ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Thursday, July 14, 2011

እሹሩሩ... ለ"ተሐድሶ" ያስፈልጋልን?

በብስራት ገብሬ

ቀጥታ ወደቁምነገር:-

                      በመጀመሪያ የኢ.ኦ.ተ.ቤ.መጠበቅ የሁላችንም ኃላፊነት ነው::እግዚአብሔር ያውቃል...እኛ ምንም አንሆንም እያልን ስንት ወገኖቻችን ሄደዋል:: እኛ ግን በግራና በሞቀ ቤታችን ሆነን 'ይህን ካላየሁ አላምንም' ይህን ካልሰማሁ.... እንላለን:: ቤተክርስቲያናችን በአሁኑ ወቅት እንዲህ አይነት ፋታ የሚሠጥ ነገር ሣይሆን መሠረቷን በብዙ አቅጣጫዎች እንድታጣ ሆና በአራቱም አቅጣጫ ተወጥራለች:: የምትጠብቀው "..በሉ አሁን ጀምሩ የሚለውን.." የእግዚአብሔር ፊሽካ ሳይሆን በሚቆረቆሩላት በሚኖሩባት በሚያዝኑላት ልጆቿ ታግዛ አይምሬ ቅጣት ሊቀጧት ከተዘጋጁ ጠላቶቿ ጋር ፊት ፊት እንድንዋጋላት...እንድንጋፈጥላት ነው::እግዚአብሔርም ከእሱ ስርዓት ውጭ ካልሆንን ከጎኗ ይሆናል::

       እይታዬ:- ሁላችንም እምነታችንን እንወዳለን ነገርግን እምነታችንን የሚነካ የሚበርዝ የሚያጠፋ ነገር ሲነሳ ከውጪ ሆኖ "አይይ... ልቦና እግዚአብሔር ይስጣቸው..." ብሎ ከንፈር ከመምጠጥ ውጭ አንዳችም ነገር ስናደርግ አንታይም ይህም ነው ቤታችንን ጠላቶቿ እንዲዳፈሯት የሚያደርገው ጠላትን ለማጥፋት ማን ነው ሽጉጥና ጠመንጃ ብቻ መፍትዔ ያደረገው?? ለጠላት ሽጉጥም...ጠመንጃም... 'የበዛ' ትህትናም አያስፈልግም:: በቤተክርስቲያናችን ስርዓትና ወግ መሠረት አንድም እንዲማሩ ማድረግ ካልሆነም አርፈው እንዲቀመጡ ማድረግ/ማፅዳት እንጂ::ለዚህም ይረዳን ዘንድ


1ኛ.የጠላትን ውስጠ-መሠረት እና ማንነት ማወቅ



2ኛ.ዝም ብንል የሚያስከትለውን ጥፋትና እልቂት መገንዘብ


3ኛ.እኛ ያለንበትንና ጠላቶቻችን ያሉበትን ሁኔታና ደረጃ ለማወቅ መቻል እና እንዴት መከላከል እንዳለብን ማወቅ(በግልም በህብረትም)



4ኛ. ከተቻለ ዳግመኛ እንዳይመለሡ ለማድረግ መጣር::
እነዚህን ማድረግ ከቻልን ቤታችንን መጠበቅ የሚቻል ይሆናል በእኔ እይታ አሁን የኢ.ኦ.ተ.ቤ. የምትፈልገው ሁሉን ለማወቅና ተገቢውን እርምጃ ለመውሠድ ብቃቱም ኃይሉም ኖሮት ውስጡ ግን ተነሳሽነት የጎደለውን 'ፈሪ' አይደለም ! ፈሪ ማለት ለኔ ይሄ ነው! ሌላው ሲሞት የሚደራደረውን::ሃይማኖት... እምነት ሲጠፋ ቆሞ የሚያየውን::





             በአንድ ወቅት አንዱ የተሐድሶ አቀንቃኝ 'ስላሴ' አትበሉ 'እየሱስ' በሉ ብሏል ብዬ በመፃፌ "...ለምን ሙሉ ሲዲውን(CD) እንዲሁም ሙሉ ስብከቱን አንሠማም..." እህህ..."ነገርን ማባባስ ለምን?" ያስፈልጋል ተብያለሁ:: አውቃለሁ ምን ያህል የኢ.ኦ.ተ.ቤ. ልጆች ትህትና እንዳለን:: ልንኮራበትም ይገባል:: ይህም ቢሆን ትህትናው በሌሎች ፍርሃት መሠለ:: ዋጋም አስከፈለን:: ትህትናችን ከመብዛቱ የተነሣ በቤታችን... በጓዳችን... በካፌ ውስጥ ቁጭ ብሎ ከማውራት ከመቆዘም ዝም ከማለት የተሻለ/የዘለለ ምንም አላደረግንም::


ዋናው ቁምነገር ግን እምነታችንን... ውበታችንን ሳናጣ ስለጠላቶቻችን ድርጊትና እንቅስቃሴ በግልፅ ማውራት ያለብን ይመስለኛል በግልፅም ወደመፍትዔ መሄድ አለብን::
....ነገር ማባባስ ነው ተብሎ ዝም ከማለት የሚመጣውን መቀበል በብዙ ይበልጣል::


*እየተባለ ያለው ቤታችንን ስለመጠበቅ ነው!


