ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Monday, April 23, 2012

“ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማም”


“ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን  በተናገሩት አልስማማም

(ኤፍሬም እሸቴ - በግል)

በፀሐፊው ፍቃድ የተወሰደ

ማክሰኞ ሚያዚያ 9/2004 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ እንደተለመደው የምክር ቤቱ ክቡራን አባላት በንባብ ላቀረቡላቸው ጥያቄዎቻቸው መልስ ሲሰጡ ተከታትያለኹ። ከጥያቄዎቹ አንዱ ወቅታዊው የሙስሊሞች ጉዳይ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምሻቸው “መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ አልገባም” የሚለውን በሰፊው ሲያብራሩ ቆዩ። አንዱ ማብራሪያቸው ስለ ሰላፊያዎች (አል-ሰላፊያ ወይም ወሐቢያዎች) ነው። ራሳቸውን አል-ሰላፊዩን የሚሉትና ትክክለኛውን የቁርዓን ትምህርት እንከተላለን የሚሉት የሙስሊም ክፍል የሆኑትና መሠረታቸውን በሳዑዲት አረቢያ ያደረጉት ጽንፈኛ ወገኖች በተቃዋሚዎቻቸው ደግሞ “ወሐቢያዎች” ይባላሉ። የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ስለ ወሐቢያዎች እና ስለአክራሪነታቸው ማተት ስላልሆነ የዚህን ቡድን አስተምህሮ እና በኢትዮጵያ ላይ ስለ ጋረጠው ከፍ ያለ አደጋ “አክራሪ እስልምና በኢትዮጵያ” (ኤፍሬም እሸቴ፣ በ2000 ዓ.ም/ 2008 የታተመ) የሚለውን መጽሐ ማንበብ እንደሚቻል በመጠቆም አልፋለኹ

 ወደ ርዕሰ ጉዳያችን ስንመለስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ሙስሊም አክራሪዎች ከማብራራታቸው ጎን ለጎን ደግሞ አክራሪነት በእስልምና ብቻ ያልተገታ መሆኑን ለማስረዳት በሚመስል መልኩ በክርስትናው ውስጥ በተለይም በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያለውን በምሳሌነት ለማንሣት በጥምቀት ወቅት ወጣቶች ይዘውት ወጡ ያሉትን መፈክር ጠቅሰዋል። “ጥምቀት ላይ ከነበሩት መፈክሮች አንዱ ‘አንድ  አገር - አንድ ሃይማኖት’ የሚል ነው። …. ‘አንድ አገር - አንድ ሃይማኖት’ የሚል ሕገ መንግሥት የለንም። (መፈክሩ) … የክርስቲያን መንግሥት እንዲኖር የሚፈልጉ … እንዳሉ ያሳየናል” ብለዋል - ጠ/ሚኒስትሩየዚህም መነሻው የግንዛቤ ማነሥ በመሆኑ በማስተማር የሚመለሱ ናቸው” ሲሉ አክለዋል።

ቀጥለውም ይኸው አክራሪነት በክርስትናም ውስጥ እየታየ መሆኑን ለአብነትም ጥምቀት ላይ የሚታዩ መፈክሮችን ካብራሩ በኋላ አክራሪዎቹ “አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱትን ግልባጭ ሲያራምዱ ታይተዋል” ሲሉ የእስልምናው “ሰለፊ” በክርስትናው በተለይም በኦርቶዶክሱ በኩል “ማኅበረ ቅዱሳን” ነው የሚል አንድምታ ያለው አጭር ነገር ግን ከባድ ኃይለ ቃል ተናግረው አልፈዋል። “አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱት” ያሉት ግን ምን መሆኑን በርግጥ አላብራሩም። ምናልባት ከላይ “አንድ አገር - አንድ ሃይማኖት” የሚል መፈክር ያዙ የተባሉት የጥምቀት አክባሪዎች “የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ሳይሆኑ አይቀ/ ናቸው” በሚል እሳቤ የተናገሩትም ይመስላል። ወደ ኋላ እንመለስበታለን።

