ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡
Showing posts with label ቤተ-እምነት. Show all posts
Showing posts with label ቤተ-እምነት. Show all posts

Monday, September 9, 2013

አንተ ነህ መስከረም

                                                            በገብረክርስቶስ ደስታ

ማለቂያ በሌለው ደማቅ ሰማያዊ፣
ከሩቅ ያለው ጋራ ተነክሮ ሐምራዊ፡፡
በዚያ ላይ ደመናው እንደ ጥጥ ተነድፎ፣
እየተራራቀ ሲያንጃብብ ተቃቅፎ፡፡
አንተ ነህ መስከረም፣
የሐምሌን ጨለማ የነሐሴን ዝናም፣
የሻርከው አንተ ነህ፣
በብርሃን ውበትህ፡፡
በክረምቱ ወራት ሰማዩን ያስጌጠው፣
የማርያም መቀነት በቀለም ያበደው፡፡
ጤዛው አርሶታል መሬቱ ላይ ለቆ፣
በቀይና ብጫ መስኩ ተለቅልቆ፡፡
ወንዝና ጅረቱ ድንጋይና አፈሩ፣
ሀገሩ ውብ ሆኗል ሜዳው ሸንተረሩ፡፡
ዕንቁጣጣሽ አንተ ስጦታህ የበዛ፣
ለሰው መታሰቢያ ውበት የምትገዛ፡፡

Thursday, July 25, 2013

የብስራት እይታ Bisrat Gebre's View: የገብርኤል ድርሳን ፡ ሐምሌ

የብስራት እይታ Bisrat Gebre's View: የገብርኤል ድርሳን ፡ ሐምሌ:   
                                  ‹‹ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ ››
                                                                                     ሉቃስ 1፡ 19      

           ሹም እለእስክንድሮስ ጭፍሮቹን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፡፡  ሰም፣ጨው፣ ባሩድ፣ሙጫ፣የዶሮ፣ ማር፣እርሳስ፣ ብረትን፣ ቅንጭብ፣ ቁል...

ሙሉውን ለማንበብ ከፈለጉ - "ይጫኑኝ"

Monday, April 29, 2013

ሆሣዕና በአርያም …!!!


ፀሐፊ ፡- ፍቅር ለይኩን፡፡
READ IN PDF


         ‹‹ሆሣዕና›› ቃሉ የዕብራይስጥ ሲሆን ትርጓሜውም ‹‹አሁን አድን›› ማለት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ከፋሲካ በፊት ያለው እሁድ የሆሣዕና እሁድ በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ ዕለትም በቤተ ክርስቲያን የሚዘመረው መዝሙር፣ ማኅሌቱ፣ ቅዳሴውና ማንኛውም መንፈሳዊ አገልግሎት ዕለቱ በታላቅና እጅግ ደማቅ በሆነ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት የሚዘከርበት ነው፡፡ ይህ በዓል እጅግ በደማቅና ልብን በሚመስጥ መንፈሳዊ ሥርዓትና ድምቀት ከሚከበርባቸው ቅዱሳን ገዳማትና መካናት መካከል የአክሱሟ ርዕሰ አድባራት ጽዮን ማርያም እና በዚህ በአዲስ አበባችን ደግሞ የእንጦጦ ማርያም በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ሆሣዕና የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ወደ ኢሩሳሌም በታላቅ ድል የገባበት ዕለት ነው፡፡ አስቀድሞ በመጽሐፍ ቅዱስ በነቢዩ ዘካርያስ፡- ‹‹ለጽዮን ልጅ፡- እነሆ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያቱ ግልገል በውርንጭላይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት፡፡›› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ፡፡ ጌታ፣ አምላክና መድኃኒት የሆነው ኢየሱስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡

Thursday, July 26, 2012

የገብርኤል ድርሳን ፡ ሐምሌ

  
‹‹ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ ›› ሉቃስ 1፡ 19

       ሹም እለእስክንድሮስ ጭፍሮቹን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፡፡  ሰም፣ጨው፣ ባሩድ፣ሙጫ፣የዶሮ፣ ማር፣እርሳስ፣ ብረትን፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨመሩበት፡፡ ጭፍሮችም ያዘዛቸውን ፈፅመው መጥተው ያዘዝከንን ሁሉ ጨምረንበት ነዶ ፈልቷል አሉት፡፡ ድምፁም እንደ ነጎድጓድ ይሰማል፤ ወላፈኑም እንደ ፀሐይ ያንፀባርቃል፡፡
የፍላቱም ኃይል አስራ አራት ክንድ ያህል እየዘለለ ይወጣል፡፡ በውስጡ የሚጣሉትን ሰዎች እዘዝ፡፡ ያንጊዜም ህፃን ቂርቆስንና እናቱን ኢየሉጣን ይዘው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡ በክርስቶስ ስም ስላመኑ በእስር ቤት አግብተው አስረዋቸው ነበርና ፍላቱ ወደ ላይ በሚዘል በብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው በዚያን ጊዜም እልፍ ከአንድ ሺህ አራት መቶ ሰዎች እንዲወጡና በፈላው የብረት ጋን ውስጥ የቅዱሳንን አሟሟት እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፡፡

