ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Monday, November 21, 2011

ይቺ ህዳር ወር. . . .

ይቺ ህዳር ወር እኮ ቀስ በቀስ በዓመት በዓሎች ተሞልታ ትርፍ ቀን ሊጠፋባት ነው፡፡ ‹‹ህዳር አጠና››፣ ‹‹ታላቁ ሩጫ››፣ ‹‹የብሔር ብሔረሰቦች ቀን›› ኧረ ሌሎችም አይጠፉም፡፡

ባለፉት ሰሞናት ማጤሱን እርግፍ አድርጎ ትቶት የነበረው ወዳጄ ከኪሱ እንደዋዛ ሲጋራውን መዘዝ አድርጎ ለኮሰና ጭሱን አንቧለለብኝ፡፡

‹‹የተውከውን ሲጋራ ዛሬ ምን ተገኘና አነሳኸው?›› አልኩት ጢሱ ወደ ዐይኑ እንዳይገባ አንድ ዓይኑን ጨፍኖ በተለመደ ትህትና ፣ ‹ህዳር ሲታጠን› አለኝ፡፡ እና ጢሱን ወደ እኔ አንቧለለብኝ፡፡ (በልቤ ታዲያ የምታጥነው እኛን ነው እንዴ? እያልኩ በአፌ ዝም!)
በየዓመቱ ህዳር 12 ‹‹ህዳር ሲታጠን›› በርካታ የአገራችን ክፍል ይታጠናል፡፡ ለምን? ታሪኩ በከፊል የሚከተለውን ይመስላል፡፡

በዛ ዘመንም በአገሪቱ ሕመም በረታ በመላው አገሪቱ በሽታው እየተላለፈ በርካቶችን ለሞት ዳረገ፡፡ ሕፃን፣ ሽማግሌ ሳይለይ ለህመም እና ሞት የዳረገው ይህ ዘመን ለአገሪቱ ትልቅ ስጋት ሆነ፡፡ ምን ይደረግ? ሲሉ ሊቃውንት መከሩ፡፡ መከሩ እና ቆሻሻን ሰብስቦ በማቃጠል ህዳርን አጠኑት፡፡ ችግራቸውም ከጭሱ ጋር አብሮ በነነ፡፡ አንዳንዶች አሁንም ቢሆን ያሉብንን ችግሮች ለማቃለል ብቸኛው መፍትሔ ይኽ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ለምሳሌ እንደ ኑሮ ውድነት፣ እንደ መልካም አስተዳደር እጦት፣ እንደ ሙስና የመሳሰሉት ህዳር ሲታጠን ይጠፋሉ የሚል እምነት በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ አለ፡፡ ለምሳሌ ያ ወዳጄ የሲጋራውን ጢስ ወደ እኔ ያቦነነው ችግሬ አንተ ነህ ሊለኝ ፈልጎ ነው፡፡ ምን አደረኩት? ምንም፡፡ ከመምከር በስተቀር ምን የማድረግ አቅም አለኝ?


የሆነ ሆኖ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ይቺን ቀን ለማክበር በየዓመቱ ህዳር 12 በአገራችን፣ ‹‹ህዳር አጠና›› ቆሻሻን በማቃጠል ይከበራል፡፡ በርግጥ በየሚዲያዎቻችን ቆሻሻን የማቃጠል ባህል አካባቢን ይበክላልና አጽዱ እንጂ አታቃጥሉ ተብሏል፡፡ ቢሆንም ግን በርካቶች አሁን ችግራቸውን ከጢሱ ጋር ለመሸኘት አካባቢያቸውን አጽድተው ቆሻሻንም አቃጥለዋል፡፡ የማጽዳት ስንፍና ያለባቸውም እንደ ወዳጄ ያሉ ሰዎች በሲጋራ ጢስ፣ ‹‹ችግር›› የሚሉንን እኛን (መካሪዎቻቸውን) ለማጥፋት ሙከራ አድርገዋል፡፡


(አበበ ቶላ፤ የአቤ ቶኪቻው ሽሙጦች፣ 2002)

3 comments:

 1. **"በዛ ዘመንም በአገሪቱ ሕመም በረታ በመላው አገሪቱ በሽታው እየተላለፈ በርካቶችን ለሞት ዳረገ፡፡ ሕፃን፣ ሽማግሌ ሳይለይ ለህመም እና ሞት የዳረገው ይህ ዘመን ለአገሪቱ ትልቅ ስጋት ሆነ፡፡ ምን ይደረግ? ሲሉ ሊቃውንት መከሩ፡፡ መከሩ እና ቆሻሻን ሰብስቦ በማቃጠል ህዳርን አጠኑት፡፡ ችግራቸውም ከጭሱ ጋር አብሮ በነነ፡፡"

  በወቀቅቱ ይህ ዘዼ መፍትሂ አስግኝቶ ይሆናል:
  **"አንዳንዶች አሁንም ቢሆን ያሉብንን ችግሮች ለማቃለል ብቸኛው መፍትሔ ይኽ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ለምሳሌ እንደ ኑሮ ውድነት፣ እንደ መልካም አስተዳደር እጦት፣ እንደ ሙስና የመሳሰሉት ህዳር ሲታጠን ይጠፋሉ የሚል እምነት በአንዳንድ ሰዎች ዘንድ አለ፡፡"
  ነግር ግን ዛሪ ላይ አይሰራም::

  ReplyDelete
 2. what about world AIDS day and Urban day???????????

  ReplyDelete
 3. የኢትዮጽያ ችግር አኮ በማጠን ብቻ የሚለቅ ኣይደለም....እግዚኣብሕር ካልገላገለን በስተቀር ....

  ReplyDelete