ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Sunday, November 13, 2011

መዝሙርና ዘማርያን. . .

  • እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ከሰጠው ታላቅ ጸጋ መካከል የመዝሙር አገልግልት አንዱ ነው፡፡
  • በቤተክርስቲያን ትምህርት ለቅዱሳን ከሚሰጡ አስሩ ማዕረጋት ሶስተኛው ጣዕመ ዝማሬ ይባላል
           የመዝሙር በአጋጣሚ የተጀመረ ሳይሆን ከአምላክ የተሠጠ የአገልግሎት ፀጋ ነው፡፡ የሠው ልጅ መዝሙርን የተማረው የተማረው ከመላዕክት ነው፡፡ የመላዕክት እንጀራ ምስጋናቸው ነው፡፡ “የመላዕክትን እንጀራ የሠው ልጅ በላ” ተብሎ ተፅፏል፡፡ይህ ማለት መላዕክት የሚበሉት እንጀራ የሚጠጡት መጠጥ አላቸው ሳይሆን የሠው ልጅ የቅዱሳን መላዕክትን ምስጋና ለማመስገን መፈጠሩን ማስረጃ ነው፡፡ቅዱሳን መላዕክት ለፈጣሪያቸው የሚቀርቡት ምስጋና ምግብ ሆኖአቸው ያለማቋረጥ ሲያመሰግኑ ይኖራሉ፡፡
ህዝበ እስራኤል ከምድረ ግብፅ ከባርነት ነፃ ለመውጣት ባህረ ኤርትራን በደረቅ በሚሻገሩ ጊዜ ይከተላቸው የነበረው ፈርኦንና ሠራዊቱ በፈረሶቻቸው ላይ እንዳሉ ባህረ ኤርትራ ተከድኖባቸው በሚጠፉ ግዜ ይህን ያየችው ማርያም እኅተ ሙሴ ከህዝቡ ጋር ከበሮ ይዛ በህብረት “. . .በክብር ከፍ ከፍ ብለሃልና ለእግዚአብሔር እንዘምራለን. . . ” በማለት ለፈጣሪያቸው የአንድነት ዝማሬ አቅርበዋል፡፡ ዘፀ.
፲፭፣፩-፳፩ ሊቀ ነቢያት ሙሴም ለእስራኤል ልጆች በተለያየ ጊዜያት መዝሙር ያስተምራቸው ነበር፡፡
በእስራኤል  ላይ ስትፈርድ የነበረችው ነብይቱ ዲቦራ “. . .እኔ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔርም እዘምራለሁ . . . ” በማለት የዘመረችው መዝሙር ማህሌተ ዲቦራ በመባል ይታወቃል፡፡ መሳ.፭፤፩-፴፩ ቅዱስ ዳዊትም በእሰራኤላውያን ዘንድ ከጥንት ጀምሮ የነበረውን የመዝሙር ሥርዓት ወስኖ ሁለት መቶ ሰማንያ መዘመራንን መድቦ መዝሙሩን በተለያየ ግዜ ከፈፍሎ እንዲዘምር ከማድረጉም በተጨማሪ እራሱም በገና እየደረደረ በቤተ መቅደስ ያገለግል ነበር፡፡ የነብዩ ዳዊት ልጅ ሠለሞንም ከመዝሙራት ሁላ የሚበልጥ መዝሙር “መኃልየ መኃልየ ዘሰለሞን” የተባለውን ዝማሬ ይዘምር ነበር፡፡
የዘማሪ ይልማ ኃይሉ የመዝሙር ካሴት ሽፋን
በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን የሱስ ክርስቶስ በቤተልሄም ተወልዶ ባዩት ጊዜ ተለያይተው የነበሩ ሰውና መላእክት በአንድነት ዘምረዋል፡፡መዝሙር በዕለተ ሆሳዕና የቢታንያን ድንጋዮች ያዘለለ፤ጡት የሚጠቡ ህጻናትን ሳይቀር ለምስጋን ያነሳሳ ታላቅ የአገልግሎት ጸጋ ነው፡፡ቅዱሳን ሐዋርያትም ሐሙስ ማታ በአላዓዛር ቤትቅደስ ቁርባንን ከተቀበለ በኋላ በአንድነት ዘምረዋል፡፡ማቴ ፳፮፤ ፡፡ በቤተክርስቲያን ትምህርት ቅዱሳን ከሚሰ አስሩ ማዕረጋት ሶስተኛው ጣዕመ ዝማሬ ይባላል፡፡ከጣዕመ ዝማሬ ማዓረግ የደረሱ አበው ሳያቋርጡ ሳይሰለቹ ለፈጣሪያቸው ምስጋና ያቀርባሉ፡
         
