ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Monday, July 2, 2012

"አአዩ" ሳምሪ እና የፍቅር ሀይማኖት

ፀሐፊ ፡ ረድኤት መስፍን

      ሳምራዊት ሰይድን ደሴአረብ ገንዳመስጊድ አካባቢ ዞርዞር ብትሉ አታጧትም፡፡ ሰፈሯ እዚያ ነው፡፡ ከመነሀርያው ፊት ለፊት፡፡ ልብን የሚሰረስሩ ዓይኖቿን ሰብራ መንገድ የሚያስተውን ረጅም ጸጉሯን ደብቃ ሆድ የሚያባባው ፈገግታ አምቃመቅሪብንለመስገድ በራ ትጠፋለች፡፡ በርግጥ ሳሚሪ ወፍ አይደለችም፡፡ ግን እርግብ ናት፡፡ ይቺ እርግብ ትላንት ወዲያ ወሎ የረሀብ ጠኔ መቷት እፍኝ ጥሬ እና ውሀ አጥታ ዋይ ዋይ ስትል የኔ ነበረች፡፡ትላንትም ወሎ የጎሳ ፖለቲካ የታሪክ ቀሚሷን ለመቶ ሲበጣጥቅባት ከኔ አልራቀችም ነበር፤ የዛሬዋ ወሎ ግን ከጣቶቼ እያፈተለከች ነው፡፡ ሀይማኖት የሚሉት የተቀደሰ ነገር ፍቅሬን እየቀማኝ ነው፡፡ ለኔ ወሎ ማለት ሳምሪ ናት፤ ሳምሪ ማለት ሀገር ናት፤ ሀገር ማለት እኔ ነኝ፤ እኔ ደግሞ ፈርቻለሁ፡፡ሀይማኖት በፍቅሬ በኩል ሰርጎ እየገባ ሰላሜን ነስቶኛል፡፡

ረሀብና ፍቅር

        1966 ..ነገሌ፣ አርሲ፡፡ መስፍን ጉተማ ኪሱን በአንድ አንድ ብሮች አጭቆ ይንጎማለላል፡፡ ከርሱ በላይ ሰው አይታየውም፤ ቁመቱ የረዘመ መስሎታል፤አይኑም ሻሸመኔ ድረስ እንደሚመለከት አምኗል፡፡ጫማውን ሊያስጠርግ ቁጭ አለ፡፡ወዲያው አንዲት የዶሮ አይን የምትመስል እንስት በፊቱ ቀርፈፍ  ብላ አለፈች፡፡ አባቴ በአይኑ ብቻ አልሸኛትም፤ ተከተላት፤ አልፈራም፤ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት 10 ኩንታል ስንዴ ሽጧላ፡፡ እናም ጠየቃት፤ የዛሬዋ እናቴ አልማዝ አራጌ ያን ጊዜ አልችልም የሚል መልስ የመስጠት አቅም አልነበራትም፤ ደክሟታል፤ ረሀብ ጉልበቷን በልቶታል፤ ችግር ወኔዋን ሰልቦታል፤ ሰቆቃ ተስፋዋን አጨልሞታል፤ በርግጥ 66 ረሀብ መዘዝ ለጃንሆይም ተረፏል፡፡ ቢሆንም ፍቅር መላመድ ነው እንዲሉ ሁለቱም ተዋወቁ፤ ተስማሙ፤ ተዋሀዱ፤ እኔም ወደ ኢትዮጵያ በሰላም መጣሁ፡፡

