ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Thursday, June 7, 2012

የደጋጎች ሀገር - ማህበረ ፃድቃን ዴጌ

   ማቴዎስ ሐዋርያ ከክርስቶስ ልደት በፊት በሳባ፣በባዜንና በሮምሃይ ዘመነ መንግስት መስዋዕተ ኦሪት ይሰዋበት ወደ ነበረው ወደ እዚህ ገዳም መጥቶ ጥምቀት ይጀምራል፡፡ ያን ግዜ የነበሩ አረማውያን ሁኔታው ስላላማራቸው ሐዋርያውን በብዙ መንገድ ሊፈትኑት ከፍ ሲልም ሊገሉት ይሞክሩ ነበር፡፡ ለዚህም ምሳሌ የሚሆነው በጣም አደገኛ የተባሉ ሁለት ዘንዶዎችን እንዲበሉት ሰደውበት ካሁን አሁን ሞቶ እናገኘዋለን ብለው ሲጠብቁ ዘንዶዎቹን በመስቀል ቢባርካቸው  መልካቸው ሳይለወጥጠባያቸው እንደ በጎች ሆነዋል፡፡
እንደገና ዳግም የንጉሱ ሳባጥ ልጅ ድንገት ትሞትና ይጠራል፡፡ በያዘውም መስቀል ቢነካት ወዲያው ተነሳች፡፡ ይሄኔ አናምንም ብለው የነበሩት አረማውያን ይህንን ተአምራት አይተው አምነው ተጠመቁ፡፡


‹‹ አቴዥን ሕንደኬ›› ንግስተ ነገስታት ዘኢትዮጵያ

        
ማህበረ  ዴጌ ቤተክርስቲያ  በ39 ዓ.ም እንደተተከለ በግልፅ ተቀምጧል ፡፡ ይኸውም ‹‹መፅሐፈ ሱባዔ›› በመሪ ኤ.ኤም የተዘጋጀ መፅሐፍ ከምዕራፍ 11 በገፅ 132 ላይ ‹‹ አቴዥን ሕንደኬ›› ንግስተ ነገስታት ዘኢትዮጵያ ሆና በነገሰች በ39 ዓ.ም በአንደኛ ዓመተ መንግስትዋ ወንጌላዊ ማቴዎስ በ 40 ዓ.ም ማህበረ ፃድቃን ዴጌ ገብቶ ሲያስተምርና ሲያጠምቅ ሰምታ መኳንንትንና መሳፍንትን አስከትላ ‹‹ መርዌ›› ወረደች ይላል፡፡
በዚህም ንግስቲቱ ቅዱስ ማቴዎስን አግኝታ‹‹ እየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አብ የባህርይ ልጅ መሆኑን አውቃለሁ ይሁን እንጂ ዳግመኛ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መወለዱን አላውቅም ነበር፡፡ አሁን ግን በትምህርትህ መንፈስ ቅዱስ ስለገለፀልኝ አጥምቀኝ›› አለችው፡፡


ማቴዎስም ንግስቲቱን ካጠመቀ በኋላ መኳንንቱን፣ መሳፍንቱን ፣ የጦር ሠራዊቱን ሁሉ አጥምቋቸዋል ይላል፡፡  አያይዞም ንግስቲቱ ማቴዎስን ይዛ ወደ አክሱም ተመለሰች፡፡ ልጆቿንና ቤተሰቦቿን  አስጠመቀች፤እንዲሁም አክሎስ የሚባል ባልዋንም አምኖ ተጠመቀ በማለት ያትታል፡፡
ታሪኩ በማብራራት ሲቀጥል ቅዱስ ማቴዎስ ከዚያ በፊት ‹‹የነባብና የናግራንን›› ህዝቦች አጥምቋል ካለ በኋላ  በዚህ ጊዜ ሐዋርያው ማቴዎስ የማህበረ ፃድቃን ዴጌን ማህበር አቋቁሞ በጌታችን በእየሱስ ክርስቶስ ስም በየወሩ በ29 ቀን እየተሰበሰቡ አንዲጠጡ አድርጓል፡፡ ሲል ያረጋግጣል፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ ህዝቡን ካጠመቀ በኋላ ወዲያው ወደ እየሩሳሌም የሄደ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥምቀት ስላልተጋረሰ ከሳቴ ብርሃን አባሰላማ በአብርሃ ወኣፅብሃ ዘመነ መንግስት አክሱም ላይ ጥምቀት ጀመረ፡፡ ንጉሱም በክብር ተቀብለው ኢትዮጵያ በሙሉ ተጠመቀ ፡፡