በመጀመሪያ “አንድ ሃይማኖት” የሚለው መሠረታዊ ሐሳብ ለብዙ ውይይቶች በር የሚከፍት ትልቅ ጉዳይ ነው። ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚያስተምረን እና የጥምቀት አክባሪ ክርስቲያኖች በቲ-ሸርቶቻቸው ላይ አትመውት በፎቶግራፍ የተመለከትኩት ኃይለ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ ኤፌሶን መልእክ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ የጻፈው “አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንዲት ጥምቀት” የሚለው ሐዋርያዊ ቃል ነው። ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል እንጂ የጥምቀት አክባሪዎቹ የፈለሰፉት አይደለም። በዚህ የሐዋርያው ቃል ውስጥ ያለው “አንድ ሃይማኖት” የሚለው አገላለጽ የሚናገረው ስለ ክርስትና ሃይማኖት ነው። ሌሎች እምነቶች የሉም፣ መኖርም የለባቸው የሚል የጨፍላቂነት ትምህርት አለመሆኑን ሊቃውንቱ አምልተው አስፍተው ሲያስተምሩ ኖረዋል፤ እያስተማሩም ነው። አሁን ደርሶ የሚለወጥ ነገር የለም።

በኢትዮጵያ ዐውድ ከተመለከትነው “ክርስቲያኖች ኢትዮጵያ የምትባለው አገር የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ብ….ቻ ናት፣ ያለ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሌሎቻችሁ ቦታ የላችሁም ትላላችሁ” የሚል አንድምታ እየሰጡ የሚናገሩ እና የሚጽፉ ብዙ ኢትዮጵያውያን ከመኖራቸው አንጻር “አንድ ሃይማኖት” የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል አንዳንድ ሰዎች የተሳሳተ ትርጉም እንዳለው አድርገው እየተጠቀሙበት እንዳይሆን ሥጋት አለኝ።

“አንድ ሃይማኖት” የሚለው አገላለጽ ከሃይማኖት ጋር በማይተዋወቁ ሰዎች ዓይን ከተመለከትነው መቻቻልን ለማስተናገድ ፈቃደኝነት የጎደለው አገላለጽ ሊመስል ይችላል። መቻቻል ማለት ግን መሠረታዊ የራስን ሃይማኖት አስተምህሮ መናድና መካድ ስላልሆነ መፍትሔው እርስ-በርስ መገነዛዘብና መረዳዳት ነው። የትኛውም ክርስቲያን “አንድ ሃይማኖት” ቢል የሐዋርያውን ቃል መጥቀሱ እንጂ ሌላ እምነት ላላቸው ኢትዮጵያውያን ጥላቻ አለው ማለት አይደለም። የጥምቀት አክባሪ ወጣቶች ቲ-ሸርቶች ላይ የተጻፈውን የሐዋርያውን ቃል የምረዳው በዚህ መንፈስ ነው።


ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠቀሱት መፈክር  “አንድ ሃይማኖት” ብቻ ብሎ ሳያበቃ “አንድ አገር” የሚለውን ጨምሮበት “አንድ አገር - አንድ ሃይማኖት” ሚል ተጽፎ ከሆነ አባባሉ ሌላ ትርጉም ማለትም “የክርስቲያን መንግሥት ለመመሥረት መሻት” የሚል አንድምታ ሊሰጠው ይችላል። ቲ-ሸርቶችን የለበሱ እና ባነሮችን የያዙ ወጣቶች በምቀት በዓላት አሁን ባለው መልክ በዓል ማክበር ከጀመሩ ገና ሁለት ወይም ሦስት ዓመታቸው ነው። በነዚህ ሁለት ወይም ሦስት ዓመታት የጥምቀት በዓላት ላይ የተነሱ እና ከተለያዩ ድረ ገጾችና ማኅበራዊ ገጾች የሰበሰብኳቸው ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ፎቶግራፎች በድጋሚ በጥንቃቄ ለመመልከት ሞክሬያለኹ። እነዚህ በተለያዩ ካሜራዎች፣ በተለያዩ አንሺዎች፣ ከተለያዩ አቅጣጫዎችና በተለያዩ ቦታዎች ተነሡት ፎቶግራፎች ውስጥ ጠ/ሚኒስትሩ ያሉት ዓይነት ጥቅስ ወይም ተመሳሳዩን ፈልጌ ላገኝ አልቻልኩም። በርግጥ መፈክሩ በነዚህ ፎቶዎች ውስጥ ባለመገኘቱ የተነገረው ነገር ስህተት ነው ማለት ላይሆን ይችላል። ነገር ግን ከመፈክሩ ከባድነት እና ከያዘውም ሐሳብ ጽኑዕነት አንጻር አንዱም ፎቶ አንሺ ሊያነሳው ያለመቻሉ ሁኔታ የአጋጣሚ ብቻ ነበር ለማለት አያስችልም። ስለዚህ አስቀድሞም ኅሊናዬ እንደሚነግረኝ እንዲህ የሚል ጥቅስ አልነበረምም አልተጻፈምም ለማለት እደፍራለኹ። 

