ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡
Showing posts with label አስጎብኚው. Show all posts
Showing posts with label አስጎብኚው. Show all posts

Thursday, June 7, 2012

የደጋጎች ሀገር - ማህበረ ፃድቃን ዴጌ

   ማቴዎስ ሐዋርያ ከክርስቶስ ልደት በፊት በሳባ፣በባዜንና በሮምሃይ ዘመነ መንግስት መስዋዕተ ኦሪት ይሰዋበት ወደ ነበረው ወደ እዚህ ገዳም መጥቶ ጥምቀት ይጀምራል፡፡ ያን ግዜ የነበሩ አረማውያን ሁኔታው ስላላማራቸው ሐዋርያውን በብዙ መንገድ ሊፈትኑት ከፍ ሲልም ሊገሉት ይሞክሩ ነበር፡፡ ለዚህም ምሳሌ የሚሆነው በጣም አደገኛ የተባሉ ሁለት ዘንዶዎችን እንዲበሉት ሰደውበት ካሁን አሁን ሞቶ እናገኘዋለን ብለው ሲጠብቁ ዘንዶዎቹን በመስቀል ቢባርካቸው  መልካቸው ሳይለወጥጠባያቸው እንደ በጎች ሆነዋል፡፡
እንደገና ዳግም የንጉሱ ሳባጥ ልጅ ድንገት ትሞትና ይጠራል፡፡ በያዘውም መስቀል ቢነካት ወዲያው ተነሳች፡፡ ይሄኔ አናምንም ብለው የነበሩት አረማውያን ይህንን ተአምራት አይተው አምነው ተጠመቁ፡፡


‹‹ አቴዥን ሕንደኬ›› ንግስተ ነገስታት ዘኢትዮጵያ

        
ማህበረ  ዴጌ ቤተክርስቲያን  በ39 ዓ.ም እንደተተከለ በግልፅ ተቀምጧል ፡፡ ይኸውም ‹‹መፅሐፈ ሱባዔ›› በመሪ ኤ.ኤም የተዘጋጀ መፅሐፍ ከምዕራፍ 11 በገፅ 132 ላይ ‹‹ አቴዥን ሕንደኬ›› ንግስተ ነገስታት ዘኢትዮጵያ ሆና በነገሰች በ39 ዓ.ም በአንደኛ ዓመተ መንግስትዋ ወንጌላዊ ማቴዎስ በ 40 ዓ.ም ማህበረ ፃድቃን ዴጌ ገብቶ ሲያስተምርና ሲያጠምቅ ሰምታ መኳንንትንና መሳፍንትን አስከትላ ‹‹ መርዌ›› ወረደች ይላል፡፡
በዚህም ንግስቲቱ ቅዱስ ማቴዎስን አግኝታ‹‹ እየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አብ የባህርይ ልጅ መሆኑን አውቃለሁ ይሁን እንጂ ዳግመኛ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መወለዱን አላውቅም ነበር፡፡ አሁን ግን በትምህርትህ መንፈስ ቅዱስ ስለገለፀልኝ አጥምቀኝ›› አለችው፡፡

