ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Saturday, December 2, 2017

ህዳር 24 - ካህናተ ሰማይ

ህዳር 24 የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ትልቅ በዓል እንደሆነ ለማታውቁ ወዳጆቼ ፦


       ህዳር 24 ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የስላሴን መንበር ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር ሃያ አምስተኛ በመሆን ያጠኑበት የመታሰቢያ በዓል ነው፡፡

ሃያ አራቱ ካህናት ብለን የምንጠራቸው " አኪያል ፣ ቀርቲያል ፣ ደርቲያል ፣ ኤልያል ፣ ዘርቲያል ፣ ቱቲያል ፣ ዮልያል ፣ ከርቲያል ፣ ለብቲያል ፣ ሚታአል ፣ ራዋል ፣ ሳውር ፣ አናዋል ፣ ፈላላአል ፣ አክርቲያል ፣ አፍልኤል
፣ አውኑዋል ፣ ናናንኤል ፣ ዋቲርናናሳኬብኡማስ ፣ ቲታር ፣ ትርሙን ፣ ዝርኬ ፣ እብጦ ፣ አርናስ " ሲሆኑ አባታችንም ሃያ አምስተኛ ሆነው የፀባዖትን ዙፋን ያጠኑ ሲሆን ይኽም በታላቁ ደብረሊባኖስ ገዳም በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡
በዕለቱም አባታችንን በማሰብ ታቦት ወጥቶ ካህናት የአባታችን በረከት ይደርብን እያሉ የገዳሙን ቅፅር እየዞሩ ያጥናሉ፡፡ ያለው ድባብ ልዩ ነው ፤ ከቻላችሁ ወደ ገዳሙ በመሄድ ካልሆነም በየአቅራቢያችሁ ባሉት የአባታችን ደብሮች የጻድቁን በረከት ታገኙ ትካፈሉ ዘንድ እጋብዛለሁ፡፡

No comments:

Post a Comment