ጠላ
(የጣና እና የሸዋ በር ሠፈር ወግ)
ፈጣሪ ተመስገን..
መሬትን ሰጠኸን
ማሽላ ፤ዳጉሳ እንድንዘራ ገብስን
ዘሩን በተንክልን፤
ፈጣሪ ተመስገን..
ስለገለጥክልን የጠላ ጥበብን
በጠላ ተጠምቀን
ተረጋጋን ደግሞ በሀሴት ተሞልተን፡፡
በል ተቆላ ገብስ
ተቃጠል በእሳት ፤ በምጣድ ላይ ታመስ
የኑሮዬ ምስ፡፡
ይጠመቅ ያ ጠላ
ዋንጫዬ ይሞላ፤
ደጋግሜ ልጋት
የቀኑን ስንክሳር፤እንዳላይ በሌት
የቀትሩ ልክፍት፤እንዳይሆን ቅዠት
ልጠመቅ በጠላ፤ ባሻሮ ዋግምት፤
እዋንጫው ውስጥ ጠልቀህ
ሳይጠብህ ተስፋፍተህ
በአሻሮ ሽረህ
በጠላ እግረሙቅ አእምሮህን ታስረህ
እረፍ በነጻነት፤ ልሳህን ዘግተህ፤
ይኼኔ ነው እረፍት
ይኼኔ ነው እረፍት
ጭው ብለህ ገብተህ፤ ተእንቅልፍ ጽልመት፡፡
ደግሜ ደግሜ እንድልህ ተመስገን
ቀኑንም ባርክልን
አርገው የሁላችን፡፡
ጠላ ካልተጠጣ ተመስገን አይባልም እንዴ
ReplyDeleteእግዚብሔር ቅድስት ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን። በርቱልን ውድ የቤተክርስቲያን ልጆች።
ReplyDeleteI don't like the color composition of the site. Please try to learn from Daniel views and Adababaye.Black is heavy color to stay with for most of us.
ReplyDelete