ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Tuesday, April 10, 2012

ጉዞ ወደ ‹‹ ዝቋላ አቦ ›› ልዩ የጉዞ ማስታወሻ 2 ??



     ‹‹ጉዞ ወደ . . .  ዝቋላ አቦ ልዩ የጉዞ ማስታወሻ 1 ›› በሚል እየፃፍኩ የነበረውን የጉዞ ማስታወሻ አንብባችሁ ቀጣይ ክፍሉን በጉጉት ለምትጠብቁ አንባቢያን አንዲት መልዕክት ላስተላልፍ ፈለኩ፡፡
የአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክብረ በዓል እጅግ በጣም ማራኪና የአባታችን ተአምራት በዐይን የሚታይበት አስገራሚና ውብ ክብረ በዓል ነው፡፡ የእውነትም ክርስቲያን መሆን በራሱ ኩራት የሚሆንበትና እምነትን የሚያፀና የበረከት ቦታ ነው፡፡ በተጨማሪ በዓሉን ለማክበር ወደ ቦታው ሲኬድ ያለው ጉዞ እንዲሁ ድንቅ ሊባል የሚችል ነው፡፡ከሁለትና ሶስት ሠዓት በላይ የሚፈጀው ይህ ጉዞ የእምነት ብርታት ጥንካሬ የሚለካበት ህብረቱ፣ሳቁ፣ ጨዋታው፣ መከባበሩ ድካሙ ሁሉም የሚታዩበት ነው፡፡ በዓለ ንግሱም ፍፁም መንፈሳዊና ውብ ነው፡፡ መሳጭ ታሪክም አለው፡፡
የአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክብረ በዓል እጅግ በጣም ማራኪና የአባታችን ተአምራት በዐይን የሚታይበት አስገራሚና ውብ ክብረ በዓል ነው፡፡ የእውነትም ክርስቲያን መሆን በራሱ ኩራት የሚሆንበትና እምነትን የሚያፀና የበረከት ቦታ ነው፡፡ በተጨማሪ በዓሉን ለማክበር ወደ ቦታው ሲኬድ ያለው ጉዞ እንዲሁ ድንቅ ሊባል የሚችል ነው፡፡ከሁለትና ሶስት ሠዓት በላይ የሚፈጀው ይህ ጉዞ የእምነት ብርታት ጥንካሬ የሚለካበት ህብረቱ፣ሳቁ፣ ጨዋታው፣ መከባበሩ ድካሙ ሁሉም የሚታዩበት ነው፡፡ በዓለ ንግሱም ፍፁም መንፈሳዊና ውብ ነው፡፡ መሳጭ ታሪክም አለው፡፡
ሁሌም የሚያስገርመኝ  በቅዳሴ ሰዓት እርኩስ መንፈስ የተፀወታቸው (ያዛቸው) በሙሉ መሄጃና ማምለጫ ስለሌላቸው ዛፍ ላይ በመውጣት ነው እንደአውሬ የሚጮኹት፡፡

ወደ ጉዳዬ ስመጣ ይህንም ጉዞ ‹‹ ጉዞ ወደ. . .  ዝቋላ አቦ- የጉዞ ማስታወሻ ›› በሚል ርዕስ ስለቦታው ቅዱስነት እንዲሁም ስለ በዓሉ ይዘት በማስታወሻ መልክ ማቅረብ ጀምሬ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ክፍል አንዱ ላይ ያሰፈርኳቸው ግለሰቦችና አባቶች የጉዞ ማስታወሻው ውበትና የ ታሪኩን ፍሰት የሚጠብቁልኝ ነበሩ፡፡ እዚህ ላይ እንድታውቁልኝ የምፈልገው ገዳሙ ውስጥ ያሉ አባቶችና እናቶችን ለእናንተ ለማቅረብና ለማስተዋወቅ ያለኝን ፍላጎት ነው፡፡ ብዙ አስገራሚ ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡ ይህንን ነበር በጉዞ ማስታወሻዬ ላይ ላቀርብላችሁ የነበረው፡፡ ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ታሪኩ ሲያልቅ ታሪካቸው ለህዝብ የሚወጣባቸው አባቶችና እናቶችን አሉ፡፡ ይህንን የሚያውቁ ሠዎች ደግሞ ፅሁፉን ካነበቡ በኋላ በስልክም በአካልም አግኝተውኝ አውርተን ነበር፡፡ እርግጥ ነው ፅሑፉን ስጀምረው የሚመለከታቸውን ጠይቄና አስፈቅጄ እንዲሁም ስለታሪኩ አቀራረብ አውርቼ ነበር፡፡

ነገር ግን ፅሁፉ ካለቀ በኋላ የሚያመጣውን ተፅዕኖና ቀውስ እንዲሁም ታሪካዊ ፋይዳ ስረዳ ፅሑፉን ትንሽ መዘግየት ፈለኩ፡፡ ቀውስ ስል አባቶች ከአባቶች፣እናቶች ከእናቶች ይጋጫሉ ወይም ረብሻ ይፈጠራል ለማለት አይደም፡፡ ታሪኩ ላይ ያሉ ዓለማዊ ህይወት በቃን ብለው ሁሉን ትተው ወደ ገዳሙ የገቡ አባቶች ላይ ጫና ላለመፍጠር እንዲሁም ላለመረበሽ መፈለግ ነው፡፡ አባቶቹ ሠዎች ስለነሱ ባያውቁ ምርጫቸው ከመሆኑም በላይ መንፈሳዊ ህይወታቸውንም በዚህ ወቅት ማሳየትና መረበሽ ተገቢም ባለመሆኑ ነው፡፡በጉዞ ማስታወሻዬ ላይ ታሪካቸውን፣የገዳሙን ውበትና በጉዞው የሚገኘውን ታላቅ በረከት ሁሉን ብዘረዝረው ደስታዬ ነበር፡፡ቃሌንም ባለማክበሬ እንዲሁም ሁለተኛውን እ ቀጣይ ክፍሎቹን ስጠብቁ ለነበረ ሁሉ ይቅርታ እየጠየኩኝ አሁንም በዚህም ይሁን በሌላ መንገድ ቀጣዩን ክፍል ለማቅረብ ጥረት ላይ ነኝ፡፡ ቅድሚያ ግን ለአባቶቼና እናቶቼ ፍላጎትና አስተሳሰብ እገዛለሁ፡፡ የሚሉኝንም ሠምቼ አዲስ ነገር ይዤ ልቀርብ እሞክራለሁ፡፡


አመሰግናለሁ! አበቃሁ!   

በወቅቱ የነበረውን ጉዞና በረከተ ድካም ለመመልከት ከፈለጋችሁ ‹‹ የዝቋላ ውበቱ ›› የሚለውን ይመልከቱ የገዳሙ ተፈጥሯዊ ውበት ልዩ ነው፤ይማርካል፡፡ እንዲሁም ክፍል አንድን ማንበብ ለምትፈልጉ ‹‹ጉዞ ወደ . . . ዝቋላ አቦ ልዩ የጉዞ ማስታወሻ 1 ›› የሚለውን ይመልከቱ፡


No comments:

Post a Comment