ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Tuesday, July 3, 2012

ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል፡፡

የስዊድን ስቶክሆልም ካህን ለፃፉት ፅሑፍ የተሠጠ ምላሽ
ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል፡፡

ፀሐፊ፡ ብርሃነ ስላሴ

       ይህን ፅሑፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ በደጀ ሰላም ድረ-ገፅ ላይ በወጣው ሽምጥጥ ያለ ውሸት በመፃፉ ነው፡፡ ውሸት በቅዱስ መፅሐፍ ‹‹ አቡሀ ለሐሰት›› የሐሰት አባቷ ሰይጣን ነው ይላል ( የሐ.8፡44 ፤ የሐ.ሥራ 5፡3 ፤1ኛ ጢሞ. 4፡1 ፤ራእ. 12፡9)፡፡ እውነትን ማጣመም ፣ሐቅን መደበቅ ፣ያልተደረገ ታሪክን ተደረገ ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ ፈጥሮ መፃፍና ማውራት፤ሐቅን መካድና በተጨማሪም መንፈሳዊና ማኀበራዊ ኑሮን ማደናቀፍና እንዲፈራርሱ ማድረግ በተለይም የተለይም የተደራጀውን ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰላትን ቤተክርስቲያን  (ምህመናንን) ለማፍረስ መነሳት፤ የሐሰት አባት የተባለው የሚያሰራው ነው፡፡ከሁሉ በላይ ደግሞ ፍርሃትና በራስ አለመተማመን ለውሸት ዋና መንገዶች ናቸው፡፡ እንደዚህ ሆኖ የኖረ ሰው ሁሉን ጠርጣሪ በመሆኑ ኑሮው በሙሉ ሰውን ሳያምን እሱም ሳይታመን ይኖራል፡፡ ይህ ባህሪይ ያለበት ሰው መንፈሳዊ በመሆን፣በመፀለይ፣ ቅዱስ መፅሐፍን በመማርና በማጥናት ሊለወጥ ይችላል፡፡ (ሐሰት ግዕዙ ሲሆን ውሸት አማርኛ ነው፡፡)
በሚያዝያ 27 ቀን 2004 ዓ.ም. በደጀ ሰላም ድረ-ገፅ የወጣው የግለሰቡ ፅሑፍ ከዚህ የመነጨ ነው፡፡ ለዚህ የሐሰት መልስ ለመስጠት አርዕስቱን ‹‹ ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል›› በማለት በመገረምና በማዘን ለመፃፍ ተገደድኩ፡፡ ከዚህ በውሸት ከጎደፈው ፅሑፍ ውስጥ በተለይ እንዲህ የሚል ቃል አገኘሁ፡፡
   ‹‹ በቧገታ( ለማኞች ማለት ነው) ወይም በሸመታ ካህናት ከለንደንና ከአንዳንድ ሀገሮች ነጋዴና አትራፊ ካህናት ጋር ግንኙነት በመፍጠር. . . . . . . ›› ይላል፡፡
ውሸት እውነት ሆኖ በታሪክነት እንዳይቀር እውነቱን በዳኝነት መፃፍ አለብኝ ብዬም ከህሊናዬ ጋር ተሟገትኩ፡፡
የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ በሲዊዲን ስቶክሆልም የደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ከተመሰረተና ፅላቱም በክብር ከተተከለ በኋላ ብዙ ሳይቆይ በእመቤታችንንና በሌሎች ታላላቅ በዓሎች ከለንደን እየተመላለስኩ በመቀደስና ምዕመናንን በማገልገል በማደራጀት የኖርኩ ካህን ነኝ፡፡

3 comments:

  1. endet des yilal hassabin betihitina maseredat malet yih new. . .

    ReplyDelete
  2. ውድ አዘጋጅ። በቅድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችንና በክህነት ሥልጣን ስም የሚደረገውን አሳዝኝ ነገር በመጠኑ የሚያጋልጠውን ተቆርቋሪ ጽሑፍ በድረ ገጽዎ ስላወጡት እግዚአብሔር ይስጥዎ። ከስቶክሆልም ታዛቢ።

    ReplyDelete
  3. bisrat
    tebarek sefi leb yalew sew yemiyadegewen adergehal.

    ReplyDelete