Tuesday, January 17, 2012

የገና በዓልና አከባበሩ


"ታኅሣሥ ገሠገሠ ከተፍ አለ ገና፣
እጠብቅሃለሁ አንተ ልጅ ቶሎ ና፡፡
የታኅሣሥ ትውውቅ የገና ፍቅር፣
ይላል ቅር ቅር፡፡"
           ዓመት ጠብቀው፤ ዐውደ ዓመትን ዙረው ከሚመጡት በዓላት አንዱ የገና (ልደት) በዓል ነው፡፡ በያመቱ ታኅሣሥ 29 ቀን ይከበራል፡፡ "ዮም ተወልደ ቤዛ ኵሉ ዓለም" (ዛሬ የዓለም ቤዛ ተወለደ) እያሉ ኢትዮጵያውያኑ በደማቅ ሥነ ሥርዓት በዓሉን ያከብራሉ፡፡ ይህን በዓለ ልደት ለማክበር በመንፈቀ ኅዳር የጀመሩትን ጾም ለ43 ቀኖች አሳልፈዋል፡፡
"ያለም ሁሉ መድኃኒት
ተወለደ በበረት፣
እያሞቁት እንስሳት
ብርሃን ሆነ በዚያች ሌት
ሲዋዥቡ መላእክት
ደስ አሰኙ ለኖሩት" የሚለው ኅብረ ዝማሬ የበዓሉ መገለጫ ነው፡፡
ልደት የእምነታችን መክፈቻ በር
ቤተ ክርስቲያን የክርስቲያኖችን መንፈሳዊ ሕይወት ከዕለት ዕለት በጋለ ሁኔታ ለማሻሻል እንዲረዳ በዓመቱ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ በዓላትን ታከብራለች ከእነዚህም በዓላት በጣም በደመቀ ሁኔታና በታላቅ ደስታ የሚከበረው የልደት በዓል ነው፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት የክርስቶስ ልደት የእምነታችን መክፈቻ በር በመሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪም  በየትኛውም የዓለም ክፍል አዲስ ህፃን ተወልዶ ወደ ህብረተሰቡ በሚቀላቀልበት ጊዜ የሚኖረው ደስታና ፈንጠዝያ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡ የህፃኑም ልደት በየዓመቱ በሚከበርበት ጊዜ በመጀመሪያ የቤተሰቡ ከዚያም የወዳጅ ዘመድና የጓደኛ ደስታ ፍፁም ልዩ ነው፡፡ ለዚህም ነው የክርስቶስ ልደት በክርስቲያን ቤተሰቦች ዘንድ በትልቅ ጉጉትና ደስታ የሚጠበቅ ልዩ ቀን የሆነው፡፡

Sunday, November 13, 2011

መዝሙርና ዘማርያን. . .

  • እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ከሰጠው ታላቅ ጸጋ መካከል የመዝሙር አገልግልት አንዱ ነው፡፡
  • በቤተክርስቲያን ትምህርት ለቅዱሳን ከሚሰጡ አስሩ ማዕረጋት ሶስተኛው ጣዕመ ዝማሬ ይባላል
           የመዝሙር በአጋጣሚ የተጀመረ ሳይሆን ከአምላክ የተሠጠ የአገልግሎት ፀጋ ነው፡፡ የሠው ልጅ መዝሙርን የተማረው የተማረው ከመላዕክት ነው፡፡ የመላዕክት እንጀራ ምስጋናቸው ነው፡፡ “የመላዕክትን እንጀራ የሠው ልጅ በላ” ተብሎ ተፅፏል፡፡ይህ ማለት መላዕክት የሚበሉት እንጀራ የሚጠጡት መጠጥ አላቸው ሳይሆን የሠው ልጅ የቅዱሳን መላዕክትን ምስጋና ለማመስገን መፈጠሩን ማስረጃ ነው፡፡ቅዱሳን መላዕክት ለፈጣሪያቸው የሚቀርቡት ምስጋና ምግብ ሆኖአቸው ያለማቋረጥ ሲያመሰግኑ ይኖራሉ፡፡
ህዝበ እስራኤል ከምድረ ግብፅ ከባርነት ነፃ ለመውጣት ባህረ ኤርትራን በደረቅ በሚሻገሩ ጊዜ ይከተላቸው የነበረው ፈርኦንና ሠራዊቱ በፈረሶቻቸው ላይ እንዳሉ ባህረ ኤርትራ ተከድኖባቸው በሚጠፉ ግዜ ይህን ያየችው ማርያም እኅተ ሙሴ ከህዝቡ ጋር ከበሮ ይዛ በህብረት “. . .በክብር ከፍ ከፍ ብለሃልና ለእግዚአብሔር እንዘምራለን. . . ” በማለት ለፈጣሪያቸው የአንድነት ዝማሬ አቅርበዋል፡፡ ዘፀ.
፲፭፣፩-፳፩ ሊቀ ነቢያት ሙሴም ለእስራኤል ልጆች በተለያየ ጊዜያት መዝሙር ያስተምራቸው ነበር፡፡
በእስራኤል  ላይ ስትፈርድ የነበረችው ነብይቱ ዲቦራ “. . .እኔ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ፤ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔርም እዘምራለሁ . . . ” በማለት የዘመረችው መዝሙር ማህሌተ ዲቦራ በመባል ይታወቃል፡፡ መሳ.፭፤፩-፴፩ ቅዱስ ዳዊትም በእሰራኤላውያን ዘንድ ከጥንት ጀምሮ የነበረውን የመዝሙር ሥርዓት ወስኖ ሁለት መቶ ሰማንያ መዘመራንን መድቦ መዝሙሩን በተለያየ ግዜ ከፈፍሎ እንዲዘምር ከማድረጉም በተጨማሪ እራሱም በገና እየደረደረ በቤተ መቅደስ ያገለግል ነበር፡፡ የነብዩ ዳዊት ልጅ ሠለሞንም ከመዝሙራት ሁላ የሚበልጥ መዝሙር “መኃልየ መኃልየ ዘሰለሞን” የተባለውን ዝማሬ ይዘምር ነበር፡፡
የዘማሪ ይልማ ኃይሉ የመዝሙር ካሴት ሽፋን
በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በቤተልሄም ተወልዶ ባዩት ጊዜ ተለያይተው የነበሩ ሰውና መላእክት በአንድነት ዘምረዋል፡፡መዝሙር በዕለተ ሆሳዕና የቢታንያን ድንጋዮች ያዘለለ፤ጡት የሚጠቡ ህጻናትን ሳይቀር ለምስጋን ያነሳሳ ታላቅ የአገልግሎት ጸጋ ነው፡፡ቅዱሳን ሐዋርያትም ሐሙስ ማታ በአላዓዛር ቤት መቅደስ ቁርባንን ከተቀበለ በኋላ በአንድነት ዘምረዋል፡፡ማቴ ፳፮፤ ፴ ፡፡ በቤተክርስቲያን ትምህርት ለቅዱሳን ከሚሰጡ አስሩ ማዕረጋት ሶስተኛው ጣዕመ ዝማሬ ይባላል፡፡ከጣዕመ ዝማሬ ማዓረግ የደረሱ አበው ሳያቋርጡ ሳይሰለቹ ለፈጣሪያቸው ምስጋና ያቀርባሉ፡፡
         
መዝሙር የሚለው ቃል”ዘመረ” አመሰገነ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም ምስጋና ማለት ነው።መዝሙር በቤተ ክርስቲያን የዝማሬ ሥርዓት መሠረት በዜማ የሚቀርብ ምስጋና ነው፡፡ ምስጋና የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ እግዚአብሔር ክብሩ በባሕሪው ብቻ እንዲይቀር ስሙን እንዲቀድሱ ክብሩን እንዲወርሱ መላእክትንና ሰውን አስተዋይና አዋቂ አድርጎ ፈጥሮአቸዋል ፡፡ከቅዱሳን መላዕክት ወገን የነበረው ሳጥናኤል ያልተሰጠውን አምላክነት በመሻቱና ምስጋና እንዲቀርብለት በመፈለጉ ከክብሩ ተዋርዷል። ሕዝ.፳፰፡፲፫ በእርሱም ፈንታ እግዚአብሔርን የሚያመሰግን እጅግ ያማረና የከበረ ሰው ተፈጥሮአል። መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ ፪፡፲፪ "እንዳንተ ካለ ሠራዊተ መላእክት ሁላ ይልቅ ራስህን አኩርተሃልና ስለ ትዕቢትህ እግዚአብሔር ከናቃቸው ከሰራዊቶችህ ጋር አንተ ስለምታመሰግነው ምስጋና የእግዚአብሔርን ምስጋና ያመሰግኑ ዘንድ አዳምን ከልጆቹ ጋራ ፈጠረው” በማለት የሰው ልጅ የተፈጠረበትን ዓቢይ አላማ ይገልጻል፡፡ ቅዱስ ዳዊትም “እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፤ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው”፡፡በማለት የሰው ልጅ ያለማቋረጥና መሰልቸት ፈጣሪውን ማመስገን እንደሚገባው ተናግሯል፡፡መዝ ፴፫፤፩ ፡፡እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ከሰጠው ታላቅ ጸጋ መካከል የመዝሙር አገልግልት አንዱ ነው፡፡
      
          
ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር የቱ ነው? እንዴትስ መቅረብ አለበት?

