ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Thursday, September 11, 2014

መልካም ምኞት ለ አዲስ ዓመት

እንኳን አደረሳችሁ፡፡ መጪው ዘመን የደስታ ፣ የሠላም ፣ የፍቅር የጤና ፣ የብልጽግና ፣ በረከት የሞላበት ፣ ህፃናት ቦርቀው ተጫውተው የሚያድጉበት፣ እናቶች እና አባቶች የሚከበሩበት፤ የሚደመጡበት ፣ ያለ ፍርድ በየእስር ቤቱ ተወርውረው የሚገኙት ወንድም እና እህቶቼ እውነተኛ ፍርድ የሚያገኙበት ፣ ሀገሩን የሚወድ ፤ ለሀገሩ የሚቆም ትውልድ የሚነሳበት ፣ ኢትዮጵያዊነት ኩራት የሚሆንበት ፣ ባህላችን፤ ትውፊታችን ወጋችን ፣ ስርዓታችን ሳይጠፋ ይበልጥ የሚዳብርበት ፣ በውጭ ሀገር ያሉ ኢትዮጵያውያን ወደእናት ምድራቸው የሚመለሡበት አስደሳች ዘመን ያድርግልን። በየመንገዱ ወድቀው የሚገኙ ወገኖች አይዟችሁ አለንላችሁ ባይ የሚያገኙበት ፣ የህመም በስቃይ የሚገኙ የሚፈወሱበት ፣ ቅዬው መንደሩ ሠፈር ሀገሩ ሠላም የሚሆንበት ዓመት ይሁንልን ።

ከሁሉ በላይ ግን ከጠፋንበት ተመልሰን በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እቅፍ ውስጥ ሆነን እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት ፣ ከደጀ ሠላሙ የማንጠፋበት ፣ ጠፍተን ከቆየንም ወደ ቤቱ መልሶ ልጆቹ ፣ አገልጋዮቹ የምንሆንበት ፣ ተዓምረ እግዚአብሔር የማይጠፋበት የሚበዛበት ያደርግልን ዘንድ ልባዊ ምኞቴ ነው። አመቱን ሙሉ የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የመላዕክት ጥበቃ፣ የፃድቃን ሰማዕታት ፀሎትና ምልጃ ፣ የእመ አምላክ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ንፅሂተ ንፁሃን የሆነችው የቅደስት ድንግል ማርያም ፍቅር እና ሠላሟ ፣ ልመናዋ እና እናትነቷ አይለያ
ሁ። 

መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ።

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር

No comments:

Post a Comment