መዝሙር የሚለው ቃልዘመረአመሰገነ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም ምስጋና ማለት ነው።መዝሙር በቤተ ክርስቲያን የዝማሬ ሥርዓት መሠረት በዜማ የሚቀርብ ምስጋና ነው፡፡ ምስጋና የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ እግዚአብሔር ክብሩ በባሕሪው ብቻ እንዲይቀር ስሙን እንዲቀድሱ ክብሩን እንዲወርሱ መላእክትንና ሰውን አስተዋይና አዋቂ አድርጎ ፈጥሮአቸዋል ፡፡ከቅዱሳን መላዕክት ወገን የነበረው ሳጥናኤል ያልተሰጠውን አምላክነት በመሻቱና ምስጋና እንዲቀርብለት በመፈለጉ ከክብሩ ተዋርዷል። ሕዝ.፳፰፡፲፫ በእርሱም ፈንታ እግዚአብሔርን የሚያመሰግን እጅግ ያማረና የከበረ ሰው ተፈጥሮአል። መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ ፪፡፲፪ "እንዳንተ ካለ ሠራዊተ መላእክት ሁላ ይልቅ ራስህን አኩርተሃልና ስለ ትዕቢትህ እግዚአብሔር ከናቃቸው ከሰራዊቶችህ ጋር አንተ ስለምታመሰግነው ምስጋና የእግዚአብሔርን ምስጋና ያመሰግኑ ዘንድ አዳምን ከልጆቹ ጋራ ፈጠረውበማለት የሰው ልጅ የተፈጠረበትን ዓቢይ አላማ ይገልጻል፡፡ ቅዱስ ዳዊትምእግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፤ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው፡፡በማለት የሰው ልጅ ያለማቋረጥና መሰልቸት ፈጣሪውን ማመስገን እንደሚገባው ተናግሯል፡፡መዝ ፴፫፤፩ ፡፡እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ከሰጠው ታላቅ ጸጋ መካከል የመዝሙር አገልግልት አንዱ ነው፡፡
      
          
ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር የቱ ነው? እንዴትስ መቅረብ አለበት?

   * . . . ኢየሱስ ጓዴ ነው
   
መልዕክቱ
ጥንታውያን ኦሪየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በመባል የሚጠሩት ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ሶርያ፣ አርመንና ሕንድ በእምነታቸው (የተዋሕዶን ትምህርተ ሃይማኖት በመጠበቃቸው) አንድ ቢሆኑም በሥርዓተ መዝሙር (ማለትም በመዝሙር ዜማና አቀራረብ) ግን በመጠኑ ይለያያሉ፡፡
ለምሳሴ ግብፃውያን የዜማ መሣሪያዎቻቸው ሁለት ብቻ ናቸው፡፡ ነገር ግን ከቅዳሴ በፊትና በኋላ በመዘመራችን፣ ሌሊት ማኀሌት በመቆማችን፤ ሥርዓታችን ተመሳሳይ ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን መዝሙራትን “ኦርቶዶክሳዊ” ነው የምትለው ትምህርተ ሃይማኖትዋን፣ ሥርዓትዋን፣ ለምሳሌ በግብፃውያን ሥርዓት ከዜማቸውና ከመዝሙር መሣሪያዎቻቸው ውጭ መዘመር አይፈቀድም፡፡
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም አንድ መዝሙር ኦርቶዶክሳዊ ነው፣ የቤተ ክርስቲያን ነው ሊባል የሚችለው በየትም ቦታ በጉባዔም ሆነ በግል የምንዘምረው፣ አልያም ደግሞ በካሴት አስቀርፀን የምናሳትመው መዝሙር አዕማደ ምሥጢራትን፣ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን፣ ታሪከ ቤተ ክርስቲያንንና ትምህርተ ሃይማኖትዋን፣ ሥርዓትዋን፣ ታሪኳንና ትውፊትዋን ሲጠብቅና መሠረት ሲያደርግ ብቻ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ልዑል እግዚአብሔርን፣ ቅዱሳንን፣ ንዋያተ ቅድሳትን፣ ወዘተ የምትጠራበት፤ እምነቷንና ፍቅርዋን የሚገልጹ ቃላት አሏት፡፡ እነዚህ ቃላት ዘመን ወለዶች ሳይሆኑ ከጥንት ጀምሮ ቅዱሳን አበው ልመናቸውን፣ ምልጃቸውን፣ ምሥጋናቸውን ያቀረቡባቸው፣ ልጆቻቸውን ያስተማሩባቸው፣ አንድ ገጽ ጽሑፍ ሊገልጣቸው የማይችላቸውን ምሥጢራት በአንድ ቃል የገለጡባቸው ናቸው፡፡ የምንዘምራቸው መዝሙሮች እነዚህን ዕንቁ የሆኑ ቃላት ማፋለስ የለባቸውም፡፡ ምክንያቱም መልእክቱን ያዛባዋልና፡፡
ለምሳሌ አንድ መዝሙር “ኢየሱስ ጓዴ ነው” የሚል ቃል ሊጠቀም አይችልም፡፡ ይህንን ቃል የተጠቀመ አባት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የለም፡፡ ቃሉ የጌታችንን ክብር የሚያሳንስ ነውና፡፡ ቤተ ክርስቲያን ጌታችንን አምላክ፣ አምላከ አማልክት፣ የጌቶች ጌታ፣ የንጉሦች ንጉሥ፣ መድኃኒተ ዓለም፣ ወዘተ. እያለች ትጠራዋለች እንጂ እንደ ሥራ ባልደረባ “ጓዴ” ብላ አትጠራውም፡፡
በአንዳንድ መዝሙራት ላይ ደግሞ ሕዝቡን የበለጠ ለመሳብ ወይንም አንድን ነገር የበለጠ ለመግለጥ እየተባለ ያልተደረገ እንደተደረገ ሆኖ የሚቀርብበት አጋጣሚም አለ፡፡
ለምሳሌ ጌታችን “ከአጥንቱ አንድም አይሠበርም” (ዘጸ.12÷46) የሚለው ቃል ይፈፀም ዘንድ አጥንቱ አልተሠበረም፡፡ ነገር ግን በአንዳንድ የስቅለት መዝሙራት ላይ “አጥንቱ እስኪሠበር ተገረፈ” የሚል ሐረግ ይገኛል፡፡ ይህ ግን ከቅዱሳት መጽሐፍት ትምህርት የወጣ ነው፡፡ ስለ እመቤታችን ሐዘን በሚዘመሩ መዝሙራትም ላይ “በመስቀሉ ሥር ስትወድቅ ስትነሣ እያለቀሰች ያዙኝ ልቀቁኝ እያለች” በሚል አኳኋን ይቀርባል፡፡ ነገር ግን
እመቤታችን አስቀድሞ ስምዖን፡፡ ‹‹በነፍስሺ ሰይፍ ያልፋል›› (ሉቃ.2÷35) በማለት ነግሮአት ስለነበር መከራውን ታውቃለች፡፡ ሐዘንዋ ተስፋ የመቁረጥ ሳይሆን የእናትነት ፍቅርዋን የሚገልጥ ነው፡፡
ስለዚህ የምንዘምረው መዝሙር የቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓትና ትውፊት የጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ይህንንም ለማወቅ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በእምነታቸው በተመሠከረላቸው አባቶችና መምህራን ማሳረም፣ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ጠንቅቶ
መማር፣ መጻሕፍት ቅዱሳትን ማንበብና በእግዚአብሔር ቤት ዘወትር መኖር ዋና መፍትሔዎቹ ናቸው፡፡
  ዜማው ያሬዳዊ ሲሆን

       ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 1300 ዓመታት ያህል ለልዑል እግዚአብሔር ምሥጋናዋን ታቀርብ የነበረበት ዜማ የቅዱስ ያሬድ ዜማ ነው፡፡ በዚህ ዜማ ተጠቅመው አያሌ ቅዱሳን ምሥጋናቸው በልዑል እግዚአብሔር ፊት ቀርቦላቸዋል፡፡ ክብረ ቅዱሳንንና፣ ርስት መንግስተ ሰማያትን ወርሰዋል፡፡ በየጊዜው የተነሡ የቤተ ክርስቲያናችን አበው (እነ አባ ጊዮርጊስ፣ እነ አባ ዘድንግል) ሰዓታትን፣ ማኀሌተ ጽጌን፣ ሰቆቃወ ድንግልን በዚሁ በያሬድ ዜማ ዘመሩት እንጂ ሌላ ዜማ ለመፍጠር አልፈለጉም፡፡ እግዚአብሔር የዘረጋው መንገድ እያለ ለምን ሌላ መንገድ ይፍጠሩ!
አሁንም ሆነ ለወደፊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን እግዚአብሔር በቅዱስ ያሬድ አማካኝነት የሰጣትን ይህንን ዜማ እንደምትጠቀምበት ቅዱስ ሲኖዶስ ለሰ/ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ባወጣው ደንብ ምዕ.5/26/1/ሀ ላይ ደንግጓል፡፡ አጽንቷል፡፡ በመሆኑም ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ የምንዘምረው መዝሙር ይህን ዜማ የጠበቀ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም፣
· ዜማው እግዚአብሔር ወዶ ፈቅዶ የሰጠን እንጂ ቅዱስ ያሬድ በጥበቡ የተፈላስፎ፣ ተራቅቆ፣ ያመጣው አይደለም፡፡
· ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንድንጠቀምበት፤አባታችን እግዚአብሔርንም እንድናመሰግንበት ጠብቃ ያቆየችን ወስናም የሰጠችን ነውና፡፡
· የዜማው ሥርዓት፣ ባሕልና የመሣሪያዎቹ ትርጉም ፍፁም ኦርቶዶክሳዊ መልእክት ያለው ነውና፡፡
አንዳንድ ዘማሪያን የመናፍቃኑን ዜማ ስለሚወዱት በግድ ዜማውን እየጐተቱ በከበሮ በማጀብ ያሬዳዊ ለማድረግ ይጥራሉ፡፡ ነገር ግን ያሬዳዊ ዜማ ማለት የተጐተተ ዜማ ማለት አይደለም፡፡ ይህ ሁሉንም ላለመልቀቅ የሚደረግ ጥረት ካልሆነ በቀር የራሳችን አለን፡፡ የራሳችን እያለንም ወደ ጐረቤት መጓዝ አያስፈልግም፡፡
ክርስቲያን የሆንነው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት መሠረት ተጠምቀን ነው፡፡ ክርስቲያን ለመሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን የመጣነው ሕግዋን ሥርዓትዋን አክብረን እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የሰጠውን ጸጋና በረከት ለማግኘት እንጂ እምነት፣ ሥርዓትና ሕግ ለዋጮች ለመሆን አይደለም፡፡ ስለዚህም ቀድመን የመጣንበትን ምክንያት አንርሳ፡፡ እኛ የምኖረው እግዚአብሔርን በቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት መሠረት እያገለገልን እንጂ በቤተ ክርስቲያንና በክርስትና ሽፋን የገዛ ፍላጐታችን እያሟላን መሆን የለበትም፡፡የራሳችን ዜማ ፈጥረን ከካሴቱ ሽፋን ላይ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ዜማና ሥርዓት የጠበቀ ስላልነው ብቻ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር
መሆን አይችልም፡፡