   * . . . ኢየሱስ ጓዴ ነው
   

Friday, October 14, 2011

ደብረ ዳሞ ን በአጭሩ

    
         በ6ኛው ክፍለ ዘመን የተቆረቆረ ገዳምና ይህ ገዳም የሚኖርበት ተራራ ስም ነው። ደብረ ዳሞ ከአዲግራት በስተምዕራብ በመካከለኛው ትግራይ ይገኛል። ከተራራው ቀጥ ብሎ ለመውጣት አዳጋችነቱ የተነሳ ወደገዳሙ ለመድረስ ከቆዳ በተሰራ ገመድ ላይ መንጠላጠል ግድ ይላል። ቤተ ክርስቲያኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥንታዊ የአሰራር ዘዴን ተከተሎ እስካሁን ዘመን ድረስ በመዝለቅ ቀደምትነት ስፍራን ይይዛል። የተሰራውም በአቡነ አረጋዊ በ6ኛው ክፍለ ዘመን እንደነበር ትውፊት አለ። ቶማስ ፓከናም የተባለው የታሪክ ተመራማሪ አምባው እንደ ወህኒና አምባ ግሸን ወንድ የነገስታት ዝርያወችን ለማሰሪያነት ያገለግል እንደነበር ትውፊት እንዳለ በጥናት ደርሶበታል።  የገዳሙ ውጫዊ ወለሎች በጥንቱ ዘመን ዘዴ፣ የኖራ ድንጋይንና የጥድ እንጨትን በማፈራረቅ የተሰራ ነበር። ይህም በስነ ህንፃ ጥበበ አክሱማዊ ዘዴ አሰራር ይባላል።
ደብረ ዳሞ መወጣጫ ጠፍር

Saturday, July 9, 2011

Christianity in Ethiopia

Christianity in Ethiopia


The Ethiopian Orthodox Union church, an autonomous Christian Church headed by a patriarch and closely related to the Coptic Church of Egypt, was the state church of Ethiopia until 1974. About 62.8 percent (Orthodox 43.5%, Protestant 18.6% and Catholic 0.7 %) of the people of Ethiopia are Christians, and Christianity is predominant in the north. All the southern regions have Muslim majorities, who represent about 33.9 percent of the country's population.

Saturday, June 25, 2011

ዘማሪ እስጢፋኖስ ሣህሌ (ቄሴ) ምእመኑን ይቅርታ ጠየቀ::

ዘማሪ እስጢፋኖስ ሣህሌ (ቄሴ) ምእመኑን ይቅርታ እየጠየቀ ነው
(ደጀ ሰላም፤ ጁን 24/2011)፦


“እኛ የአባቶችን አገልግሎት ለማስረሳት ሠራን፤ የእነርሱም ኀዘን እኛን ጣለን፡፡›› (እስጢፋኖስ ሣህሌ)
በተለያዩ አህጉረ ስብከት ሕገ ወጥ ሰባክያንንና እና ዘማርያንን የመከላከሉ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፤
በጋሻው ደሳለኝ “በቪሲዲ የተሰራጨብኝ ማስረጃ በአኒሜሽን የተቀናበረ ነው!!›› አለ
በቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ዋዜማ በሜጋ - ሞያሌ መንገድ የመኪና አደጋ የደረሰባቸው ምርትነሽ ጥላሁን እና አሰግድ ሣህሉ በሕክምና ላይ ናቸው
በደብረ አሚን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ወጣቶች ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም የአካላዊ ቅጣት ርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል አንዱ የነበረው ዘማሪ እስጢፋኖስ ሣህሌ (በቅጽል ስሙ ቄሴ)

Sunday, June 5, 2011

ሕገ ወጥ ሰባክያንና ዘማርያን በደብረ አሚን ተ/ሃይማኖት የከረረ ተቃውሞ ገጠማቸው...

ደጀ ሰላም Deje Selam: ሕገ ወጥ ሰባክያንና ዘማርያን በደብረ አሚን ተ/ሃይማኖት የከረረ ተቃውሞ ገጠማቸ...: "To Read, Print and Share this Message, click HERE (PDF) . ይህንን መልእክት በPDF ለማንበብ፣ ለማተም እና ለሌሎች ለማዳረስ ይህንን ይጫኑ። የደብረ አሚን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ..."