“አንድ አገር” የሚለውን ነጥብም በተመለከተ ባለሙያዎች የበለጠ ሊያብራሩት እንደሚችሉ ባምንም በግሌ የሚሰማኝን ግን በአጭሩ ለመጠቆም እሞክራለኹ። እዚህ በምንኖርበት አገር በአሜሪካ Pledge of Allegiance የሚሉትና ቃል ኪዳናቸውን የሚያጸኑበት መሐላ (ማለትም "I pledge allegiance to the flag of the United States of America, and to the republic for which it stands, one nation under God, indivisible, with liberty and justice for all”) አላቸው። አሜሪካዊ የሆነ ሁሉ ከትንንሽ ተማሪዎች እስከ ምክር ቤት አባላት ድረስ ያውቁታል፣ በየአጋጣሚውም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይሉታል። ለአገራቸው ያላቸውንም ቃል ኪዳን ይገልፁበታል።

አንድ አገር/ one nation under God ያሉት ግን የሁሉም የሆነ አገር ማለታቸው መሆኑ ግልጽ ነው። አገር የጥቂቶች ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ ሊሆን ይገባዋል። ኢትዮጵያን በምሳሌነት ካነሣን በአንዲቱ አገራችን ውስጥ ኢትዮጵያውያን ለብዙ ሺህ ዓመታት በሰላም እንደኖርነው ሁሉ አሁንም ክርስቲያኑም፣ ሙስሊሙም፣ የሚያምነውም የማያምነውም “አገሬ” ብሎ ሊኖርባት ይገባል እንጂ ለዚህኛው እምነት ተከታይ “አገር” ሆና ለሌላው እምነት ተከታይ ደግሞ አገር የማትሆንበት ምንም ምክንያት አይኖርም።

“አንድ አገር” ሲባልም ሥጋት የሚገባው ዜጋ ሊኖር አይገባም። “አንዲት አገር” ዜጎቿ ተጨፍልቀው፣ ተጠፍጥፈው የምትፈጠር አይደለችም። በሌላ ጽሑፍ እንዳነሣኹት ኢትዮጵያውያን ብዙዎች ብንሆንም አንዲት አገር ናት ያለችን። አገራችን ቀለማችንና ቋንቋችን ለየቅል ቢሆንም ሁላችን በአንድነት የምንኖርባት የጋራ ቤታችን ናት። ኢትዮጵያውያንም እንደ አሜሪካኖቹ “ከፈጣሪ በታች ያለች አንዲት አገር/ one nation under God” አለችን ብንል የሚያሳፍር አይሆንም። በእርሷ ነውና እኛም “ኢትዮጵያውያን” የተባልነው። በሃይማኖትም አንጻር ካየነው ይህቺ አገራችን ቅዱሳን በኪደተ እግራቸው የባረኳት፣ አበው በደማቸው የጠበቋት፣ እምነት እና ቋንቋ ሳንለይ የምንኖርባት ቅድስት ምድር ናት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እግረ መንገዳቸውን ያነሱትን እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን “አክራሪነት” በክርስቲያኑ በኩል “ይወክልልናል” ብለው የጠቀሱትን ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ እኔም እንደ አንድ አባል የማምንበት አቀርባለኹ። ማኅበሩ በኃላፊዎቹ በኩል የሚሰጠው መልስ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሁለት አሥር ዓመታት አባል የሆንኩበት እና መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት በሁሉም ዘንድ የተመሰከረለት ማኅበር “አክራሪ” አለመሆኑን በግሌ ለመመስከር እገደዳለኹ።   