   መዝሙሮቻችን እና ወጣቱ. . .

        አሁን አሁን በከተማችን ውስጥ የመናፍቃን መዝሙር እንደ አሸን መፍላቱና የእኛ የምንላቸው ዘማሪዎቻችን ጭምር ጊዜው ባመጣው ሙቀትና ጩኸት ተጠቂ እየሆኑ መምጣታቸው፤ታክሲ ውስጥ፣ረጅም ጉዞዎች ላይ የተለያዩ ቦታዎች ላይ የምንሠማው ከትክከለኛው ስርዓተ-ምስጋና ያፈነገጡና ከላይ የገለፅኩት አይነት ሆነው ለይስሙላ መዝሙር እየሆኑ ነው፡፡
 ዘማሪ መሆንና ቤተክርስቲያን አገልጋይ መሆን ይለያያል፡፡ እግዚአብሔር ለማመስገን የግድ ዘማሪ ወይም የመዝሙር ካሴት ማውጣት ላያስፈልግ ይችላል፤አይገባምም፡፡ ምክንያቱም ስንቶቻችን ነን መዝሙርን በመዝሙር ስሜትና ስርዓት የምንዘምረው? ደስ እንዳለን አይደለምን? መዝለል፣መጮህ፣መዘቅዘቅ . . .ማን ያግደናል? ደሞ ለእየሡሴ ብዘቀዘቅለትስ እንዳለችው መናፍቅ ሳይሆን ስራችን ምስጋናችን ወደ ውጪ ሲወጣና ብዙዎችን ሲወክል ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል፡፡ ትልቁ እና ታላቁ ስርዓታችን ይይዘናል፤ብዙ አማኞች ፤ብዙ ለእግዚአብሔር ክብር የሚጨነቁ፣ብዙ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸው፣የበዙ እውነተኛ ክርስቲያኖች አሉ፡፡እነሱን ለገንዘብ ብለን የስሜታችንና የሆዳችን ማራገፊያ ለምን እናደርጋቸዋለን? አንዳንዴ እልም ያለ ዓለማዊ ዘፈን እንኳን እንደዛ አያስጨፍርም መዝሙር ከተብዬው፡፡ በእርግጥ ለምን እንዲህ ተዘመረ መለት ሊከብድ ይችላል ማንም እንደፈለገ የፈለገውን ለገበያ ማቅረብ ይችላል፤መብቱም ከእሱ ጋ ነው፡፡ የማይገባኝ ግን በኢ.ኦ.ተ.ቤ ስር ያሉ መዘምራን ለምን ከአለማዊ አስተሳሰብ፤ ከገንዘብ ፍቅር ተላቀውና ወጥተው እምነቱን የማይመጥን ነገር እንደማያቀርቡ ነው፡፡እነሱ ተሳስተውና እየተሳሳቱ ለምንስ ምክንያተ መጥፊያ እንደሚሆኑ ነው፡፡ ለምንስ ስራዎቻቸውን ለአባቶች ማሳየት መፍራት ጀመሩ? አዋቂነት ይሆን. . . ? “ልጅ አባቱ ሲስቅለት አዋቂ የሆነ መሰለው” እንደሚባለው ትንሽ አጋፋሪና አይዞህ ባይ ሲገኝ ሁሉ የገባን መስሎን ይሆን?
የሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ የመዝሙር ካሴት ሽፋን 
ከሁሉ ግን ቤተ-ክርስቲያናችን ትምህርተ ሃይማኖትን፣ ሥርዓት እና ትውፊትን የጠበቁት እና ያልጠበቁትን የምትቆጣጠርበት መላ ማለት ይኖርባታል፡፡ እንኳን ይህን የተከበረና በረከት ያለው ስጦታ የያዙት ቀርቶ ዓለማዊ ዘፋኞችም የራሳቸው የሆነ ማህበር አላቸው፡፡ ዘፈኖቸውን የሚቆጣጠሩበት. . . . የሚተጋገዙበት ፡፡ “ዘፈኖቻችን የቁጥጥር ስርዐት ይኑራቸው. . . .ጥራት ይጎላቸዋል. . . የወረዱ ናቸው. . .ሞተ ተነሳ. . .እያሉ ይጮኻሉ፤ይወቃቀሳሉ. . .ያወግዛሉ፡፡” እኛ ብዙዎችን የሚወክልና የሚያስተምር ትልቅና ልክ የሆነ ስርዓተ ሀይማኖት ይዘን ዘማርያኑ በመናፋቃዊ መንፈስ የሚያወጡትን መዝሙር መሳይ ዘፈኖች በትንሹ እንኳን መከላከል አልቻልንም፡፡ ስንሞክርም አንታይም፡፡የቤተ-ክርስቲያናችን ስርዓትና ትውፊት የሚያፋልስ ትውልዳዊ እምነትን የሚያጠፋና አባቶቻችን እናቶቻችን ያቆሙትን እና ያወረሱንን የሚንድ እምነተ ተቃርኖ እያየን ዝምታን የወደድነው ለምን ይሆን? ቢያሳስበን መልካም ነው፡፡