Thursday, April 12, 2012

ከማን አንሼ ሳምንት

    አውዳዓመት ሲመጣ ወዳጅ ከዘመድ ይጠያየቃል፡፡ ‹‹ እንኳን አደረሳችሁ›› ‹‹ እንኳን አብሮ አደረሰን›› ማለት ባህላችን ነው፡፡ እኔም እንኳን አደረሳችሁ ብያለሁ፡፡ እነሆ ታላቁ አውዳዓመት ፋሲካ ሊደርስልንበጣት የሚቆጠሩ ጥቂት ቀናት ቀርተውታል፡፡ በተለይ ያለፉትን ሁለቱን ወራት በፆምና በፀሎት ለፈፀሙ ለኢ.ኦ.ተ.ቤ አማኞች በዓሉ ከምንም በላይ ነው፡፡ ቀጣዮቹ ሳምንታትና ቀናት በበዓላት የተሞሉ ናቸው ስቅለት፣ ፋሲካ( ትንሳዔ)፣ ዳግማ ትንሳኤ በሽበሽ ነው፡፡ ለሁለት ወራትም ከብዙ ነገር የራቀው ሆድም ያገኘውን ያፍሳል፡፡ እዚህ ላይ ብዙ ግዜ የሚገርመኝ ፆም ከመግባቱ በፊት ያለው ግርግርና እንዲሁም ደግሞ ፆሙ ሲፈታ ያለው ውክቢያና ፈንጠዝያ ነው፡፡ መንደሮች ይደማምቃሉ፣ ቅምቀማ( መጠጫ) ቦታዎችም ከአፍ እስከ ገደብ ይሞላሉ፤ ግሮሰሪዎች፣ ስጋ መሸጫዎችንም እንዲሁ በስራ ይወጠራሉ፡፡ በዚህ ወቅት አንባቢ ማግኘት ይከብዳል፤ ቤተመፅሐፍቶቻችን ይቀዛቀዛሉ፣ጋዜጣ አንባቢ ብዙም አይገኝ፡፡ ‹‹ ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ›› እንደሚባለው ሁሉም በዓሉን በደስታ ለማሳለፍ የተቻለውን ያደርጋል፡፡ ሲልም ካቅም በላይ የሆኑ ነገሮችን ከማድረግ ወደ ኋላ የሚል የለም፡፡ በዓል ነዋ! ይህ ነገራችን ቢቀረፍና እራሳችንን ሆነን በዓሉን ብናከብር መልካም ነው፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት የኑሮ ውድነት ጣራ በነካበትና ሁሉ ነገር ውድ በሆነበት ሁኔታ ከአቅም ጋር የማይሄድ ወጪ ማድረግ ትርፉ ብስጭትና ማማረር ነው፡፡ ይህ መማረር ምናልባትም ከመንግስት አልፎ  ‹ እግዚአብሔር›ንም ወደ ማማረር ሊያመጣ ይችላል፡፡ ይሄኔ ጉዳዩ ከበድ ይላል፡፡

Tuesday, April 10, 2012

ጉዞ ወደ ‹‹ ዝቋላ አቦ ›› ልዩ የጉዞ ማስታወሻ 2 ??



     ‹‹ጉዞ ወደ . . .  ዝቋላ አቦ ልዩ የጉዞ ማስታወሻ 1 ›› በሚል እየፃፍኩ የነበረውን የጉዞ ማስታወሻ አንብባችሁ ቀጣይ ክፍሉን በጉጉት ለምትጠብቁ አንባቢያን አንዲት መልዕክት ላስተላልፍ ፈለኩ፡፡
የአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክብረ በዓል እጅግ በጣም ማራኪና የአባታችን ተአምራት በዐይን የሚታይበት አስገራሚና ውብ ክብረ በዓል ነው፡፡ የእውነትም ክርስቲያን መሆን በራሱ ኩራት የሚሆንበትና እምነትን የሚያፀና የበረከት ቦታ ነው፡፡ በተጨማሪ በዓሉን ለማክበር ወደ ቦታው ሲኬድ ያለው ጉዞ እንዲሁ ድንቅ ሊባል የሚችል ነው፡፡ከሁለትና ሶስት ሠዓት በላይ የሚፈጀው ይህ ጉዞ የእምነት ብርታት ጥንካሬ የሚለካበት ህብረቱ፣ሳቁ፣ ጨዋታው፣ መከባበሩ ድካሙ ሁሉም የሚታዩበት ነው፡፡ በዓለ ንግሱም ፍፁም መንፈሳዊና ውብ ነው፡፡ መሳጭ ታሪክም አለው፡፡
የአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክብረ በዓል እጅግ በጣም ማራኪና የአባታችን ተአምራት በዐይን የሚታይበት አስገራሚና ውብ ክብረ በዓል ነው፡፡ የእውነትም ክርስቲያን መሆን በራሱ ኩራት የሚሆንበትና እምነትን የሚያፀና የበረከት ቦታ ነው፡፡ በተጨማሪ በዓሉን ለማክበር ወደ ቦታው ሲኬድ ያለው ጉዞ እንዲሁ ድንቅ ሊባል የሚችል ነው፡፡ከሁለትና ሶስት ሠዓት በላይ የሚፈጀው ይህ ጉዞ የእምነት ብርታት ጥንካሬ የሚለካበት ህብረቱ፣ሳቁ፣ ጨዋታው፣ መከባበሩ ድካሙ ሁሉም የሚታዩበት ነው፡፡ በዓለ ንግሱም ፍፁም መንፈሳዊና ውብ ነው፡፡ መሳጭ ታሪክም አለው፡፡
ሁሌም የሚያስገርመኝ  በቅዳሴ ሰዓት እርኩስ መንፈስ የተፀወታቸው (ያዛቸው) በሙሉ መሄጃና ማምለጫ ስለሌላቸው ዛፍ ላይ በመውጣት ነው እንደአውሬ የሚጮኹት፡፡

