ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Sunday, April 22, 2012

በማደግ ላይ ያለ

      አዲስ ዓይነት ይዘት፣ በቀለማት ያሸበረቀና በማደግ ላይ ያለ አዲስ ዓይነት ድረ ገፅ- ‹‹የብስራት እይታ››  ከብዙ አንባቢያን በደረሰኝ አስተያየት ድረ ገፁ ከሚነበቡና ከሚታዩ ነገሮች በተጨማሪ የሚሰሙ ነገሮች ቢኖሩ ጥሩ እንደሚሆንና ተመራጭ ሊያደርገው እንደሚችል ነው፡፡ ይህንን በማየት በድምፅና በምስል የተቀረፁ መንፈሳዊ መዝሙሮች በድረ-ገፁ ላይ መጫኑንና ማዳመጥ የምትችሉ መሆኑን በትዕትና እገልፃለሁ፡፡
‹‹የብስራት እይታ›› መለያ( Logo) 


ይህ ብቻ ሳይሆን ከመዝሙር በተጨማሪ ዘፈኖችን ማዳመጥ ለምትሹ ቆየት ያሉና ተወዳጅ ናቸው ያልኳቸውን ዘፈኖችንም እንዲሁ አካትቻለሁ፡፡ አሁን ‹‹የብስራት እይታ ››የሚያነቡት ብቻ ሳይሆን የሚያዩት የሚሰሙትም ሆኗል፡፡ የፈለጉት ያንብቡ የፈለጉትን ያዳምጡ፡፡

 እዚህ ላይ ከአንዳንድ አንባቢያን በሚደርሰኝ አስተያየት ድረ ገፁ የሚያተኩረው መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ እንደመሆኑ ሌላ ዓለማዊ ነገር ሊኖረው እንደማይገባ ነው፡፡ ነገር ግን እውነታው እንደዛ አይደለም፡፡ ይህ ድረ ገፅ ሲቋቋም እንደዓላማ አድርጎ የተነሳው ሁሉንም ዓይነት ይዘት እንዲኖረው ተፈልጎ ነው፡፡ ከመዝናኛነት አንስቶ እስከ መረጃ መለዋወጫነት፣ ትምህርት ሰጪነት ድረስ እንዲሄድ ነው፡፡ጥቂትና የተወሰኑ አንባቢያን ብቻም ሳይሆን ሁሉም ሊያነበውና ሊሳተፍበት የሚችል ማድረግ ነው፡፡
ይህንንም ለማድረግ ጥረት በመደረግ ላይ ነው፡፡ በአንድ ጉዳይ ላይ ብቻ የሚያተኩር ሆኖ የገፁ እይታ እንዲጠብ አይፈለግም፡፡

 ይህ ማለት ግን ሀይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ ፅሁፎች ልክ እንደሌላው ጉዳዮች እኩል ይታያሉ ማለት አይደለም፡፡ ቅድሚያ የሚሰጠውም ሀይማኖት ነክ ለሆኑና መሰል ፅሑፎች ነው፡፡  በተረፈ ግን ሁሉም ነገር ይቀርብበታል፡፡ አዝናኝ ፅሁፎች ማለትም ግጥሞች፣አጫጭር ታሪኮች፣መጣጥፎች፣ስፖርታዊ ክንውኖች፣ የመፅሐፍ ዳሰሳዎች. . . . .ሌላም ሌላም  እንደጊዜውና ወቅቱ መረጃዎችን ይዞ ለመቅረብ ይሞከራል፡፡  ስለሆነም አብራችሁኝ ለመስራትና ፅሑፎቻችሁን ለመላክ እና ለማካፈል ለምትፈልጉ በሙሉ ከሚከተሉት አድራሻዎች በመረጡት ይላኩኝ፡፡

Facebook- Bisrat Ge 

E-mail - bisratview@gmail.com  

 Twitter-    Bisratge (Bisrat Gebre) 

Mobile-    +251-922-123458 



‹‹ በማደግ ላይ ያለ ዐይነ-ገብ ድረ ገፅ››
 
 





5 comments:

  1. well done Bisrat, berta

    ReplyDelete
  2. web sitek endalikew eyadege new ene balehubet Norway bizu anbabiyan aluk

    Selam from Norway

    ReplyDelete
  3. louv ur colur choice

    ReplyDelete
  4. hulet egr alegn teblo hulet zaf lay aywetam. < manm endatastu tetenkeku>

    ReplyDelete
  5. WELL DONE AND YOU ARE DOING GREAT.

    ReplyDelete