*እየተባለ ያለው እምነታችንን ስለመጠበቅ ነው!


*እየተባለ ያለው እውነትን ስለመጠበቅ ነው!


ሁላችንም የሚሆነውንና እየተካሄደ ያለውን ነገር በትኩረትና በአንክሮ የመከታተል የመረዳት ግዴታ አለብን:: ማንም ጊዜ ኖሮት ስለጠላት ለማውራትና ጭቅጭቅ ለመፍጠር የሚፈልግ ያለ አይመስለኝም:: ችግር ከሌለበት በስተቀር::ማንም ለኔ ስለለኔ መረጃም ሆነ ማስረጃ ማቅረብ የለበትም:: እንደ ዕድል ይሁን እንዳጋጣሚ ብዙዎቻችን አስተያየት ሠጪና የሩቅ ተመልካች ሆነን ተፈጥረናል:: የሚያስቀው'ለማመን' እንኳን ጠላቶች ያደረጉትን ነገር ሁሉ/ሙሉውን መረጃ እቤታችን..ቢሯችን ድረስ እንዲመጣን እንፈልጋለን:: ለምን? የሚገርመው የመጣንን መረጃ እንኳን ግራና ቀኝ አይቶ መወሠን ካለመቻላችንም በላይ ለማጥላላት ስንሞክር እንታያለን:: በዚህ መሐል ደግሞ ለኢ.ኦ.ተ.ቤ. የተቆረቆሩ የሚመስሉ የበግ ለምድ የለበሱ የኛን ትንሿን ድክመት ጨምረው የተገኘውን መረጃ የማንቋሸሽ ስራ በስፋት ይሠራሉ:: የውስጣችንንም ኃይልና ብርታት ይገሉታል:ያዳክሙታል:: የተፈለገውም እንዳይሆን ይጥራሉ::


      በመጨረሻ ወዳጆቼ እርስ በራስ ከመተቻቸት ከመሸሽ አንድ ሆነን እግዚአብሔር እንዲረዳን ብርታቱን እንዲሠጠን እየለመንን በአንድ ድምፅ በመጮህ ጠላቶቻችንን ይብቃችሁ እንበላቸው ፊት አንስጣቸው::





እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን




አሜን



ይቀጥላል....


ብስራት ገብሬ
man.bisrat@yahoo.com
14 july 2o11

20 comments:

  1. Melikam iyita new !!

    ReplyDelete
  2. Egziabher yerdan. For the time being all of the EOTC followers who have the knowledge about Tehadesso must write and expose their work. It may start from your family, friends, and so on.
    Berta tiru eyeta new
    Yohannes Mengistu

    ReplyDelete
  3. This comment has been removed by a blog administrator.

    ReplyDelete
  4. Yes there is no more "ESHURURU" Please our Pops do what you have to do.

    ReplyDelete
  5. This comment has been removed by a blog administrator.

    ReplyDelete
  6. kale hiwot yasemalen. bisrat betam des yamil amelekaket new egziabeher yisteh.. beterefe ene emelew sebakiw hulum endet tehadiso yelem endemilu yigermegnal. cause i know someone who is diakon and he always go to our church but he pray in english that means in the way what protestant is praying so i was so shocked about him. and protestants had a strategy to diminish our church by preaching on road however they are now changed their way of diminishing our church like what begashaw or other tehadiso are doing... bisrat i appreciate your view because nobody has leak this issue so far you are i think the first who leak this issue on blog so pls if you contact others who has blog pls discuss with each other and let others put it on their blog.... thank you i wanted to tell more but i lack word to say... God be with you and i wish you all the best...

    ReplyDelete
  7. ewente mendenat? selase manew eyesuses man new ???today is my first day to read your blog so what do you think endate new betachenen(haymanotachenene) yementebekew yekomen yemeselen endanwodek entenkeke
    Amen!!!

    ReplyDelete
  8. ene enemimeslegn egzihabihe lehulachinim melkam libona yisten neger gin manachinim binihon kehatiat yesedan aydelenim endesu cherinet gin bedeju enigegnalen yehunina betekiristiyan gwebtew endayaskedisu yemekelkel mebt keegziabiher tesettonal wey beterefe silehulum neger egziabiher melkamun yadrig..............?

