ፀሐፊ፡- አለማየሁ አንበሴ
ምንጭ፡- አዲስ አድማስ ጋዜጣ / መስከረም 4 ቀን 2006 ዓ.ም እትም
ምንጭ፡- አዲስ አድማስ ጋዜጣ / መስከረም 4 ቀን 2006 ዓ.ም እትም
![]() |
ከሌሊቱ 9 ሰዓት በቅድሰት ክርስቶስ ሠምራ ነዓለ ንግስ ላይ በምዕመናን
መካከል ተገልፆ በቀስተ ደመና ብርሃን በመብረቅ ድምፅ የወረደው መስቀል
ምስል፡-አዲስ አድማስ ጋዜጣ |
ባለፈው ሃሙስ ከአቃቂ ከተማ በማለዳ ተነስተን ከ2 ሠአታት የእግር ጉዞ በኋላ ከቤተ ክርስቲያኑ ስንደርስ፣ በጥቂት ምዕመናን ተሣታፊነት የእለቱ ቅዳሴ እየተከናወነ ነበረ፡፡ ከቆይታ በኋላ ግቢው ከየአቅጣጫው የመስቀሉን ታሪክ ሠምተው በመጡ ምዕመናን ተሞላ፤ መስቀሉ ከሰማይ ሲወርድ አይቻለሁ የሚሉት መጋቢ ሃዲስ ፍስሃ፣ ስለ መስቀሉ አወራረድ ገለፃ ማድረግ የጀመሩት ከቅዳሴው በኋላ ነው፡፡
ግቢው ውስጥ ከቤተ ክርስቲያኑ ህንፃ አጠገብ መስቀሉ የወደቀበትን ስፍራ እያመለከቱ ይናገራሉ -ቦታው በቆርቆሮ ታጥሮ ድንኳን ተተክሎበታል። መስቀሉ አርፎበታል ከተባለው ስፍራ አፈር እየቆነጠረ የሚቀርብላቸው ምዕመናን አፈር እየተመለከቱ የመጋቢ ሃዲስን ገለፃ ያዳምጣሉ፡፡






