በኤፍሬም እሸቴ
“ፌስቡክ”ን መጠቀም ከጀመርኩበት
ጊዜ ጀምሮ ብዙ ሰዎች “ሃይማኖት” የሚለው ቦታ ላይ የሚያስቀምጡትን ስመለከት እንዲሁም አንዳንድ የማላውቃቸው ሰዎች
ወይም “የፌስቡክ ጓደኝነት” የሚጠይቁኝ ወዳጆቼ እነማን መሆናቸውን ለማወቅ የግል ማኅደራቸውን እና ማንነታቸውን
ወደሚያሳየው ቦታ ስገባ እና ስለ ሃይማኖታቸው ሳነብ የሚገርም ነገር አይቻለኹ። ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሣሣኝ
ደግሞ ተደጋጋሚነቱ ነው። እና እነዚህ ወዳጆቼ ሃይማኖት የሚለው ሥፍራ ላይ ሲጽፉ “ግሪክ ኦርቶዶክስ” ይላሉ። ሰዎቹ
ግሪካውያን እንነዳልሆኑ ይታወቃል።
ምክንያቱም ግሪካዊነት በትውልድ የሚመጣ
ዜግነት ነው። ማለት የፈለጉት ደግሞ ስለዜግነታቸው እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ነገሩ “ምን ዓይነት ኦርዶክስ እንደሆንን
ያለመረዳት” ወይም “ኦርቶዶክስነታቸውን ለሌሎች ዜጎች የማስረዳት ችግር” መሆኑን ገመትኩኝ። ስለዚህም ነው “ምን
ዓይነት ኦርቶዶክስ ነን?” ለማለት የፈለግኹት።የሚገርመው ይህንን የሚመስል አንድ ድንቅ ጉዳይ በማስታወስ ልጀምር። ታሪኩ የታላቁ ኢትዮጵያዊ የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ነው። እንዲህ ይላል፦
"ይህችን መጽሐፍ ለመጻፍ ያነሣሣኝ ዋናው ምክንያት የሚከተለው ነው። በ1962 ዓ.ም ለትምህርት ወደ ውጭ አገር በሔድኩበት ጊዜ ብዙ ፈረንጆች እኔንም ሆነ ጓደኛዬን የሚጠይቁን “የቅብጥ” ‘የኮፕት ቤተ ክርስቲያን መነኮሳት ናችሁ ወይ?’ እያሉ ነበር። በትምህርት ገበታችንም ላይ እንዳለን የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን “የቅብጥ ቤተ ክርስቲያን” እያሉ ሲጠሯት በማስማቴ ኅዘን አደረብኝ። በመሠረቱ “ኮፕት/ ቅብጥ” ግብጽ ወይም ምስር ማለት ሲሆን “”ሂኩፕታህ” በጥንት የግብጽ ቋንቋ “ቤት” ማለት ነው። ከሱ የወጣ ነው። ግሪኮች ግን “ሀ” ፊደል ስለሌላቸው “ኤጊፕቶስ” ወይም ኮፕት ይሉታል። እንግዲህ “ኮፕት” የሀገር ወይም የነገድ ስም ነው ማለት ነው። ስለዚህ የግብጽ ክርስቲያኖች በሀገራቸው በነገዳቸው የኮፕት ወይም የቅብጥ ክርስቲያኖችም ይባላሉ። ዐረቦችም እል አቅባጥ ይሏቸዋል። የቃሉ ፍች ይህ (ሆኖ) ሳለ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን የቅብጥ ቤተ ክርስቲያን ብሎ መሠየም ሀገረ ትውልድን የሚያቃውስ ዜግነትን የሚደመስስ መስሎ ይታያል። … እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት በዶግማና በቀኖና አንድ ይሁኑ እንጂ በሀገረ ስብከት የየራሳቸው ድርሻ ስላላቸው፣ ባንዱ ስም ሌላው አይጠራበትም። ስለዚህ በስማችን ሌላ እንዲጠራበት አንፈልግም፤ እኛም በሌላ ስም መጠራት አንሻም።” (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ 3ኛ እትም፤ 1991 ዓ.ም፤ ገጽ 8-9)"
A picture I took from St.Emmanuel Church
in Berlin Germany
His Grace Archbishop Zekarias and Melake Tsion Belachew Worku, at Columbus Ohio St.Gabriel Church. |
እንግዲህ አሁን ሃይማኖታቸው
የ“ግሪክ ኦርቶዶክስ” የሚመስላቸውም ቢሆኑ የተሳሳቱት ብፁዕነታቸው እንዳሉት የራስን እምነትና ታሪክ ካለማወቅ
የተነሣ ነው። እርሳቸው “የቅብጥ ኦርቶዶክስ” እንዳልሆንን ያስረዱበት መልስ አሁንም ላነሣነው ጥያቄ መልስ ይሆናል።
በእንግሊዝኛ ወይም በሌላ የውጭ ቋንቋ ራሳችንን
መግልጽ ቢያስፈልግም “ኦርየንታል ኦርቶዶክስ Oriental Orthodox” (ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ ሶርያ፣
ሕንድ-ማላንካራ፣ አርመን እና ኤርትራ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት) መሆናችንን፤ ከዚያም ውስጥ ደግሞ ልክ እንደ
