በ1928 ዓ.ም በትግራይ ጠቅላይ ግዛት፣ አድዋ አውራጃ፣ እርባ ገረድ በተባለች መንደር ከአባቱ ከቄስ ገብረ እግዚአብሔር ዮሐንስ እና ከወይዘሮ መአዛ ወልደ መድኅን ተወለደ። ትምህርቱን በስዊድን ሚሲዮን፣ እንዲሁም በ1952 በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከታትሎ በትምህርት አስተዳደር የመጀመሪያ ዲግሪውን ተቀብሏል። 1953 ደግሞ በቤተ መጽሃፍት ሳይንስ ትምህርቱን ሊከታተል ወደ አሜሪካ ተጉዞ ሳይጨርስ ተመልሷል።
በአስፋ ወሰን ትምህርት ቤት በእንግሊዝኛ መምህርነት ለ2 ዓመት አገልግሏል። በመቀጠልም ከየተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፤ ሳየንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ባገኘው የትምህርት እድል አማካይነት ወደፈረንሳይ (ኤክስ አን ፕሮቫንስ) በመሄድ ከ1962-1964 ቆይቷል። የሄደበትን ትምህርት አጠናቆ ምስክር ወረቀት ባይቀበልም ቆይታው ከአውሮፓ ባህል እና ስነ-ጽሁፍ እንዲተዋወቅ በጣም እንደረዳው ይናገራል። ወደ ፈረንሳይኛ «Les
Nuits d'Addis-Abeba» ተብሎ በፍራንሲስ ፋልሴቶ የተተረጎመውን የልብ-ወለድ ድርስቱን «ሌቱም አይነጋልኝ»ን ብዙውን ለመጻፍ የበቃው እዚያው በፈረንሳይ እንደሆነም ይናገራል። ይኸው ድርሰቱም ወደ ፈረንሳይኛ ቋንቋ የተተረጎመ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ልብ-ወለድ ነው።
ሌቱም አይነጋልኝ በውቤ በረሃ በ1957 ዓ.ም. ተጀምሮ
በፈረንሳይ አገር ኤክስ አን ፕሮቫንስ የተፈጸመ መጽሐፍ ነው። ደራሲው ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር መጽሐፉ እንዲታተም እሱ ደንታ ባይኖረውም...በመጽሐፉ ውስጥ እንደጠቀሰው «እኔ 'ኮ ያደረብኝ ለዘብተኛ ልዝብ ዛር በበቂ ደሞዝና 'ትርፍ' ስኣት እያምበሻበሸ ስላበረታታኝ ፃፍኩ'ንጂ፤ ይታተም አይታተም ደንታ አልነበረኝም።»
ሌቱም አይነጋልኝ በውቤ በረሃ በ1957 ዓ.ም. ተጀምሮ
በፈረንሳይ አገር ኤክስ አን ፕሮቫንስ የተፈጸመ መጽሐፍ ነው። ደራሲው ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር መጽሐፉ እንዲታተም እሱ ደንታ ባይኖረውም...በመጽሐፉ ውስጥ እንደጠቀሰው «እኔ 'ኮ ያደረብኝ ለዘብተኛ ልዝብ ዛር በበቂ ደሞዝና 'ትርፍ' ስኣት እያምበሻበሸ ስላበረታታኝ ፃፍኩ'ንጂ፤ ይታተም አይታተም ደንታ አልነበረኝም።»
ወዳጆቹ ቢሞክሩም በመንግስት ሳንሱር «ለአንባቢያን የማይገቡ ግልጽ የወሲብ ቃላቶች አሉበት» በሚል ምክንያት እየታገደ ለሃያ አምስት ዓመታት በአንባቢዎቹ እጆች በእጅ እየተገለበጠ ሲነበብ ኖሯል።
በአሁኑ ሰዓት በመጀመሪያ እነዚያ ወሲባዊ ቃላቶችን «ለስለስ» ባሉ ቃላቶች በመተካት ለአንባቢያን እንዲደርስ መጽሐፉ ታትሞ ለገብያ የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም በአገራችን አቆጣጠር በ1999 ያንኑ መጽሐፍ ደራሲው የተጠቀመባቸውን ቃላቶች ትክክለኛ ግልባጭ የያዘ «ሌቱም አይነጋልኝ...እንደ ወረደ» ለአንባቢያን ቀርቧል።
ስብሐትም እዚሁ ዕትም ላይ «እንግዲህ አንባብያን ሆይ፤ በገዛ ታሪኬ፤ በገዛ ሦስት ሺ ዘመን ያገሬ ክርስትና፤ በገዛ ውቤ በረሀዬ፤ የኖርኩትን፤ ያየሁትን፤ የሰማሁትን፤ በተቻለኝ አቅምና በታደልኩት የትረካ ተሰጥዎ ለአራዳዎችም ለፋራዎችም ያገሬ ልጆች (ያውም ከሊቅ እስከ ደቂቅ!) ለምን አላበረክትላቸውም? አራዳዎቹም አብረውኝ ደስ ይላቸዋል፤ ፋራዎቹም ድብርታቸው ይብስባቸውና አንጀቴ ቅቤ ይጠጣል፤ ቀኑ የፆም ቢሆንም፤ እና እኔ የቄስ ልጅ፤ የደብተራ የልጅ ልጅ በመሆኔ የምኮራ ብሆንም። ያውም መብቴ በህገ መንግስት እየተጠበቀልኝ! ለሁላችሁም እንሆ በረከት!» እያለ ይኼንን የሚይስቅ፤ የሚያዝናና እና የ'ውቤ በርህን' የ1950ዎቹ ታሪክ 'የሚያስተምረን' መጽሐፍ አቅርቦልናል።