ማህበረ ዴጌ

ማህበረ ዴጌ ማለት የደጋጎች ሀገር ነው፡፡  የደጋጎች ሀገር የተባለበት ምክንያት እኒህ ቅዱሳን ስላሉበት ነው፡፡ ገዳሙ የሚገኘው በትግራይ ክልል በአክሱም አውራጃ ከአክሱም ከተማ  ወደ ደቡብ ምዕራብ በሚወስደው መንገድ አስራ ሁለት ኪሎሜትር ያህል ርቀት ላይ ነው፡፡
በ365 ዓ.ም በአስፍሕ ወልደ አብርሃም ንጉሰ ነገስት ዘኢትዮጵያ  ዘመነ መንግስት ‹‹ ሮምያ›› ከምትባል መንደር የቅዱስ መፅሐፍ ቃል የሆነውን መሰረት 1ኛ ‹‹ ስለ ጽድቅ ብለው የሚሰደዱ ብፁአን ናቸው መንግስተ ሰማያት የነርሱ ናትና›› ያለውን 2ኛ ‹‹ አባቱንና እናቱን ሚስቱንና ልጆቹን ያልተወ ሊያገለግነኝ አይችልም›› ብሎ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን አንብበው የዚህም ዓለም ጣዕም ጥቅም ንቀው ሃገራቸውን ትተው መንነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ነበሩ፡፡
እነዚህም በአክሱም ከተማ በስተሰሜን በሐውልቱ ጀርባ ቤተ ቀጠንት በሚባል ስፍራ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ያህል እንደ ተቀመጡ በዚያም ምቾትና ድሎት ስለተሰማባቸው ለዚሁ ለዚሁማ ከሀገራችን ለምን ትተን መጣን? ስለዚህ ሱባዔ ገብተን በፆም በፀሎት ተወስነን የምንሄድበትን ቦታ በረከተ ነፍስ የምናገኝበትን ስፍራ እግዚአብሔር እንዲያሳየን እናመልክት ብለው ሱባዔ ገቡ ፆም ያዙ፡፡
ከሱባዔው በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልፃ ግማሾቹን እያንዳንዳቸው የሚኖሩበትን በዓት አመልክታቸው በዚያም በጾምና በፀሎት ፀንተው እንዲኖሩ ነገረቻቸው፡፡
ሶስት ሺህ/3000/ ያህሉ ደግሞ ከላይ ወደጠቀስነው ሄዱ፡፡ ከነርሱ የተቀሩት ደግሞ ወደ ቆየፃ ሓባር ፣ተድባ፣ አኮርየን፣ ተንስሓ፣ደብረ አንሳ ወደ ተባሉ ቦታዎች ሄደዋል፡፡
ተጨማሪ ሶስት ሺ ደግሞ እዚያ ከነበሩት ጋርም ተደመሩ፡፡ ከዚያም የቅዱስ ጳውሎስና የቅዱስ ዮሐንስ መመሪያ ተከትለው ማለት ‹‹ከሁሉ ፍቅር ይበልጣል›› የሚለውን ጠብቀው በእምነት በፍቅር በአንድነት ፀንተው በየሳምንቱ እሁድ እሁድ ተዝካረ ሰንበትን ጠብቀው ማህበር ሲጠጡ ጀመሩ፡፡
የማህበረ ዴጌ ታሪክም ተቀየረ ፡፡ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በአምሳለ ነዳይ ድሀ መስሎ በመካከላቸው ተገኘ፡፡  ከነርሱ ጋርም አንድ ማህበርተኛ ሁኖ እንዲታወቅ ጠየቃችው፣ እነርሱም ፈቀዱለት እና አንዱ የማህበሩ አባል ሆነ፡፡ አንድ ዓመት ከስድስት ወር ያህልም ከነርሱ ጋር ሳይለይ ቆየ፡፡ በዚሁ ጊዜ ‹‹ እስቲ ለኔም ተራ ስጡኝ እንደአቅሜ ዝክር ላውጣ፡፡›› አላቸው፡፡በዚህ ግዜ ግን ድህነቱን አይተው ‹‹ አይሆንም አንተ ድሀ ነህ ከኛ ጋር ሁነህ በዓሉን አክብር እንጂ ምን አለህና ነውን የምትደግሰው ይቅርብህ ›› አሉት፡፡ እርሱም ‹‹ አይሆንም ስጡኝ እንጂ›› አላቸው እነርሱም ካልክማ ብለው ቀን ወስነው ሰጡት፡፡ ቀኑም ጥር 29
ነበር፡፡
ጌታ ዘወትር በሚቀመጥበት ድንጋይ