ማኅበረ ቅዱሳን “እግዚአብሔር ያከበራቸው የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፣ ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከበርበት” ማኅበር ሲሆን አገልግሎት መስጠት ከጀመረ እነሆ 20 ዓመት ሆነው። ማኅበሩም ያለውን ዓላማ፣ ግብና ርዕይ በመጽሔቶቹ፣ በጋዜጦቹ፣ በዐውደ ርእዮቹ፣ በኦዲዮ እና ቪዲዮ ውጤቶቹ ደጋግሞ ጽፏል፣ ተናግሯል፣ አስተምሯል። ከዚህ አንጻር ማኅበሩ አገርንም ሆነ ፖለቲካን፣ ሌሎች እምነቶችንም ሆነ ተቻችሎ መኖርን በተመለከተ ከማንም በላይ በሰፊው በሰለ እና ጤናማ ሆነ መንገድ ሐሳቡን አስተጋብቷል። ስለዚህም የማኅበረ ቅዱሳን አቋም “ጥምቀት ላይ የወጡ ጥቂት ሰዎች ይዘዋቸው ነበር” በተባሉ መፈክሮች የሚገለጽ አይደለም። በነዚህ 20 ዓመታት የተሠሩ ሥራዎቹን፣ የሕትመት ውጤቶቹን እና አባላቱ በግልጽም ሲናገሩት የኖሩትን መመርመር በርግጥም ማኅበሩ ምን ዓይነት ነጽሮተ- ዓለም (Weltanschauung) እንዳለው በቅጡ ለመረዳት ያስችላል።

ታዲያ “ማኅበረ ቅዱሳንን ከአክራሪነት ጋር ማገናኘት” ለምን አስፈለገ የሚለው ግን በደንብ መታየት አለበት። መንግሥትም የዚህን አስተሳሰብ ምንጭ መረዳት አለበት ብዬ አምናለኹ። መነሻው ቤተ ክርስቲያናችንን የእርሷ ባልሆነ ትምህርት እና እምነት ለመለወጥ የሚሞክሩ ነገር ግን “ይህንን እንዳናደርግ ማኅበረ ቅዱሳን እንቅፋት ሆኖብናል” የሚሉ አካላት (ተሐድሶዎች) ለረዥም ዘመን ሲያሰሙት የቆዩት ክስ ነው። በእነርሱ አስተያየት አንድ ሰው ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮውን አልለውጥም ካለ “አክራሪ” ይሉታል። እነርሱ “አክራሪ ነው” የሚሉትን ሰው በሙሉ ጠቅልለው በጋራ “ማኅበረ ቅዱሳን” ብለው ይጠሩታል። ሰውየው የማኅበሩ አባል ቢሆንም ባይሆንም ለቤተ ክርስቲያኑ ጥብቅና የሚቆም ከሆነ ማሸማቀቂያቸው “ማኅበረ ቅዱሳን ነህ እንዴ?” የሚል ነው።

እንግዲህ በኦርቶዶክሳውያን እና በተሐድሶዎቹ መካከል ሲደረግ የቆየ ትግል አዲስ ምዕራፍ የሚያገኘው እነዚህ ኦርቶዶክስን ለመከለስ (ለማደስ) የሚፈልጉ ሰዎች “በፖለቲካው ጉያ ምቹ ቦታ ባገኘን” የሚለው ሙከራቸው ተሳክቶ በራሱ በመንግሥት ስም ዓላማቸውን ማራመድ ከጀመሩ ነው። ከነዚህም አብዛኞቹ የኢሕአዴግ የፖለቲካ መስመር ደጋፊዎች በመምሰል (በተለይም ከ1997 ዓመተ ምሕረቱ ምርጫ - ምርጫ ’97) እና ውዝግቡ ጀምሮ ማኅበረ ቅዱሳን ለቅንጅት ማሸነፍ ትልቅ ሚና ተጫውቷል በማለት በመንግሥት ልምጭ የራሳቸውን ዱላ ለማሳረፍ በብዙ ሲጥሩ እንደነበር ይታወቃል። በይፋም ጽፈዋል። የጠ/ሚኒስትሩ አጭርና ብዙ መልእክት የተሸከመች ዐረፍተ ነገር “እነዚያ መንግሥትን ተገን አድርገው ቤተ ክርስቲያኒቱን ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ የሚሞክሩ ሰዎች/ ተሐድሶዎች መንግሥትን ለዓላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ተሳካላቸው ማለት ነው?” የሚል ስሜት ያጭራል።