2000 .. ደሴ ለአዲስ አመት የእናቴን ቤተሰቦች ለመጠየቅላኮመልዛደርሻለሁ፡፡ አሁንአይጠገብካፌ ቁጭ ብየ የቁንጅና ማኪያቶዬን አጣጥማለሁ፡፡እውነቴን ነው ትኩስ ነገር አላዘዝኩም፤ ለምን ብየ እቃጠላለሁ? ሳምሪ ከጓደኞቿ እየተፍለቀለቀች መጣች፤ ያኔ እንዲህ ግልጽ ነበረች፤ ጸጉሯን አልሸፈነችም፤ አይኗን አልሰበረችም፤ ደርቄ ቀረሁ ይቺ ልጅ ብታምኑም ባታምኑም እናቴን ትመስላለች፤ እንደዚህ አይነት ውበት ከናቴ ሌላ ይኖራል ብየ አስቤም አልሜም አላውቅም፡፡ ዛሬ ግን ከእድሜ ልክ እውነት ጋር ተፋጠጥኩ፡፡ሳምሪን ለመተዋወቅ ከወንበሬ ተነሳሁ፤ወዴት ነው ልጄ? የእናቴ ጥያቄ ነበር፤ ወደ ፍቅሬ ልበላት?

ካምፓስና ፍቅር

     2004 . ደብረብረሀን የኒቨርስቲ፡፡ ከምማርበት ስድስት ኪሎ በርሬ የመጣሁት ሳሚሪ ናፍቃኝ ነው፡፡በዚያ ላይ ደግሞ ፈርቻሁ፡፡እዚህ አዲስአበባ አወልያ /ቤት የተጀመረው የሙስሊም ወንድሞቼ ተቃውሞ ወደእኛ ካምፓስ ቀስበቀስ እየገባ ነው፡፡ተማሪዎች እየተንሾካሾኩ ማውራት ጀምረዋል፤ እየተጠራሩ መውጣት ቀጥለዋል፤ እየተሰባሰቡ መነጋገር ይዘዋል፡፡አልተገረምኩም፤ማንም ወጣት የለውጥ ማእበል ማስነሳት ይመኛል፤ የለውጡ አካል የመሆን  ፍላጎቱም ከፍተኛ ነው፤ ለውጡ ግን አወንታዊ ወይም አሉታዊ ሊሆን ይችላል፡፡ባለፈው ሳምንት ያየሁት ግን ልቤን ይዤ ወደ ፍቅሬ እንድሮጥ አስገደደኝ፡፡ፌስቡክ ላይ ተጥጃለሁ፤የዛሬ ወር አካባቢ አዋሳአበባ ላይ የጻፍኩትን "ደሴን ያያችሁ"የጉዞ ማስታወሻ ከወደዱት(ላይክ)ካደረጉት መካከል ሀናን አህመድ አንዷ ነበረች፤ያው የደሴ ልጆች ስማቸው አንዱ ከክርስትናው ሌላው ከእስልምናው ይመነጫል፡፡የሀናንም እንደዚያው ነው፡፡በዚች የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ፌስቡክ ገጽ ላይ የተለያዩ የተቃውሞና የአትነሳም ወይ መልእክቶችን አነበብኩ፤ወዲያው በጥያቄ ጎርፍ ተጥለቀለኩ፡፡ለምን?ምክኒያቱ ምንድን ነው?መፍትሄውስ?ይህ መንገድስ ወዴት ያደርሰናል? እመኑኝ ሀናን የመምህር አካለወልድ እና የሸህ ሁሴን ጅብሪል ልጅ ልትሆን ትችላለች፡፡ ወይም አቶ አህመድ እና የወ/ ቅድስት
ከሳምሪ ጋር ቁጭ ብያለሁ፤
"…ውዴ ፈራሁ
ለምን ትወደኝ የለ?
አወ ግንእኮ እተለወጥሽ ነው
ሁላችንም በለውጥ ውስጥ ነን፤አንተም ጭምር፡፡
ሳምሪ ይሄ ለውጥ ግን አንቺን የሚነጥቀኝ ከሆነ ገደል ይግባ…"
ሳምሪ ፈገግ አለች፤ተጠግታ ሳመችኝ፤እኔ ቀዝቅዟለሁ፡፡ወደ ዩንቨርሲቲ ለመጀመርያ ጊዜ ስትገባም እንዲህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ ነበር፡፡ግቢ ውስጥ በተለይ ስለእኛ ኦሮሞ የሚወራውን አውቃለሁ፡፡አብዛኛዎቹ ምክንያት አልባ ነበሩ፤የተቀሩት መላምቶች ደግሞ ሚዛን አይደፉም፤ሌሎቹ ግን ከኛው የሚነሱ ናቸው፡፡ይህ የመርዝ ዝናብ የሳምሪን ልብ እንዳያርስብኝ ፈርቼ ነበር፤ተሳክቷል፤ሳምሪ ሚዛናዊ ናት፡፡ የትላንት ሰው አይደለቸም፡፡ እርሷ የነገ ናት፡፡
"…ለምን መጣህ..ኢግዛም አልደረሰም እንዴ?
ደርሷል..ግን ተጨነኩ አልኩሽ አይደል
እንዴት፤ አሸባሪ ብለው ያስሯታል ብለህ?
አትቀልጂ ሳምሪ..ቀልድ አያምርብሽም ደግሞ ናፈቅሽኝ..
እንዴ፤ የዛሬ ሳምንት አዲስአበባ አልነበርኩ ..
እኔንጃ በዚህ ቀውጢ ሰአት አብሬሽ መሆን አለብኝ፡፡
ኔቨርተመለስ፡፡ስሜታዊ እንዳልሆንኩ ታውቃለህ፤ሀይማኖቴን የምር መያዝና መንከባከብ አለብኝ፡፡ሊነጥቁኝ የመጡትን አይሆንም እላቸዋለሁ፤ረዲበምክኒያት ነው፤በቦንብ አይደልም፤ሰው በመግደልም አይደልም፤በማስተማር ብቻ፡፡ ያልገባቸው ብዙዋች አሉ፤ከነዚያ እስክንግባባ ጠብቀኝ፡፡በኋላ ላንተ ሰፊ ግዚያቶች ይኖሩኛል፡፡ አሁን ግን ተመለስ፤ረዲአንብብ፤ ከዚያም ወደ አርሲ ዘመዶችህ ሂድና የአባትህን ስንዴ እርሻዋች ተንከባከብ…"
ውስጤ እያነባ ተለየኋት፤ሳምሪ አልሸኘችኝም፡ቀና ብላ አላየችኝም፡፡ እቅፍ አድርጋ አልሳመችኝም፡፡