         አሁን አሁን ገንዘብ ያላቸው መናፍቅ ወንድሞቻችን ስራዎቻችውን በስፋት እየበተኑ . . . ይህ አሁን አሁን እየተነሳ ያለውን ወጣት ግራ እያጋባቡብን ነው፡፡ “እናሸንፋለን” የሚል መዝሙር ይሁን መፈክር. . . . . .የእግዚአብሔርን ክብር የሚያሳንሱ ቀሽምና የመሸታ ቤት ግጥሞች የሚመስሉ ለደቂቃ እንኳን መሠማት  የማይገቡ ዘፈኖችን ጆሯችን(ጆሮአችን) እንዲሰማ እየተገደገ ነው፡፡ይህ አዲስ ኃይል እና ተስፋ የሆነ ወጣት ባንዲራ ከመስቀልና አካባቢን ከማፅዳት ባለፈ ቤተ-ክርስቲያናዊ ስርዓት ሊማርና ሊያውቅ ይገባል፡፡ጫት ሲቅም በመናፍቅ መዝሙር መሆኑ ባይመለከተኝም መዝሙር እየሰማሁ ነው፤እግዚአብሔርን እያመሰገንኩ ነው ብሎ ግን ለዳንስ የሚጋብዝ ዘፈን ሊሰማ እንደማይገባና ሱስ እስኪሆንበት ሊጠበቅ አይገባም፡፡ ቢቻል በተጠና መልኩ ልናስተምረውና ሁኔታዎችን ልናመቻችለት ይገባል፡፡ በተለይ የሚመለከተችሁ አካላት ልብ ልትሉ ይገባል!!!
አስታውሳለሁ በአንድ ወቅት አንድ መንፈሳዊ ጉዞ እያደረግን ባለንበት ጊዜ አውቶቢሱ ውስጥ የእነ*******(ስም መጥቀስ አያስፈልግም) መዝሙር ሲከፈት የተነሳውን የ “ዝጉልን . . . አትዝጉልን  . . . ” አተካሮና ፀብ፡፡ በመጨረሻ እግዚአብሔር ይመስገን አንድ በመሀላችን የነበሩ ትልቅ አባት የተከፈተው መዝሙርና ፤ መዝሙር በምን መልክ መቅረብ እንዳለበት እንዲሁም መያዝ ያለበትን መዝሙራዊ ለዛ በክርቲያናዊ መንፈስ፤ በአባታዊ  ትምህርት ካስረዱ በኋላ የተከፈተው መዝሙር ‘ እውነት መዝሙር ነውን ’ ብለን እራሳችንን እንድንጠይቅና ጋብዘውን ዝም አሉ፡፡  ምናልባትም ደቂቃም አልፈጀም ካሴቶቹና ሲዲዎቹ ተሰባብረው በመስኮት ሲጣሉ፡፡ ግን ሌላ ቦታስ? አሁንም መናፍቃዊ ይዘት ያላቸው ስራዎች ባለማወቅ ይሰማሉ፡፡ አሁንም በጌታ ደስ ይበላችሁ ይባላሉ፡፡ አሜን ብሎ የሚያልፈው ግን ስንቱ ይሆን?
እርግጥ ነው ጥቂቶች ዘማርያንንና ዘፋኞችን መለየት ይችሉ ይሆናል ግና የበዛው ክፍል ገና ነው ይቀረዋል፡፡ ይሄ ወጣትስ? ታዳጊዎቻችንስ?? ህፃናቱስ???
  እየሱስ እየሱስ የሚሉና የእየሱስ ክርስቶስን ስም በሠፈርተኛ እንድምታ የሚጠሩትን ጨፋሪዎች እንዳይሰማ ማን ያግዘው? ግልፅ ነው ብዙ ስራና ትግል ይጠይቅ ይሆናል፡፡ እስቲ በቅርባችን ያሉትንና በኢ.ኦ..ተ.ቤ. ስርዓተ-ደንብ መሰረት የተዘጋጀ የሚሉትን የራሳችንን ልጆች ልንቆጣጠር እንሞክር፡፡ ነገር ግን ወደፊት የሚወጡትን መዝሙሮችን የሚቆጣጠር አካል ሊቋቋም ይገባል ብዬ አምናለሁ፡፡ ልክ ከላይ እነዳልኩት እንደሙዚቀኞቹ ማህበር ማለት ነው፡፡ ዘማሪዎቻችንም ብትሆኑ እራሳችሁን መመርመርና ምን እየሰራችሁ እንዳለ ልብ ልትሉ ግድ ነው፡፡ እርሶም የሚሰሙትን መዝሙር ልብ ይበሉ፤ በቀላሉ ልዪነቱን ይረዱታል፡፡ 