ከዚህ አንጻር ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ የወጣ እምነት ይዘው ቤተ ክርስቲያኒቱን እና ትምህርቷን በመለወጥ የራሳቸው ለማድረግ የሚሞክሩ ሰዎች፣ ቡድኖች እና ድርጅቶች መኖራቸው እየታወቀ በገንዘቡ፣ በጉልበቱ እና በዕውቀቱ ለቤተ ክርስቲያኑ ብቻ ሳይሆን ለአገሩም በቅንነት የሚያገለግለውን አንድ ትውልድ ጨፍልቆ በአክራሪነት ስም መፈረጅ በቤተ ክርስቲያኒቱ ህልውና ላይ ትልቅ የሚዛን መናጋት ያስከትላል ብዬ በድፍረት መናገር እችላለኹ። ተሐድሶዎቹም ሆኑ ሌሎች የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቀናቃኞች “ዓላማችንን ሊያውቅብን ይችላል” የሚሉትን ማኅበር ሕጋዊ አገልግሎት ያለ አግባብ ሌላ ስም መስጠት ይህንን ቃል እንደ መመሪያ ወስደው የግል ፍላጎታቸውን ለመፈጸም ለሚቋምጡ ወገኖች ትልቅ ደስታ ነው።

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እምነት አክራሪነትን መሸከም አይችልም። ሌላ ማንም አካል ሳያስፈልጋት ራሷ ቤተ ክርስቲያን የእርሷ ያልሆኑትን ለመለየት ችሎታ አላት። አማኞቿም ማን አክራሪ እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ። በበግ ለምድ ተደብቀው ሌሎችን “አክራሪዎች ናቸው” በሚል ሽፋን በጎች-ምእመናንን ለመንጠቅ የሚሞክሩትንም ያውቃል። የአክራሪነትን ምንነት ለመረዳት ሰፕቴምበር 11ን፣ የሎንዶኑን የባቡር ጣቢያ ፍንዳታ፣ የጅማውን ጭፍጨፋ፣ የኒው ዴልሒን የሽብር አደጋ፣ አል-ሸባብ በየጊዜው በሶማሊያ የሚፈጽመውን መመልከት ያስፈልጋል። ትርጉሙና ምንነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ያለቦታው ይህንን ቃል መጠቀም ሕዝቡ ቃሉ ያዘለውን ቁምነገር እንዳይረዳ ከሚያደርገው በስተቀር ውጪ ሌላ ምንም ጥቅም የለውም።

በርግጥ ገዳማትንና አብነት ት/ቤቶችን ከጥፋት መታደግ አክራሪነት ነውን? ወጣቱ ትውልድ ሃይማኖቱን አውቆ በሥነ ምግባር ታንጾ አገሩንና ቤተ ክርስቲያኑን በቅንነት እንዲያገለግል ማድረግ አክራሪነት ነውን? በገንዘቡ፣ በዕውቀቱና በጉልበቱ በነጻ የትውልድ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚሞክር ትውልድ መፍጠር አክራሪነት ነውን? በጭራሽ!!! ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ማኅበሩ ባሉት ሐሳብ አልስማማም።

ከላይ በመግቢያዬ በጠቀስኹት መጽሐፍ ላይ በዝርዝር ለመቅረብ እንደሞከርኹት “አክራሪነት”ን በማይገባው ምሳሌ መግለጽ በሕዝቡ አእምሮ ውስጥ ሊፈጥረው የሚችለው ሥዕል ዞሮ ዞሮ አገሪቱ ከአክራሪዎች ሊገጥማት የሚችለውን አደጋ ይጨምረዋል ብዬ አስባለኹ። ምክንያቱም ‘አክራሪነት’ አስቀያሚ መልኩን በኒውዮርክ ፍንዳታ ፍንትው አድርጎ ስላሳየ ዛሬ ማኅበረ ቅዱሳንን በዚህ ስም መጥራት በራሳቸው በወሐቢያ አክራሪዎቹ ዘንድ ሳይቀር የማይሆን ግምት ያሰጣል።