ከማህበርተኞቹ መካከል ‹‹ ሣይዳን ›› የሚባል ሰው ነበር፡፡ ይህም አሳላፊ ወይም ሙሴ ነበር፡፡ ይህም ሰው እንግዳና ድሀ ሰው ፈፅሞ አይወድም ነበርና ጌታችንም ከማህበርተኞቹ መካከል ሲገኝ ደሀ መስሎ ስለነበር በጣም ይጠላው ነበር፡፡አንድ ዓመት ከስድስት ወር ከነርሱ ጋር ሲቀመጥም አንድ ቀን ስንኳ አንድ ዋንጫ የወይን ጠጅ ሰጥቶት አያውቅም ነበር፡፡ የሆኖ ሆኖ መድረሱ አልቀረም የጌታችን ማህበር ደረሰ፡፡ እንደማህበሩ ስርዓት የወይን ጠጅ የሚጠመቅባቸውን ጋኖች የሚያጥበው ሙሴው/አሳላፊው/ ነው፡፡ ስለሆነም በስርዓቱ መሰረት ጌታችን ሙሴውን  ጠርቶ ጋኖችን እጠብልኝ አለው፡፡ አሳላፊውም በቁጣ  ‹‹ አንተ ቤትህ የማይታወቅ፤ ከየት አምጥተህ ማህበር ልታደርግ ነው አንተ ብሎ›› አናንቆ አልታዘዝህም ብሎ ሄደ፡፡ ይህን የተመለከተው ጌታም አንድ እረኛ ጠርቶ ‹‹አንተ ልጅ ከብቶችህን እኔ እጠብቅልሃለሁና በዚህ ውሀ አምጣልኝ›› አለው፡፡ ትንሹ እረኛ ልጅ ገምቦውን ይዞ ትንሽ ወጣ እንዳለ ጌታ ዘወትር በሚቀመጥበት ድንጋይ ላይ ሆኖ ዘንጉን ወደ ልጁ አቅጣጫ ወረወረው፣ ዘንጉንም ከልጁ ፊት ሂዶ ተተከለ፡፡ ልጁንም ጠርቶ ዘንጉንም እንዲቀለው አዘዘው፡፡ ልጁም እንደታዘዘው ዘንጉንም ቢነቅለው ውሀ ፈለቀ፡፡ ከርሱ ቀድተህ አምጣልኝ አለው፡፡ ልጁም ከዚህ ውሀ ቀድቶ አመጣለት ጋኖቹን አጠባቸው፡፡

በበዓሉ ቀን ማህበርተኞቹ ምን ሊያበላን ነው፣ምን ሊያጠጣን ነው ሳይሉ ሁሉም ተሰበሰቡ፡፡ ጌታችንም በፊታቸው ጋኖቹን ቢባርካቸው የወይን ጠጅ ሞልተው ተገኙ፡፡

