ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Friday, October 14, 2011

ደብረ ዳሞ ን በአጭሩ

    
         በ6ኛው ክፍለ ዘመን የተቆረቆረ ገዳምና ይህ ገዳም የሚኖርበት ተራራ ስም ነው። ደብረ ዳሞ ከአዲግራት በስተምዕራብ በመካከለኛው ትግራይ ይገኛል። ከተራራው ቀጥ ብሎ ለመውጣት አዳጋችነቱ የተነሳ ወደገዳሙ ለመድረስ ከቆዳ በተሰራ ገመድ ላይ መንጠላጠል ግድ ይላል። ቤተ ክርስቲያኑ በኢትዮጵያ ውስጥ ጥንታዊ የአሰራር ዘዴን ተከተሎ እስካሁን ዘመን ድረስ በመዝለቅ ቀደምትነት ስፍራን ይይዛል። የተሰራውም አቡነ አረጋዊ 6ኛው ክፍለ ዘመን እንደነበር ትውፊት አለ። ቶማስ ፓከናም የተባለው የታሪክ ተመራማሪ አምባው እንደ ወህኒ አምባ ግሸን ወንድ የነገስታት ዝርያወችን ለማሰሪያነት ያገለግል እንደነበር ትውፊት እንዳለ በጥናት ደርሶበታል።  የገዳሙ ውጫዊ ወለሎች በጥንቱ ዘመን ዘዴ፣ የኖራ ድንጋይንና የጥድ እንጨትን በማፈራረቅ የተሰራ ነበር። ይህም በስነ ህንፃ ጥበበ አክሱማዊ ዘዴ አሰራር ይባላል።
ደብረ ዳሞ መወጣጫ ጠፍር
እዚህ አምባ ላይ የሰውም ሆነ የእንስሳ ሴቶች መውጣት አጥብቆ የተከለከለ ነው። ሆኖም ግን በግራኝ አህመድ ወረራ ወቅት ንግስት ሰብለ ወንጌል እና ደንገጡሮቻ እዚህ አምባ ላይ በመጠለል ከሞት ድነዋል። ተራራው ላይ ምንጭና እህል የሚዘራበት ሰፊ መሬት ስለነበር ፖርቱጋሎቹ እነ ክራስታቮ ደጋማ ከአምባው ደርሰው ንግስቲቱ እንድትወርድ እስከአሳመኗት ድረስ የግራኝን ሰራዊት ከዚህ አምባ ላይ ሆና መከላከል ችላለች።
ደብረ ዳሞ አምባ ከሩቁ - ምኩራቡ በሁሉም አቅጣጫ አንድ አይነት ኩርባ ያለው የተፈጥሮ ቅጥር ነው


ደብረ ዳሞ ገዳም በጥንታዊ የህንጻ አሰራር ዘዴ-
ደብረ ዳሞ ቤተክርስቲያን

ምንጭ ፡-ውክፔድያ 

4 comments:

 1. this is good information and nice pic God bless ur job

  ReplyDelete
 2. የእግዚያብሔር ሠላምታ ብስራት

  በድህረ ገፅህ በግራ በኩል ታች ያስቀመጥከውን ሙዚቃ አጥፋው:: ትንሽ ማስተላለፍ ከምትፈልጋቸው መንፈሣዊ ፅሁፎች ጋ ይጋጫል::

  በተረፈ በርታ

  ReplyDelete
 3. ወልደሊባኖስ አበርሄFebruary 8, 2012 at 1:56 PM

  እግዚአብሔር ረዥም ዕድሜና ጤና እንዲሰጥህ እመኛለሁ። በተለይ የተሀድሶ መናፍቃን ስለ ማጋለጥ ቀጥሉበት።

  ReplyDelete