ተስፋና ፍቅር

      ሸገር፤ስድስት ኪሎ፡፡ድባብ ቅጭ ብያለሁ፡፡ከፊቴ የካርል ማርክስ ሀውልት ተኮፍሷል፡፡አየሁት፤እድለኛ ድንጋይ ነው፡፡ይሄው ሁለት መንግስታቶችን ለማየት በቅቷል፡፡በመኖርያ ቤቱ ላይ ዩንቨርስቲን ለገነባ ንጉስ ሀውልት የሌላት ሀገር በማርክስ ፍቅር ወድቃለች፡፡ ለነገሩ ካርል ማርክስ ቀላል ሰው አይደለም፤አንድ ጊዜ እንዲህ ብሏል አሉ.. “ሀይማኖትና ኮኬን አደንዛዥ እጽ ናቸው፡፡ተገርሜም አላባራሁ፡፡ምን ያለው ደፋር ነው..ጃል
ባልና ሚስት የሁለት ሀይማኖቶች ውህድ፤እናትና ልጅም እንደዚያው የሆኑባት ወሎ በሀይማኖት ውጥረት ሰከረች፤አበደች፤ጨርቋን ጥላ እርቃኗን ቀረች፤የመቻቻል ተምሳሌትነቷም ደፈረሰ፤እንሆ እኛ አዳዲሶቹ ወጣቶች የአባቶቻችንን ቃል ረሳን፤ምክራቸውን ተጠየፍን፤ታሪካቸውን ሸሸን፤ውጭ ውጭውን ተመለከትን፤ይህም ልባችንን አደነደነው፤ሞራላችንም ላሸቀ፤መጪውን ጊዜ መገመት ተሳነን፤ተስፋችንንም በጡንቻችን ላይ ገነባን፤እናት ሀገር ጠበበችን፤እናም ልናፈርሳት ተነሳንግን እኮ ኢትዮጵያ ለሁላችንም ትበቃናለች፡፡
ፍቅር ያሸንፋል ያለው ቴዲ ነው? ከሆነ ጥሩ እንኳንም የኔ ወንድም ሆነ፡፡አምናለሁ፤ተስፋም አለኝ..አንድ ቀን ሳምሪ ትመለሳለች፡፡ከዚያ ከስሜት  ጎርፍ ፈንጠር ብላ ትወጣለች፤ እኔም ማተቤን ሳልበጥስ እጠብቃታለሁ፤ ወዲያው ትስመኛለች በጣም ስለናፈኳት ደግማ ትስመኛለች፡፡ቀጥለን ወደ ጦሳ ተራራ እንሄዳለን፤ በዚያም ከገጠሩ አርሶአደሮች ጋር ተባብረን የጎመንና የቲማቲም ማሳዋችን እናዘጋጃለን፡፡ምርታችንንም ደሴ ሰኞ ገበያ ወርደን ለወሎዬዎች፤ ለከሚሴ ኦሮሞዋች፤ ለሚሌ አፋሮች እና ለመቀሌ ነጋዴዋች እናከፋፍላለን፡፡በሌላ ቀን ደግሞ ወደ ትውልድ መንደሬ አርሲነገሌ እንመርሻለን፡፡ እዚያ የስንዴ እርሻዎቻችንን እስከ ሲዳማ፡ ጋሞ፡ ወለጋ፡ ነቀምት፡ ጋምቤላ እናስፋፋለን፡፡ኢትዮጵያንም በስንዴ ዳቦ እናጥለቀልቃታለን፤ የሀገሩ ህጻናት ሁሉ በቀን ሺህ ጊዜ ዳቧቸውን ሲገምጡ እንዲህ እያሉ ያሳታውሱናል.."ይህ እኮ የሳም-ረዲ"ዳቦ ነው፡፡አዎ ፍቅር የወለደው ዳቦ፡፡