አርመን ኦርቶዶክስ ክርስትናን በመቀበል የሚቀድማት የሌለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች
መሆናችንን መናገር ትክክለኛ መልስ ነው።
ግሪኮችን ጨምሮ የራሺያ እና የሌሎች የምሥራቅ
አውሮፓ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት እንደ እኛው “ኦርቶዶክስ” ቢባሉም “ኦርቶዶክስ ተዋሕዶዎች” አይደሉምና
በዶግማም ሆነ በቀኖና አንድነት የለንም። ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንንም አብረን አንካፈልም። እነርሱ ጋር አንጠመቅም፣
አናስጠምቅም። ቁርባናቸውንም አንቆርብም። እነርሱም “የምሥራቅ ኦርቶዶክሶች Eastern Orthodox” ይባላሉ።
ስለዚህ ራሳችንን “የግሪክ ኦርቶዶክስ” ማለት ራሳችንን “ካቶሊክ” ወይም “ፕሮቴስታንት” እንደማለት ይሆናልና
ትርጉሙ ትክክል አይሆንም።
በተጨማሪም ሃይማኖታችን “ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነው
Ethiopian Orthodox Tewahedo” ማለት በራሱ ትልቅ ምስክርነት ነውና እምነታችንን በትክክል ለመግለጥ
እንሞክር። ከዚህ በተረፈ ግን የብፁዕነታቸውን መጽሐፍ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ)
ማንበብ “የተዋሕዶ ልጅ” መሆን ማለት ምን ማለት መሆኑን በትክክል ስለሚያስረዳን ያላነበባችሁ ታነቡ ዘንድ
እጋብዛለኹ። መልካም ንባብ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
በጣም አስፈላጊና እንደተባለውም ብዙሰዎች የሚሳሳቱትን ነገር ነው ያቀረብከውና ላንተም ለዲያቆን ኤፍሬምም ምስጋናችን ይድረሳችሁ በርቱ ጥሩ ግምር ነው!
ReplyDeleteበጣም ጥሩ መረጃ ነው:: ከቻልክ ከምሥራቅ ኦርቶዶክሶች ጋር ያለንን ትልቅ ልዩነት በታቀርብልን ደስ ይለኛል::
ReplyDeleteWhen are you going to write something new? Last time I read your article "Addis Ababa & Frkena" ... I loved it so much and I was like... we have one more guy who really can write. But... Write something or else why opening a blog????
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን።መቸም ግራ የተጋባን ትውልዶች ነን ይህን የግሪክ ኣርተዶክስ የሚባለው አባባል ብዙ ምሁር ነን የሚሉ
ReplyDeleteየሚጠቀሙበት አባባል ነው።እባካችሁ ስለዚህ ስለቁርባኑ ጉዳይም አክላችሁ ብትጵፎ መልካም ነው።
Egeziyabeher yesetelegn temerebetalehu
ReplyDeletewow !! big lesson Dn. !!
ReplyDeleteamelake bacharenatu yebarekehe ewnat betam mawake yalbenen selasawakehen amelake ahunem chamero yebarekeh degele beamalajenatw atelayeh
ReplyDeletethanks a lot but try to to show the basic difference b/n Greek and oriental orthodox for those who have no the concept about it.
ReplyDeleteIn my opinion for those who have no concept about the difference try to read the book written by diacon Ahadu Asres "yemenafiqan maninetoc ena melsochachew""የመናፍቃን ማንነቶች እና መልሶቻቸው"
from Diacon h
የእውነትን መንገድ አስተማርከን
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይባርክልን ።
እውነትን አሳየህን እግዚአብሔር ይባርክህ ።
ReplyDelete