    ReplyDelete
  9. ይኸን የተሃድሶ ወሬ የምታራግቡ ሰዎች ለቤተክርስቲያኗና ለእምነታችሁ ተቆርቋሪ መስላችሁ ነገር ግን በውስጡ የምታራምዱት የራሳችሁን ገበያና ጥቅም እንደሆነ የገባው ይገባዋል፡፡ ከዚህ ሌላ ደግሞ በውስጣችሁ የነገሰው የምቀኝነትና የቅናት ስሜት አላስቀምጥ ብሏችሁ በወንድሞቻችሁና በእህቶቻችሁ ፀጋ እራሳችሁ ስለታመመ እረፍት አጥታችሁ ትለፈልፋላችሁ፡፡ ለመሆኑ እናንተ እነማን ናችሁና ነው ያለእኛ አዋቂና ክርስቲያን የለም እያላችሁ የምታደነቁሩን፡፡ እውነተኛ ክርስቲያን ብትሆኑማ ኖሮ የተሳሳቱ ቢኖሩ እንኳን እንዲህ የማርያም ጠላት ከማድረግ ይልቅ ቀርባችሁ በማስተማርና በመወያየት ነገሩን ታስተካክሉ ነበር ወይም ለማስተካከል ትሞክሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ሁላችሁም የሚበልጣችሁ ሲመጣባችሁና ገበያችሁን የሚያቀዘቅዝባችሁ ሲነሳ የየራሳችሁን ውጣዊ ስሜት ጭምብል በማልበስ በቤተክርስቲያን ተቆርቋሪነት ስም አድማ ትቀሰቅሳላችሁ፡፡ እስቲ አንዳችሁ እንኳን የተሻለ ሃሳብ በማቅረብ የተሳሳቱ የሚመለሱበትን፣ ያላወቁ የሚማሩበትን፣ የተጣሉ ታርቀው በእውነተኛ ስሜት ቤተክርስቲያናቸውን የሚያገለግሉበትንና አንድነት የሚፈጠርበትን መልካም ነገር ስበኩ!! እባካችሁ የግል ጥቅሜ ተነካ ዓይነት ጩኸት አቁሙ!!!!

    ReplyDelete
  10. hulunem legeta metewe new lhulachenem lebe yeseten

    ReplyDelete
  11. Aykomeme never until tehadeso stops. We know that U...pente's are trying to destroy our church...never happen...kedusanen yemineku....keresetosn akeberen bilu wori new...enatun gentelew lejun yazen bilu wori new...it will never stops....egna be penti ankenam...kentenem anawekem gen we can challenge them....beafu mulu yemisadeb asetemarim keseyetan new.....azawenten yemiregem....lebete christin bizu sira yeseruten yemokonen....sijemer regeman kekerestos aydelem..yeregeman abat diablos new...we never stops whatever U say eshi

    ReplyDelete
  12. SILASE ATEBELU EYESUS BELU YALEBE MEKNYATEN ABRARTOLENAL ESU LE MALET YE FELEGEW SILE MISTERE
    SELASE NEW ABE WELD MENFESKIDUS YEMILEWEN.
    EX MANEW BEMESKEL LAYE YE TESEKELEW ?
    A EYESUS
    B SILASE THE ANSWER IS A.
    PLEASE WE HAVE TO BE CARE FUIL BY SAYING TEHADESO
    BECUSE THE REAL TEHADESOWEYAN THE ARE TAKING ADVANTEGE FROM THIS KIND OF SITUATION. I'M SURE YOU KNOW WAHAT IM TRYING TO SAY .YES WE HAVE TO WACH THOSE REAL TEHADESOAWYAN BUT ...WE SHOUD STOP CALLING PEOPLES TEHADESO WITH OUT FUILL EVIDENCE.
    GOD BLESS OUR CURCH.
    KALEB FORM MARYLAND

    ReplyDelete
  13. እውነቱን እስኪረዱት ድረስ ስለተሀድሶ መኖር የሚቃወሙ ሁሉ ተረጋግተውና ከስሜት ወጥተው ሊያስተውሉ ይገባቸዋል! ተሀድሶ እውነትነው ወደድንም ጠላንም ቤተክርስቲያናችንን ለማፍረስ በተደራጀ ሁኔታ እየሰራ ነው እስኪ በኦርቶዶክሳዊት ሚዛን ሁሉንም እንመዝን!ይህንን የምለው ተሀድሶ የለም በማለት ለተሀድሶ መስፋፋት እያወቁም ሆነ ሳያውቁ እድል እየሰጡ በመሆኑ ነው ስለዚህ ግለሰባዊ ቅናት ምቀኝነትና ሌላም ስጋዊ ሥራ የወለደው አይደለም!!! እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች ከሆንን እናስተውል!

    ReplyDelete
  14. Way cool! Some extremely valid points! I appreciate you
    penning this article plus the rest of the site is also really good.
    Here is my web blog ... cool articles for teenagers

    ReplyDelete
  15. I was wondering if you ever considered changing the layout of your blog?
    Its very well written; I love what youve got to say.
    But maybe you could a little more in the way of content so people could connect with it better.
    Youve got an awful lot of text for only having one or two
    images. Maybe you could space it out better?
    Feel free to visit my blog - my article tools

    ReplyDelete
  16. ''This comment has been removed by a blog administrator.'' why it is for? you should explain about this.i oppose the ''TEHADSO''s mov't but is that right to say them enemy(telat) i fell discomfort about this word.our ideas must pave the way for unity with love. the rest things are GREAT!

    ReplyDelete
  17. ''This comment has been removed by a blog administrator.'' why it is for? you should explain about this.i oppose the ''TEHADSO''s mov't but is that right to say them enemy(telat) i fell discomfort about this word.our ideas must pave the way for unity with love. the rest things are GREAT!

    ReplyDelete