ቀድቶ ቢሰጣቸውና ቢቀምሱትም በጣም ግሩም ጣፋጭ ስለነበር እጅግ አደነቁ፡፡ እነርሱም ጌታን ከፃድቃን አንዱ ስለመሰላቸው ከእግሩ ላይ ወድቀው እስካሁን ድረስ ሳንበድልህ አልቀረንምና ይቅር በለን ብለው ለመኑት፡፡ ተነሱ ብሎ ካስነሳቸው በኋላ እናንተ ምንም አልበደላችሁም የጠየኳችን እድርጋችኋል የበደለኝ ግን አሳላፊያችሁ ነው በማለትና አንድም  ቀን ስንኳ አንድ ዋንጫ የወይን ጠጅ አልሰጠኝምና አፋራርዱኝ አላቸው፡፡ ነገር ግን ሙሴው/አሳላፊው/ የማያፍር ደፋርና ርጉም ስለነበር ‹‹ ይህ ሰው ጌታችን በልቶ አልበላሁም ፣ ጠጥቶ አልጠጣሁም የሚል ስለሆነና ስለማይጠግብ ነው እንጂ እንዲያውም ለናንተ አንድ አንድ ዋንጫ ሲሰጣችሁ ለእርሱ ሁለት ሁለት ነበር የሚሰጠው ብሎ የሐሰት ቃል መለሰ፡፡
ጌታችንም እንግድያስ እኔ የጠጣሁበት ዋንጫ ትቅረብና ትመስክርብኝ አለው፡፡ በዚሁ ተስማምተው አሳላፊው/ሙሴው/ሄዶ አንድ ሸራፋ ዋንጫ አምጥቶ በዚህ ነበር የሚሰጠውና የሚጠጣው ብሎ አቀረበ፡፡ዋንጫዋም ከተቀመጠችበት አንድ ክንድ ከስንዝር ተነስታ ፅዋይቱን ስትመሰክር 
‹‹ ዓለማትን የፈጠረ አምላክ ምስክሬ ነው እኔ የያዝኩትን የወይን ጠጅ ዕቃ ሙሴም በእጆቹ አለያዝኩትም በከንፈሩ አልነካኝም በሌሎቹ ሰዎች እጅ ግን ተይዤ ያየን ነበር ›› አለች ያን ጊዜ እንደ ዳታን እና አቤሮን ምድር ተከፈተችና ሙሴውን ከነልጁ ዋጠቻቸው፡፡  

ማኀበረ ፃድቃንም ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ መሆኑ ተረድተው እንደገና ከእግሩ ወድቀው ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ለመኑት ፡፡ ቀኑም ጥር 29 ነበር፡፡  ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ይቅርታ ካደረገላቸው በኋላ ስማችሁ የጠራ በስማችሁ ተዝካር ያወጣ በስማችሁ ድሆችን የረዳ፣ ያለበሰ፣ ያጎረሰ፣ የሰጠ፣ የመፀወተ፣ ቤተ ክርስትያኖች  የሠራ ያሠራ፣ እሰከ 14/ እስከ አስራ አራት ትውልድ ደረስ ምሬላችኋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣቸው፡፡ ይህችን ቦታችሁ መጥቶ የሳመ እየሩሳሌም እንደሳመ አድርጌላችኋሁ አላቸው፡፡
በኦሪት ሔኖክ፣ ዕዝራ፣ ኤልያስ፤ በሐዲስ ኪዳንም እነ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድና በየጊዜውም እንደሚሰወሩ ቅዱሳን እንደዚሁም ጌታችን እነዚህን የማኀበረ ዴጌ ፃድቃንንም ከሞት ተሰወሩ ብሎ በበነጋታው ጥር 30 ቀን ሠውሮአቸዋል፡፡

በዚህም መሰረት ይህ ታላቅ በዓል ሆኖ ዛሬም በየዓመቱ ጥር 30 ቀን በደማቅ ሁኔታ ሲከበር ይኖራል፣ ይከበራልም፡፡ 


ይህን ታሪክ የምታነቡ ሁሉ አሁንም ስለታሪኩ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የሚያስረዱ በዓይን የሚታዩ በእጅ የሚዳሰሱ ተአምራት የታየባቸውና የተደረገባቸውም ሁሉ በቅርስነት ተጠብቀው በዚህ ገዳም ይገኛሉ፡
እነርሱም