አበቃሁ! አስተያየታችሁን ስጡበት

ፈሪሃ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!!! አሜ





ምስጋና፡ ማኅበረ ቅዱስ ያሬድ ዘጎንደር



22 comments:

  1. ብስራት ፡ በጣም ድንቅ እዪታ በታምም የሰረጸ ነው ። በርታ ተበራታ !! ፍቁረ-ወላዲት ትባርክህ።

    ReplyDelete
  2. gobez tiru new .... wedemecheresha yeteqeskachew abat endaregut sile-orthodoxawi mezmur mininet yeginzabe maschebecha (yezemenachinin ababal liteqem biye new :) ) timihirtochin mesitet wanawina yemejemeriya sirachin mehon alebet.
    enezih yeteqeskachew Orthodoxawiwin mesmer yeleqequ mezmuroch ye-miyadamitew sew Egziabherin sayhon erasun endiyay new migabizew lik ende zefen emotional attachment sislemifetir benezi mezmuroch yetelekefe sew beqelalu ayilaqeqim enam ehit wendimochachinin sile-mezimuratu liyunetoch sinimekir sinastemirachew befiqirna betigist yihun

    mastekakeya -Mezmurochachinina wetatu 2gna anqets
    >የማይገባኝ ግን በኢ.ኦ.ተ.ቤ ስር ያሉ መዘምራን ለምን ከአለማዊ አስተሳሰብ፤ ከገንዘብ ፍቅር ተላቀውና ወጥተው እምነቱን * የማይመጥን -yemimeTin ነገር እንደማያቀርቡ ነው

    mastewalun yadilen

    ReplyDelete
  3. egezere yestehe beserate ketel.

    ReplyDelete
  4. good point yaberetake

    ReplyDelete
  5. good point bezi ketelebete

    ReplyDelete
  6. እግዚአብሔር ይስጥልን ብስራት በርታልን

    ReplyDelete
  7. እግዚአብሔር ይስጥልን ብስራት ለዚህ ነው ዛሬ መዝሙራችን ከዘፈን ካመናፍቃን “መዝሙር” ዜማ ተወስዶ የሚዘመረው
    ለምሳሌ፡-መላዕክቱ በፊትህ ይቆማሉ ---------ና ዙማዬ ዙማዬ ለኔ ናና (ዘፈን)
    ማርያም ድንግል ንፅህት -----------እንዴት ከርመሻል እቴ ዓለሜ ( የአረጋኸን)
    እመኑ በእርሱ ……………በላያ በላያ (ዘፈን)
    ተወልደ ናሁ ………….አያሆሆ ማታ ነው ድሌ
    ሐመልማለ ሐመልማል ( የሠርግ) …….ብር አምባር ሰበረለዎ
    የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሐሔርን ለእግዚአብሔርን ……….እግዚአብሔር ትክክል ነው ነገር ሁሉ ለበጎ ነዉ (ከመናፍቃን)…….እና ሌሎችም ልናስብበት ይገባል፡፡

    ReplyDelete
  8. እግዚአብሔር ይስጥልን ብስራት ለዚህ ነው ዛሬ መዝሙራችን ከዘፈን ካመናፍቃን “መዝሙር” ዜማ ተወስዶ የሚዘመረው
    ለምሳሌ፡-መላዕክቱ በፊትህ ይቆማሉ ---------ና ዙማዬ ዙማዬ ለኔ ናና (ዘፈን)
    ማርያም ድንግል ንፅህት -----------እንዴት ከርመሻል እቴ ዓለሜ ( የአረጋኸን)
    እመኑ በእርሱ ……………በላያ በላያ (ዘፈን)
    ተወልደ ናሁ ………….አያሆሆ ማታ ነው ድሌ
    ሐመልማለ ሐመልማል ( የሠርግ) …….ብር አምባር ሰበረለዎ
    የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሐሔርን ለእግዚአብሔርን ……….እግዚአብሔር ትክክል ነው ነገር ሁሉ ለበጎ ነዉ (ከመናፍቃን)…….እና ሌሎችም ልናስብበት ይገባል፡፡