ሳምራዊት መሀመድ እንደሆነች ትላንት የኔ ነበረች፤ዛሬም የኔ ናት፤ነገም የኔ ትሆናለች፡፡ማንም ፍቅሬን ሊነጥቀኝ ከቶም አይችልም፡ሀይማኖት እንኳ! ለዚህ ደግሞዋቆምሆነነብዩ መሀመድወይምእየሱስይረዱኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

12 comments:

 1. Bisrat is it real story or creative work? or writing, really i like the story , specialy Mechetu wollo mehonu ,bize yemiyasasebegne gudayem new, yesheh husen gibrile ena ye medihaniyalem bereket wollon na ethiopian yitebike

  ReplyDelete
 2. Bekelech from Bahare darJuly 3, 2012 at 2:01 PM

  nicccccccccccccccccee.. . . .I love it

  ReplyDelete
 3. ..IT TELLS WHAT AM FEEL..

  ReplyDelete
 4. Just keep it up don't give up.I really appreciate your effort.

  ReplyDelete
 5. "ወሎየ ተጓዥ ፍቅር ነው ሰሌዳው
  ፍተሻም የለብህ ሹፌር ቶሎ ንዳው"…
  አልተባለም እንዴ…ቂቂቂቂቂቂቂቀ..አንቺም ወሎ?

  ReplyDelete
 6. "ወሎየ ተጓዥ ፍቅር ነው ሰሌዳው
  ፍተሻም የለብህ ሹፌር ቶሎ ንዳው"
  ተብሎ አልነበር እንዴ…ቂቂቂቂቂ…
  አንቺም ወሎ?

  ReplyDelete
 7. እኔም ልማል ባ’ላህ አንችም በቁልቢ ፤
  ክርሽን ሳትፈችው ነይ ከቤቴ ግቢ ፤
  …….ነበር አይ ጊዜ!!!

  ReplyDelete
 8. ...do not worry everything gonne be alright...'cause "IN LOVE WE TRUST".

  ReplyDelete
 9. ...do not give up,every thing gonna be alright,'cause in love we trust.

  ReplyDelete
 10. ...do not give up,every thing gonna be alright,'cause in love we trust.

  ReplyDelete
 11. This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete