ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Wednesday, May 25, 2022

ኦርቶዶክሳዊነት እና የሰይጣን መንግስት

 ላለፉት ዓመታት ማህበራዊ ገጾችን በተለይ ፌስቡክን ለምፈልገው ዓላማና ግብ ስጠቀምበት ነበር። ይሁንና ከጥቂት ዓመታት ጀምሮ ግን "እያስጠላኝ" በመምጣቱ ምክንያት እንደከዚህ ቀደሙ እይታዬን ፣ ፍላጎቴን ፣ ልምዴን ለማካፈል የነበረኝ ተነሳሽነት እየቀነሰ መጥቷል። በዚህም የፌስቡክ ጥቅም ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ምን እንደሆነ እየጠፋኝ እና እየዘነጋሁት መምጣት ጀምሯል።

ይኼ ሁኔታ ልክ ይሁን ልክ አይሁን አሁን ላይ ማሰብ ባልፈልግም እንደዛሬው አይነት ጉዳይ ሲገጥመኝ ግን እንደሁኔታዎች እራሴን መፈተሽ እንዳለብኝ ተሰምቶኛል።

ከአንድ ወዳጄ ጋ ሻይ ቡና እያልን ስለሀገራችን አኹናዊ ሁኔታ ስንጫወት በመሐል ኦርቶዶክሳዊነት እና ብልጽግና ስለሚባለው  ኮተት መዋቅር አንስተን መጫወት ጀመርን። ጥሩ ጥሩ ሃሳቦችን አንሸራሸርን። አድምቀን አድምተን ተወያየን።

በመሐል 

" ብስሬ የመምህር ፋንታሁን ዋቄን አዲሱን መጽሐፍ ገዝተህ አንብበው ፤ ምን ያህል ኦርቶዶክሳዊነትን ለማጥፋት እየሰሩ እንዳለ ግንዛቤ ይሰጣል " አለኝ።

ለጥሩ ውይይት ትክክለኛ ግብዣ ብዬ መጽሐፉን ማንበቤን ልነግረው አልኩና ስለመጽሐፉ የተሰማውን በዝርዝር እንዲያወራ ስለፈለኩ ተውኩት። 

መጽሐፉ፦

"ኦርቶዶክሳዊነት እና የሰይጣን መንግስት " የተሰኘ ርዕስ አለው። ውርስ ትርጉም ነው። መምህር ፋንታሁን ዋቄ ደግሞ በጥሩ ሁኔታ አዘጋጅቶና ተርጉሞ ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን በኃላፊነት መንፈስ አዘጋጅቶ አቅርቦልናል።

ግን ግን ስንቶቻችሁ አንብባችሁታል?

ካላነበባችሁት ዳይ አሁኑኑ መጽሐፉን ግዙና አንብቡት።

ትዕዛዝ ነው!!

ያው እኔ የምመርጥላችሁን ደግሞ ታውቁም የለ፦  የሚጠቅማችሁን ነው።

ምነው ብስራት ማስታወቂያ አስመሰለብህ ብትሉኝ ደግሞ መልሴ... አዎ በሶስት ምክንያቶች ማስታወቂያ ሊሆን ይችላል እላለሁ።

☝️የመጀመሪያው

ኦርዶክሳዊነቴ እና በእምነቴ ዙሪያ ያንዣበበውን አደጋ ለተቀረው አማኝ ማሳወቅ እና ማስተማር እንዴት ብሎም እምነቱንም ሀገሩንም እራሱንም መጠበቅ እንዳለበት ግንዛቤ እንዲወስድ ስለምፈልግ ነው። 

☝️ሁለተኛው ምክንያቴ ደግሞ የመጽሐፉን የሽፋን ስዕን ዲዛይን በመስራት የተሳተፍኩ መሆኔ የልብ ልብ ሰጥቶኝ ነው። ይሄ ምክንያቴ ለመጽሐፉ ማስታወቂያነት አንተን ወይም አንቺን ለማነሳሳት ብዙም ባይጠቅምም ድንገት ግን እንደተጨማሪ ማነሳሻ መጽሐፉን ለመግዛትና ለማንበብ ፍላጎት ካሳደረባችሁ ብዬ ነው።

☝️ሶስተኛው ኦርቶዶክስ ሆኖ ሀገሩንም የሚወድ ነገር ግን የተዘናጋም የተኛም ያንቀላፋም ካለ ለመቀስቀስና እራሱንና ቤተክርስቲያኑን ሀገሩን መጠበቅ እንዳለበት እንዲያስብ ለማድረግ ነው።

እሹሩሩ አልኳችሁ አይደል?

በሉ አሁኑኑ ፈልጉና ግዙት። ኦርቶዶክሳዊ ከሆናችሁ ለራሳችሁም ለቀጣዩም ትውልዳችሁ ለልጅ ልጆቻችሁ ማሰብ ግዴታችሁ ነው። በተጨማሪም ለወዳጅ ዘመድ አካፍሉት። ለታሪክ አስቀምጡት።

ወደመነሻዬ ስመጣ ፌስቡክን በመጥላቴ ለህትመት ከበቃ ወራትን  ያስቆጠረውን ይህን መጽሐፍ ሳላስተዋውቃችሁ ሳልጋብዛችሁ በመቅረቴ ይቅርታ እየጠየኩኝ መጽሐፉን በተመለከተ በተለያየ መንገድ (Share , Like , comment) ለምታስተዋወቁ አስር (10) ወዳጆቼ መጽሐፉን ገዝቼ እንደምሸልማችሁ መግለጽ እወዳለሁ።



No comments:

Post a Comment