መድረክ ነው፡፡ ይህ መድረክን  ማንኛውንም የአንባብያን ጥያቄ መልስ ከአዘጋጁ የሚመለስበት የአም እንዲሁም የእይታ ማንጸባረቂያ ነው፡፡

እንተዋወቅ
በዚህ ዓምድ ሠዎች ሊያውቸው ይገባል የምላቸውን ግለሠቦች ማለትም አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ዓለም ላይ የራሳቸውን ታሪክ የሠሩትን ታዋቂ ሰዎች ከውልደታቸው ጀምሮ አሁን እስካሉበት ደረጃ ለአንባቢያን የሚቀርብበት ነው፡፡

እይታ
ይህ ክፍል በዋነኛነት … ይህ ሆነ፣ ይህ ቢሆን ኖሮ ፣ለምን ይህ አልሆነም ተብሎ በአንድ ጉዳይ ላይ በእይታ ዓይን ቁም ነገር ለማስተላለፍ የሚሞከርበት መድረክ ነው፡፡ማንኛውም ሠው እንዲህ ቢሆን ሊልበት የሚችልበት የእይታ/የትዝብት ጥግ ነው፡፡

ኪነ-ህይወት
በዚህ መደብ በሀገራችንም ሆነ በሌላው ዓለም እየተካሄደ ያሉ ማንኛውንም ዓይነት የመዝናኛ ዜናዎች እና ኪናዊ ሃሳቦች የሚቀርቡበት ይሆናል፡፡ መታየት ያለባቸው ፊልሞች፣መሰማት ያለባቸው ዘፈኖች፣መነበብ ያለባቸው መጽህፍት፤ ሁሉም ይፈተሻሉ፡፡ በተጨማሪ በሀገራችን የሚደረጉትን የመዝናኛ እንቅስቃሴዎችን ለአንባቢያን ለማቅረብ ይህ ዓምድ ትኩረት ይሠጣል፡፡

አስጎብኚው
የአንድ ሀገር፣ከተማ፣መንደር፣ መነሻና ታሪክና ቅርስ፣ባህልና ትውፊት፣ወግና ስርዓት የሚዳሠስበት መድረክ ነው፡፡ በ<ብስራት እይታ> መጎብኘት አለባቸው የሚባሉትን ሥፍራዎች በሙሉ በተጠናከረ መንገድ በማቅረብ አንባቢው ከተቻለ በመሄድ ካልሆነም በቂ የሆነ መረጃ እንዲኖረው በማድረግ ጉብኝትዎን ሙሉ ማድረግ ነው፡፡

ስፖርት
ይህ አምድ ለስፖርት ወዳዱ ክፍል ስፖርታዊ መረጃዎችን የሚቀርቡበት ሲሆን በሀገራችንም ሆነ በዉጭ ባሉ ብሄራዊ ቡድኖችና ክለቦች መሰረተ ታሪክ እንዲሁም እንደ አስፈላጊነቱ በስፖርቱ ዓለም የራሣቸውን አሻራ ያስቀመጡ ስፖርታኞች/ግለሰቦች የሚተዋወቁበት ሜዳ ነው፡፡ይህ ማለት እግር ኳስ ብቻ ሣይሆን አትሌቲክስ፣ ቦክስ፣ ሞተር- ሣይክል ሁሉም የሚስተናገዱበት ይሆናል፡፡

ለአንባቢያን
በዚህ ክፍል በሀገራችንም ሆነ በውጪው ዓለም እየተነበቡ እንዲሁም ሊነበቡ የሚገነቡ መጽሐፍት ለመረጃ ያህል ያህል እና በዝርዝር የሚቀርቡበት  ነው፡፡ አዳዲስ  ወደ ገበያ የሚወጡትንም ለማስተዋወቅ ያሞክራል፤ይጥራል፡፡   

1 comment:

  1. ሰላም ለአዘጋጁ ብስራት በመጀመሪያ ሀሳብህን እደግፈዋለው ማንም ሰው ባለው አቅም ሀሳብ እና መረጃን ሲለዋወጥ ጥሩ ነው። እናም የእኔ ሀሳብ ግን በዌብ ላይ ስህተትን ሰርተሀል ይህም የምታወጣተቸው ጽሁፎች ሀይማኖታዊ ትምህርት የሚያስረዱ ሲሆን በዚህ በተጓዳኝ ደግሞ ዘና ብለው ያንብቡ ብለህ አለማዊ ሙዚቃን አስገብተሀል ይህ ደግሞ ከቤ/ያናችን ትምህርትና እምነት ውጪ ነው። ስለዚህ ሀሳብህ ሀይማኖታዊ መልዕክቶችን ለመለዋወጥ ከሆነ ሙዚቃውን አስወግደህ መዝሙር ማድረግ ይኖርብሀል።
    ለነበረን ጊዜ ሁሉ ቸርነቱ የማያልቅበት አምላክ የተመሰገነ ይሁን
    ወስብአት ለእግዚአብሄር

    ReplyDelete