|
ዋና አዘጋጅ
ብስራት ገብሬ |
በመጀመሪያ ይህንን ዌብ-ብሎግ(Web-Blog) ስሰራ እንደ ዓላማ አድርጌ የተነሣሁት ውስጤ ያለውን የመረጃ መለዋወጥና ማግኘት ፍላጎት ከግብ ለማድረስ ነው:: ከዚህ ቀደም
Bisrat Ge የሚል 'ፌስ-ቡክ' (Facebook) ና
Bisrat Gebre የሚል 'ትዊተር' (Twitter) አካውንት ከፍቼ እጅግ ብዙ ቁጥር ካላቸው ግለሠቦችና ተ
ቋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር መረጃዎችን ለመለዋወጥ ያስቻለኝ ሲሆን እጅግ ብዙ ወዳጆችም እንዲኖሩኝ ሆኗል:: ያም ቢሆን የጊዜው ማነስና የፈለኩትን ያህል መረጃዎችን በአንድ ጊዜ በራሴ 'እይታ' ለማስተላለፍ ያለኝን ውስጣዊ ፍላጐት እንዳሣካ በቂ ሆኖ አላገኘሁትም::
ይህም ደስተኛ ሊያደርገኝ አልቻለም:: በዚህ ምክንያት ይህን 'የብስራት እይታ Bisrat Gebre's View" ዌብ-ብሎግ (Web-Blog) እንድሠራና እንድፈጥር ሆንኩ::
የሚገርመው እጅግ አድካሚ በሆነ መንገድ 80% የሚሆነውን ክፍል የሠራሁት በምስኪኗ 'Nokia 2700' ሞባይሌ ነው:: የተቀረውን በአካባቢዬ ባሉ የ 'Internet Cafe' ውስጥ ለረጅም ሰዓት ተቀምጬ ሲሆን ወጪው በራሱ ለአንድ የቀን ገቢ ለሌለው ለእንደኔ ዓይነት ከባድ ነበር::
እዚ'ች ጋር ሌላ ልናገር የምፈልገው አንድም የ 'IT' ወይም የ' Software' አጠቃቀም ትምህርት የሌለኝ መሆኑን ነው:: ሁሉም በፍላጐትና በማንበብ ነው::
ያም ቢሆን ይኸው 'እግዚአብሔር' ይመስገን በመጨረሻ ጨረስኩት::
የሚሻሻልና የሚበረታታ ነገር ካገኛችሁ አስተያየታችሁን ንገሩኝ ላኩልኝ::
ብስራት ገብሬ
May 5,2011