1.     ጌታችን የተቀመጠበትንና የቆመበትን ድንጋይ ከነምልክቱ
2.    ምስዋሮም የሚባል ፃድቃኑ የተሰወሩበትን ስፍራ
3.    ከድንጋይ ላይ ሁኖ ወርቅ ዘንግ ወርውሮ ያፈለቀው ማየ ፀሎት ማየ ዮርዳኖስ ብሎ የሰየመው
4.    ቁመት ጨምራ ከመሬት ተነስታ እንደ ሰው አፍ አውጥታ የመሰከረችው ዋንጫ
5.    ፃድቃኑ ሲወቅጡበት የነበረው የድንጋይ ሙቀጫ
6.   በማህበራቸው ጊዜ ሲደግሱባቸው የነበሩ የድንጋይ ገበታዎች
7.    ከሀገራቸው ከሮም ያመጡት ባለመስታወት ቋሚ ዕፀ መስቀል፡፡
8.    ርዕሰ ዮሐንስ የሚባል ነገስታት ከነዘውዳቸው ጳጳሳት ከነአክሊላቸውና ከነመስቀላቸው በዚያን ጊዜ      የተሳሉበት ስዕል፡፡
9.   ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌላዊ በማህበረ ፃድቃን ዴጌውን ሆኖ ያስተማረበትና የጠመቀበትን በስዕል የሚያሳይ፡፡
10.  ይህ ገዳም በአፄ ካሌብ ዘመነ መንግስት እንደተገደመና ገዳሙ ራሳቸው የገደሙት የራሳቸው መሆኑን በአክሱም መፅሐፍ ክብረ ነገስት ተፅፎ እንደሚገኝ በታሪኩ ተረጋግጦ ተላልፎልናል፡፡
ይህን ገዳም ለማየት የሚፈልግ ሁሉ ሂዶ ማየት የሚችል መሆኑን በዚሁ ፅሑፍ እንገልፃለን፡፡
  እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡ 





10 comments:

  1. Kale heyweot yasemalen E/R yestelen .

    ReplyDelete
  2. kale hiywetin yasemalin wendmimachin ke abatochachonn bereket yikfelen

    ReplyDelete
  3. sile gedamu endew bewore esema nebre, betam new yemamesegenew heje ayewalehu betam mirt bota new God bless u bisrat
    you are doing great

    ReplyDelete
  4. Dear Bisrat i really appreciate your effort as well as perspective.But i have one question - how is it possible to be sure about this history of 'Mahebere doge' ? is their any primary source or any historical evidence than what u have stated above ? Because in Ethiopia their are a lots of oral traditions with no historical legible evidence. But i don't mean that the miracles are not true rather my question is on the historical truth.As a christian i believe that the above are very easy for our Lord but miracle and history is quite different.If the history is not true the miracle goes on like that .

    M.MOI

    ReplyDelete
  5. thank you a lot. God bless you.

    ReplyDelete
  6. እግዚአብሔር ዕድሜና ጤና ሰጥቶ ከዚህ በላይ የምትሰራበትን ጥበቡን ምስጢሩን ይግለፅልህ፡፡
    ቃለ ሕይወት ያሰማልን ወንድማችን!!

    ReplyDelete
  7. kale heywet yasemalen egziyabher yabertahe

    ReplyDelete
  8. THANKS FOR SHARING, I'VE HAD THE CHANCE TO VISIT THE PLACE A YEAR AGO. ITS QUITE AMAZING THAT NOTHING HAS BEEN SAID ABOUT SUCH A PLACE WITH A GREAT HISTORY.

    ReplyDelete
  9. kale hiwot yasemalen

    ReplyDelete
  10. ከክርስቶስ ልደት በፊት ጥምቀት ነበረ እንዴ?

    ReplyDelete