                          በአጠቃላይ ክቡር ጠ/ሚኒስትሩ የተናገሩት አጭር አስተያየት ለተለያዩ ዓይነት ትርጉሞች ክፍት ቢሆንም ይህንኑ ንግግራቸውን ከሕግ እና ከመመሪያ የሚቆጥሩ ብዙ ክፍሎች የንግግራቸውን ጫፉን ብቻ ይዘው ሙሉ መንፈሱን ሳይረዱ የመሰላቸውን አቅጣጫ እንዳይሄዱ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። በጠቅላላውም ካየነው የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ መታየት ያለበት “በቤተ ክህነቱ እና በቤተ ክህነቱ ብቻ” ነው ብዬ አምናለሁ። በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት ማለት የቤተ ክርስቲያኒቱን ጉዳይ ለራሷ መተው ነው።

በሌላም በኩል የሙስሊሞችን ጉዳይ ለሕዝብ ለማሳየት እና ቀሪው ሕዝበ-ሙስሊም እንዳይከፋ በሚመስል መልክ ከክርስቲያኑ ወገን ማኅበረ ቅዱሳንን በማነጻጸሪያነት መጥቀስ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም። የሙስሊሞቹን ጉዳይ በራሳቸው ዐውድ እና በራሳቸው የእምነት ሥርዓት መፍታት እንደሚገባው ሁሉ የክርስቲያኑንም ጉዳይ በክርስትና ሃይማኖት ሕግ እና በክርስትና መነጽር ብቻ ሊታይ ይገባዋል።

ይቆየን

 

ፀሐፊውን ለማግኘት፦

ephremeshete@Gmail.com or (http://www.adebabay.com/)

21 comments:

  1. I am not clear with your objectives!! Talking about MK as an association and some members of MK is quit different. I think, you could be one of them who are deviant from the goals of MK but act as member of MK. Think over it!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. What is the benefit of talking about some members of MK in the parliament-->It is Politics. It makes us sure that he tried to say sth to MK(not for some members as u said). What is the reason for comparing some members with selefi?? because he has to talk to either with MK or the Bete Kihnet about these some. Why he dont talk some workers of tele... This is all because he want to convey a message to MK not for some as u say!

      Delete
    2. Thank you! As you said, it could be one way of political communication. But, I feel that it is exaggerated! What is the benefit talking about the PM's message about MK?

      Delete
    3. Ok you are welcome bro,
      what u said exaggeration is relative, obviously my feeling towards something will not be in the same degree.
      you can point out this expression is exaggerated, this one is good... so that we can discuss on the ideas and reach to common understanding.
      The benefit of talking the PM's message is if he is ready to accept the truth it will be for himself and his party. Also to let the people know the truth rather than his sayings. These days we know that there are much peoples who just accept his sayings word by word and echo it everywhere which will be not good for MK and for all.
      That is all!

      Delete
  2. Boys he is the most right person in this earth ...you should know with whom you are talking to

    ReplyDelete
  3. Dear Bisrat:
    first of all, it is my first time to read your blog, and i said thank you. But there are a lot of colors in your site, if you are accepting me pls change your preferred colors (atachuhew). Then, the 2nd comment pls be different from other blogs, it is the same issues raises like adebabay, ahatitewahido....... you have to learn from Dn Daniel Kibret's view.
    Thanks

    ReplyDelete
  4. irasihin inde MK abal yemitay yimeslegnal!!! ibakihin zefen download yemideregibetin link kefteh sile MK batawera des yilegnal.

    ReplyDelete
  5. በሌላም በኩል የሙስሊሞችን ጉዳይ ለሕዝብ ለማሳየት እና ቀሪው ሕዝበ-ሙስሊም እንዳይከፋ በሚመስል መልክ ከክርስቲያኑ ወገን ማኅበረ ቅዱሳንን በማነጻጸሪያነት መጥቀስ ተገቢ ነው ብዬ አላምንም። የሙስሊሞቹን ጉዳይ በራሳቸው ዐውድ እና በራሳቸው የእምነት ሥርዓት መፍታት እንደሚገባው ሁሉ የክርስቲያኑንም ጉዳይ በክርስትና ሃይማኖት ሕግ እና በክርስትና መነጽር ብቻ ሊታይ ይገባዋል። Good Idea.