    ReplyDelete
  9. Eritrea!! is not one of the Oriential Church ???
    kal hiwet yasemalin regim yeagelglot zemen ysitih !!!
    z from london

    ReplyDelete
  10. ይኸን የተሃድሶ ወሬ የምታራግቡ ሰዎች ለቤተክርስቲያኗና ለእምነታችሁ ተቆርቋሪ መስላችሁ ነገር ግን በውስጡ የምታራምዱት የራሳችሁን ገበያና ጥቅም እንደሆነ የገባው ይገባዋል፡፡ ከዚህ ሌላ ደግሞ በውስጣችሁ የነገሰው የምቀኝነትና የቅናት ስሜት አላስቀምጥ ብሏችሁ በወንድሞቻችሁና በእህቶቻችሁ ፀጋ እራሳችሁ ስለታመመ እረፍት አጥታችሁ ትለፈልፋላችሁ፡፡ ለመሆኑ እናንተ እነማን ናችሁና ነው ያለእኛ አዋቂና ክርስቲያን የለም እያላችሁ የምታደነቁሩን፡፡ እውነተኛ ክርስቲያን ብትሆኑማ ኖሮ የተሳሳቱ ቢኖሩ እንኳን እንዲህ የማርያም ጠላት ከማድረግ ይልቅ ቀርባችሁ በማስተማርና በመወያየት ነገሩን ታስተካክሉ ነበር ወይም ለማስተካከል ትሞክሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ሁላችሁም የሚበልጣችሁ ሲመጣባችሁና ገበያችሁን የሚያቀዘቅዝባችሁ ሲነሳ የየራሳችሁን ውጣዊ ስሜት ጭምብል በማልበስ በቤተክርስቲያን ተቆርቋሪነት ስም አድማ ትቀሰቅሳላችሁ፡፡ እስቲ አንዳችሁ እንኳን የተሻለ ሃሳብ በማቅረብ የተሳሳቱ የሚመለሱበትን፣ ያላወቁ የሚማሩበትን፣ የተጣሉ ታርቀው በእውነተኛ ስሜት ቤተክርስቲያናቸውን የሚያገለግሉበትንና አንድነት የሚፈጠርበትን መልካም ነገር ስበኩ!! እባካችሁ የግል ጥቅሜ ተነካ ዓይነት ጩኸት አቁሙ!!!!

    ReplyDelete
  11. እይታዎችህ መልካም ቢሆኑም የምታየው አንተ ብቻ እንደሆንክ በማሰብህ ግን ከአይነስውር ለይቼ አላይህም አይነስውር ልቡ ብርሃን ነው አንተ ግን የሚታስበውም ልብ የሚትለውም ጭለማ ስለሆነ አልፈርድብህም መዝሙር አንተ እና መሰሎችህ እንደተረዳችሁት ብቻ ሳይሆን ከተለመደው ውጬ ልክ እንደ ንጉስ ዳዊት እ/ር በእራቁት እየተዘለለ ይመለካል እሱን ደሞ ለመፍረድ ዳር ዳር ካልክ የሚልኮልን ታሪክ ላንተ አልነግርህም ብቻ እ/ር ነገርን ከብዙ አቅጣጫ የሚያሳየውን ልቦና ይስጥ።

    ReplyDelete
  12. እኛ የምኖረው እግዚአብሔርን በቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት መሠረት እያገለገልን እንጂ በቤተ ክርስቲያንና በክርስትና ሽፋን የገዛ ፍላጐታችን እያሟላን መሆን የለበትም

    ReplyDelete
  13. --ኢየሱስም አለ አኒ አዉነት ሕይወት መንገድ ነኝ ከአኒ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም
    --ጠባብ አትሆን

    ReplyDelete
    Replies
    1. አስተያየት የምትሰጡ ይበግ ለምድ ልባሾች ቃላታችሁን አስተካክሉ "በእኔ በቀር ነው" ከእኔ አይደለም የሚለው" ለዛ ነዉ ግልብ ግልብ እያርጋችሁህ ታውቃላችሁ ባልገባችሁህ ነገር ሽንጣችሁህን ይዛችሁህ ትከራከራላችሁህ ከላይ አስተያየት የስጣችሁህ ከረሰቲያኖች እርግጠኛ ባልሆንመ አኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስለመሆናችሁህ ብቻ "ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም "እንድሚባለዉ ሆነባችሁህ በጣም ከነከናችሁህ ለዛም ነዉ እነ በግሌ የተጠራጠርኳችሁ ስልሁሉም ፈጣሪ ማስትዋሉን ይስጣችሁህ ይስጠን አሜን! ልስጋችን ባናደላ "እኔ ላንስ እርሱ ግን ሊልቅ ይገባል ብንል" ስራቷን ትውፊቷን እንደነበረ ብናቆየዉ መልካም ነዉ እይትበረዝን ብምጤ ስረአቶች ባንወሰድ ብቻ ፈጣሪ ይርዳን

      Delete
  14. AMANUEL

    yebel yegolmes............