ወደ ጉዳዬ ስመጣ ይህንም ጉዞ ‹‹ ጉዞ ወደ. . .  ዝቋላ አቦ- የጉዞ ማስታወሻ ›› በሚል ርዕስ ስለቦታው ቅዱስነት እንዲሁም ስለ በዓሉ ይዘት በማስታወሻ መልክ ማቅረብ ጀምሬ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ክፍል አንዱ ላይ ያሰፈርኳቸው ግለሰቦችና አባቶች የጉዞ ማስታወሻው ውበትና የ ታሪኩን ፍሰት የሚጠብቁልኝ ነበሩ፡፡ እዚህ ላይ እንድታውቁልኝ የምፈልገው ገዳሙ ውስጥ ያሉ አባቶችና እናቶችን ለእናንተ ለማቅረብና ለማስተዋወቅ ያለኝን ፍላጎት ነው፡፡ ብዙ አስገራሚ ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡ ይህንን ነበር በጉዞ ማስታወሻዬ ላይ ላቀርብላችሁ የነበረው፡፡ ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ታሪኩ ሲያልቅ ታሪካቸው ለህዝብ የሚወጣባቸው አባቶችና እናቶችን አሉ፡፡ ይህንን የሚያውቁ ሠዎች ደግሞ ፅሁፉን ካነበቡ በኋላ በስልክም በአካልም አግኝተውኝ አውርተን ነበር፡፡ እርግጥ ነው ፅሑፉን ስጀምረው የሚመለከታቸውን ጠይቄና አስፈቅጄ እንዲሁም ስለታሪኩ አቀራረብ አውርቼ ነበር፡፡

Friday, March 23, 2012

የዝቋላ ውበቱ

ፎቶ፡ በብስራት ገብሬ (የብስራት እይታ)

Friday, October 14, 2011

ደብረ ዳሞ ን በአጭሩ

    
         በ6ኛው ክፍለ ዘመን የተቆረቆረ ገዳምና ይህ ገዳም የሚኖርበት ተራራ ስም ነው። ደብረ ዳሞ ከአዲግራት በስተምዕራብ በመካከለኛው ትግራይ ይገኛል። ከተራራው ቀጥ ብሎ ለመውጣት አዳጋችነቱ የተነሳ ወደገዳሙ ለመድረስ ከቆዳ በተሰራ ገመድ ላይ መንጠላጠል ግድ ይላል። ቤተ ክርስቲያኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥንታዊ የአሰራር ዘዴን ተከተሎ እስካሁን ዘመን ድረስ በመዝለቅ ቀደምትነት ስፍራን ይይዛል። የተሰራውም በአቡነ አረጋዊ በ6ኛው ክፍለ ዘመን እንደነበር ትውፊት አለ። ቶማስ ፓከናም የተባለው የታሪክ ተመራማሪ አምባው እንደ ወህኒና አምባ ግሸን ወንድ የነገስታት ዝርያወችን ለማሰሪያነት ያገለግል እንደነበር ትውፊት እንዳለ በጥናት ደርሶበታል።  የገዳሙ ውጫዊ ወለሎች በጥንቱ ዘመን ዘዴ፣ የኖራ ድንጋይንና የጥድ እንጨትን በማፈራረቅ የተሰራ ነበር። ይህም በስነ ህንፃ ጥበበ አክሱማዊ ዘዴ አሰራር ይባላል።
ደብረ ዳሞ መወጣጫ ጠፍር

Sunday, September 25, 2011

መስቀሉ ተገኝቷል. . .