ስብሐት ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ በመነን መፅሄት የዝግጅት ክፍል ውስጥ ሰርቷል። በ1966 ዓ.ም. ወታደራዊው ደርግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ሲቋቋም በአርታኢነት ተቀጥሮ ሰርቷል። በመንግሥት ትእዛዝም ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን የካርል ማርክስ ሥራ የሆነውን ካፒታልን (Das Capital) ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ በመመለስ ሥራ ላይ ተሳትፏል።
ብዙዎቹ የስብሐት ሥራዎች በተጻፉበት ጊዜ ለመታተም ባይታደሉም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የህትመትን ብርሃን ለማየት በቅተዋል። ጽሁፎቹ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይታተሙ ለመቆየታቸው ዋነኛው ምክንያቱ ስብሐት በመጽሐፉ የሚጠቀማቸው ቃላት ብዙዎቹ በኢትዮጵያ ባህል ያደገ አንባቢን አይን የሚያስፈጥጡ፣ ጆሮ የሚያስይዙ በመሆናቸው ነው። በገበያ ላይ በቅርብ የወጡት ድርሰቶቹ ከመጀመሪያ ቅጂያቸው ብዙ ለውጥ እና የአርትኦት ሥራ የተደረገባቸው እንደሆኑ ይነገራል። ስለዚሁ ጉዳይ ለአዲስ ላይቭ በሰጠው ቃለመጠይቅ ላይ ሲናገር «በጨለማ ያልተደረገውን ነገር አንድም የጻፍኩት የለም... ያለውን እንዳለ ነው የምጽፈው» ብሏል። ይህንኑም ከኤሚል ዞላ የአጻጻፍ ዘይቤ የወሰደው እንደሆነ ይናገራል።
ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ደራሲ፣ አርታኢ፣ ጋዜጠኛ ብቻ አይደለም - የልብ-ወለድ ድርሰት ገጸባህርይም ነው።ለኢትዮጵያ የአጫጭር ልብ ወለዶች ማደግም ያበረከተው አስተዋጽኦው ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ሀያሲም ነው።
‹‹ደራሲው›› የተሰኘው የበአሉ ግርማ ልብ-ወለድ በስብሐት ህይወት ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ነው።
የ2 ወንዶች እና የ3 ሴቶች አባት ጋሽ ስብሃት አሁን በ76 ዓመቱ አርፏል ።የቀብር ስነ ስርአቱም ሰዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል። በደራሲ ስብሃት የቀብር ስነ ስርአት ላይ ወዳጅ ዘመዶቹ፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ታዋቂ አርቲስቶችና አድናቂዎቹ ተገኝተዋል።
ውይ ላይብረሪያችን ተቃጠለ ነብስ ይማር
ReplyDeleteውይ ላይብረሪያችን ተቃጠለ ነብስ ይማር
ReplyDeleteWhat is the relevance of this news to your view?
ReplyDeleteWhat is the relevance of this news to your view?
ReplyDeletewhat idea we gain from this?are you sure it is essential to present this on your site? please edit and tell us what we learn from this?
ReplyDeleteSibhat wetatochin sirat indaynorachew, bilginan indiweduna indilemamedu yaderege inji min aynet astewatseo adirgual? besine tsihufim min yeteleye tesetiwo neberew? Fetari nefsun yimarew
ReplyDeleterealy we lost him
ReplyDelete75 amet balge keltame neber.andande bota
ReplyDeleteስብሀት በጣም የማደንቀው ደራሲ ነበር። በዚህም ምክንያት መሞቱ
ReplyDeleteበጣም ካሳዘነኝ ሰዎች አንዷ ነኝ። እውነትን አጥርቶ ያሳየ የይሉኝታና
የውሸት ሰው ባለመሆኑ ሳደንቀው ኖሬያለሁ። ሳስበው እንደውም
ስብሀት የዘመኑ ሰው ቢሆን? ምን እናይ ምን እናነብ ነበር? ውሸትን
ያላደነቀ፣ ለውሸትም ያልኖረ እውነትን ያንጸባረቀ በመሆኑ ከሀገራችን
ሰዎች ቴዲ አፍሮንና ስብሀትን በከፍተኛ ሁኔታ አደንቃቸዋለሁ።
ውድ ስብሀት
ነፍስህን የውነት አምላክ በገነት ያኑራት
ህይወት እንደዚህ ናት
ለነገ እኔነቴ አጥብቄ ባስብም
መቼም ሰው ነኝና
ከመሞት አልድንም
ይገርማል ይሄ ጽሑፍ በመንፈሳዊ ዓይን ሲታይ ምን ዓይነት ቁምነገር ዓለው ብላችሁ ትገምታላችሁ ???????
ReplyDeletesibihat tilik sew neber aznenal
ReplyDelete