    WITH RESPECT

    ReplyDelete
  15. I really appreciate your view. I don't know how to save the youth from such kinds of "songs". I think it's better to teach the people on the right Ethiopian orthodox spiritual songs so that the people would reject the incorrect ones themselves! besides, a lot is expected from the church's management!

    ReplyDelete
  16. በእርግጥ ለምን እንዲህ ተዘመረ መለት ሊከብድ ይችላል ማንም እንደፈለገ የፈለገውን ለገበያ ማቅረብ ይችላል፤መብቱም ከእሱ ጋ ነው፡፡
    yes he can sell but he/she should take the responsibility and she/he should not say it is prepared according to Ethiopian orthodox tewahdo church rule and regulation, because it is not.our church have the right to condemn and even to brought a file against those person's who are canceling believers under the cover of the church.
    at the end of your writing you are using some harsh words i feel some inconvenience on the words(way of advice), it should be soft, and rather than blaming only those persons it is good to show your view of right way. otherwise keep it up!!! GOD BLESS YOU

    ReplyDelete
  17. Ye Bsrat eyta bemehonu akebrlhalehugn neger gn Yh ende asrtu kalate orit tekebelut KESU LIELA YELEM aynet gn tkkl aydelem!MENFES KDUS AND NEW TSEGA GN BZU ENDEHONE MEMHR ENDEMHONEH MASTAWES AYASFELGENGNM! SLEZI KE EGZIABHIER MENFESKIDUS LIELA TSEGA SIMETA ALKEBELM BEMALETH ENDATKESR EGZIABHIERNM MEKAWEM ENDAYHONBH TNKK BEL!! ESKI DEHNA EGZIEABHIER LEBELTE MEREDAT YADRSEN!

    ReplyDelete
  18. ጥሩ ብለሃል በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ስም የሚወጡ መዝሙሮች ከመውጣቱ በፊት በኣባቶች እንዲታይ የሚል ህግ ቤተ ክርስቲያን ቢኖራት መልካም ነው ዘማሪዎቻችን ምን ያህል እውቀት አላችው እውነት እንደ ንጉስ ዳዊት በእግዚአብሄር ፍቅር ተማርከው ነው ወይስ በገንዘብ ተታለው ምእመናንም በተቻልን አቅም ማንነታችንን ምንነታችንን እንወቅ እንርዳ

    ReplyDelete
  19. አስተያየት የምትሰጡ ይበግ ለምድ ልባሾች ቃላታችሁን አስተካክሉ "በእኔ በቀር ነው" ከእኔ አይደለም የሚለው" ለዛ ነዉ ግልብ ግልብ እያርጋችሁህ ታውቃላችሁ ባልገባችሁህ ነገር ሽንጣችሁህን ይዛችሁህ ትከራከራላችሁህ ከላይ አስተያየት የስጣችሁህ ከረሰቲያኖች እርግጠኛ ባልሆንመ አኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስለመሆናችሁህ ብቻ "ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም "እንድሚባለዉ ሆነባችሁህ በጣም ከነከናችሁህ ለዛም ነዉ እነ በግሌ የተጠራጠርኳችሁ ስልሁሉም ፈጣሪ ማስትዋሉን ይስጣችሁህ ይስጠን አሜን! ልስጋችን ባናደላ "እኔ ላንስ እርሱ ግን ሊልቅ ይገባል ብንል" ስራቷን ትውፊቷን እንደነበረ ብናቆየዉ መልካም ነዉ እይትበረዝን ብምጤ ስረአቶች ባንወሰድ ብቻ ፈጣሪ ይርዳን

    ReplyDelete
  20. ወንድም ብስራት በጥቂቱ ያስቀመጥከው መልእክት የሚደገፍ ነው በተለይ አሁን አሁን እኮ መዝሙር መግዛት እያቆምን ነው ፊታችንን ወደ ቀደሙት መዝሙራት ማዞር ከጀመርን ቆየት ብለናል የ አሁኑ መዝሙር ጩኸቱ ሳይበቃ ውስጡ ፍሬ አልባ መሆኑ ነው ለኛ የሚያስፈልገው ሰውነትን ብቻ በመወዝወዝ የሚያዘልል ዜማ ሳይሆን ሰምተን ምን እናድርግ አስብሎን ወደ ፍጹም ንስ ሃ የሚመራን መዝሙር ነው

    ReplyDelete