በብስራት ገብሬ

  የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።                                                                                                                      (፩ኛ ቆሮ 1፡18)  



. . . .         የሁሉ መጀመሪያ  326 ዓ.ም. .
 . .           " መስከረም ባበባው ሠርግ በጭብጨባው ይታወቃል” ይላሉ አበው። ክረምቱ አልፎ ሜዳና ተራራው በአበባ ሲሸፈን፣አዝመራው ሲያሸት አንድም መስከረም ርዕሰ ዓውደ ዓመት፣ የዘመን መለወጫ በመሆኑ ወርኃ አደይ ወወርኃ ጽጌ ተብሏል። እናም ኢትዮጵያውያን በርዕሰ በዓልነት ታላቅ ማዕዘን ላይ ያስቀመጡት ወርኃ መስከረም፣ ኃይማኖታዊና ባህላዊ በዓላትን አቅፏል። ከነዚህም ውስጥ ከዕንቁጣጣሽ በዓል ቀጥሎ በሠፊው የሚታወቀው በዓለ መስቀል  ነው።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ለማዳን የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል ሕሙማንን በመፈወሱ ምክንያት በርካታ አሕዛብ ክርስቲያን እንዲሆኑ አስችሏል፡፡ በተአምራዊነቱና በክርስቲያኖች ዘንድ ከፍተኛ ክብር የተሰጠው በመሆኑና ይህን የተመለከቱ አይሁድ ቅዱስ መስቀሉን በአንድ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቦታ እንዲቀበር አደረጉ፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች በየቀኑ ቆሻሻ ስለሚጥሉበት ቦታው ወደተራራነት ተቀየረ፡፡ ምንም እንኳን መስቀሉን ለማውጣት ባይችሉም በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች ቦታውን ያውቁት ነበር፡፡ በሰባ ዓመተ ምሕረት በጥጦስ ወረራ ኢየሩሳሌም ስለጠፋች በዚያ የነበሩ ክርስቲያኖች ተሰደዱ፡፡ የተቀበረበትን ቦታ የሚያውቅ ባለመገኘቱ መስቀሉ ከ300 ዓመታት በላይ ተዳፍኖ /ተቀብሮ/ ኖረ፡፡
       
          ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም

       በ326 ዓ.ም. የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ ቅዱስ መስቀሉን ለመፈለግ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ አደረገች፡፡ እዚያም ደርሳ. . .

Tuesday, August 2, 2011

አስጎብኚው

አስጎብኚው
የአንድ ሀገር፣ከተማ፣መንደር፣ መነሻና ታሪክና ቅርስ፣ባህልና ትውፊት፣ወግና ስርዓት የሚዳሠስበት መድረክ ነው፡፡ በ<ብስራት እይታ> መጎብኘት አለባቸው የሚባሉትን ሥፍራዎች በሙሉ በተጠናከረ መንገድ በማቅረብ አንባቢው ከተቻለ በመሄድ ካልሆነም በቂ የሆነ መረጃ እንዲኖረው በማድረግ ጉብኝትዎን ሙሉ ማድረግ ነው፡፡


በዚህ ብሎግ ላይ ሲለሚወጡ ጽሁፎች አጭር ማብራሪያ፡-



መልዕክት
ይህ ክፍል ዋና አዘጋጁ (ብስራት ገብሬ) ያለውን እና የሚሰማውን ሃሳብ በዋነኛነት የሚያስተላልፍበት እና አንባቢያን ሊረዱት ወይም ሊያውቁት ይገባል ብሎ የሚያስበውን ሃሳብ በመልዕክት መልክ የሚያስተላልፍበት መድረክ ነው፡፡ ይህ መድረክን  ማንኛውንም የአንባብያን ጥያቄ መልስ ከአዘጋጁ የሚመለስበት የአቋም እንዲሁም የእይታ ማንጸባረቂያ ነው፡፡

እንተዋወቅ
በዚህ ዓምድ ሠዎች ሊያውቋቸው ይገባል የምላቸውን ግለሠቦች ማለትም አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ዓለም ላይ የራሳቸውን ታሪክ የሠሩትን ታዋቂ ሰዎች ከውልደታቸው ጀምሮ አሁን እስካሉበት ደረጃ ለአንባቢያን የሚቀርብበት ነው፡፡

እይታ