    ReplyDelete
  6. ገብረመድህን ደስታMay 12, 2012 at 5:36 PM

    የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እምነት አክራሪነትን መሸከም አይችልም።
    “የዚህም መነሻው የግንዛቤ ማነሥ በመሆኑ በማስተማር የሚመለሱ ናቸው”- ስህተት
    ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠቀሱት መፈክር “አንድ ሃይማኖት” ብቻ ብሎ ሳያበቃ “አንድ አገር” የሚለውን ጨምሮበት “አንድ አገር - አንድ ሃይማኖት” ቢባልም ከአክራሪ ጋር ማነፀፃር ይከብዳል- አይነፃፀርምም፡፡
    አንድ አገር - አንድ ሃይማኖት የሚል ጥቅስ አልነበረምም አልተጻፈምም ወደፊትም አይፃፍ፡፡
    ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሱትን እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን “አክራሪነት” በክርስቲያኑ በኩል “ይወክልልናል” ብለው የጠቀሱትን ማኅበረ ቅዱሳንን ለሁለት አሥር ዓመታት መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት በሁሉም ዘንድ የተመሰከረለት ማኅበር“አንድ አገር - አንድ ሃይማኖት” አለ በማለት “አክራሪ” ብለው መሰየማቸው ትርጉሙና ምንነቱ ያለቦታው መጠቀም ሕዝቡ ቃሉ ያዘለውን ቁምነገር እንዳይረዳ ያደርጋል፡፡
    ሰይጣንም
    መናፍኩም
    አህዛቡንም
    .....
    እግዚአብሀሄር ያስታግስልን

    ReplyDelete
  7. that's a good idea.we all christian brother must pray for our work.god is always with us.i get good ideas thank you.for posting such ideas.good work

    ReplyDelete
  8. not good observation ,there is a big difference between "አንድ አገር - አንድ ሃይማኖት" and "አንድ ሃይማኖት".

    ReplyDelete
  9. This post will assist the internet viewers for creating new
    web site or even a blog from start to end.
    My site - cool articles to write about

    ReplyDelete
  10. Woah! I'm really digging the template/theme of this site. It's simple, yet effective.
    A lot of times it's very difficult to get that "perfect balance" between usability and visual appearance. I must say you've done a very good job with this.
    Also, the blog loads super fast for me on Safari. Exceptional Blog!
    my page > click here to see the attached video

    ReplyDelete
  11. God bless you for your brief explanation and your message,you really opened my eyes i haven't seen his message like this and also your response has helped me what MK really stands for, also known how i should deeply take care of this kind of speeches so thank you may god bless Ethiopia,MK,and you.

    ReplyDelete
  12. GOD bless you for your brief explanation and message,as a reader you really opened my eyes i haven't seen what he sayed like this and i have know what MK has stood for,also i have known how i should deeply take care of this kind of speeches so may god bless Ethiopia,MK and you.

    ReplyDelete
  13. What you wrote is true.If one paints a wall with different colors the wall never change to iron.Hence,if anybody tries to defame Mk God does erase it and shall make it more famous.We know what Mk did, is doing and will do.Moreover,God know much
    better than everyone about His slaves,Mk.God reads hearts not lips.Mk,be as strong as Saint Pauland saint George.Time heals
    the days ills.

    ReplyDelete
  14. ωhoah this weblog іs ωonderful i
    love stuԁying уour aгticles.
    Keeρ up the goοd work! You realize, a lоt of indіviduals
    arе loοking aгounԁ for
    this info, уou could aid them greatly.
    Review my web-site get him to fall for you again

    ReplyDelete
  15. he must be forgive us ...but he pass

    ReplyDelete
  16. "I couldn't find it, so it doesn't exist"..........is fool's logic

    ReplyDelete
  17. I really see what MK has done.We all orthodox chirstians must be part of them
    or supports what they are doing.

    ReplyDelete