ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Thursday, July 26, 2012

የገብርኤል ድርሳን ፡ ሐምሌ

  
‹‹ እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ ›› ሉቃስ 1፡ 19

       ሹም እለእስክንድሮስ ጭፍሮቹን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፡፡  ሰም፣ጨው፣ ባሩድ፣ሙጫ፣የዶሮ፣ ማር፣እርሳስ፣ ብረትን፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨመሩበት፡፡ ጭፍሮችም ያዘዛቸውን ፈፅመው መጥተው ያዘዝከንን ሁሉ ጨምረንበት ነዶ ፈልቷል አሉት፡፡ ድምፁም እንደ ነጎድጓድ ይሰማል፤ ወላፈኑም እንደ ፀሐይ ያንፀባርቃል፡፡
የፍላቱም ኃይል አስራ አራት ክንድ ያህል እየዘለለ ይወጣል፡፡ በውስጡ የሚጣሉትን ሰዎች እዘዝ፡፡ ያንጊዜም ህፃን ቂርቆስንና እናቱን ኢየሉጣን ይዘው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡ በክርስቶስ ስም ስላመኑ በእስር ቤት አግብተው አስረዋቸው ነበርና ፍላቱ ወደ ላይ በሚዘል በብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው በዚያን ጊዜም እልፍ ከአንድ ሺህ አራት መቶ ሰዎች እንዲወጡና በፈላው የብረት ጋን ውስጥ የቅዱሳንን አሟሟት እንዲያዩ ሹሙ አዘዘ፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም የፍላቱን ግርማ ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተጠብቆላት ያለውንም ዋጋ ትታ ልትክድ ፈለገች፡፡

ቅዱስ ቂርቆስም ይህን ባወቀ ግዜ እናት ሆይ ከብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ፤ድንጋፄም አይደርብሽ አላት፡፡ ነገር ግን አናንያንና አዘርያን፣ ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከዕቶን እሳት እንዳወጣቸው እወቂ፤ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ውስጥ ሊያድነን ይችላል፡፡ እናት ሆይ ከሚያልፈው ከዚህ ዓለም ጭንቅ ልታመልጭ በሚያልፈው በዘለዓለም እሳት ልትቀጭ ትሻለች፡፡ እናት ሆይ ይህን አትሺ፤ ይቅርብሽ አሁን እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡
ሶስናን ከሀጢያተኞች እጅ ያዳናት እኛንም ከብረት ጋን ያድነናል፡፡ ዳንኤልን ከአንበሶች አፍ ያዳነ እሱ ያድነናል፡፡እግዚአብሔር በዚህ ብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችን ልንፈፅም ፈቅዶም እንደሆነ የኢዮብን ነፃነት (ትእግስት) ልናገኝ  ይገባናል፡፡ እሱ ልጆቹንና ሚስቱን ያገኘው ገንዘብ ሁሉ አጥቶ በመጨረሻው ሰውነቱን አጥቶ ነበርና ምንም ምንም የቀረበለት አልነበረምና እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ ከማለት በቀር ያለው ነገር የለም እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔርም ወሰደ አለ፡፡ እግዚአብሔርም ሆነ፡፡
የእግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም ይመስገን አለ፡፡ እኛም ይህንን መከራ ልንታገስና የተጠበቀልንን ልንከተል ይገባናል፡፡ በዚህም ምክር እናቱን ለማፅናናት አልቻለም፡፡ ከዚህ በኋላ ቂርቆስ ዓይኖቹን ወደሰማይ አቅንቶ ተመለከተ፡፡
እግዚአብሔር ሆይ ይህችን ባርያህን ከሰጠ ከህይወት መፅሐፍ እኔን ፋቀኝ አለ፡፡ አቤቱ ይህነን ነገር ልታደርግ አይገባህም፤ አቤቱ እርሻውን ልታቃጥል ፍሬውንም ልትባርክ ትወዳለህን፡፡
አቤቱ እንጨቱን ቁረጡና አንድዱት ቅጠሉን ጠብቁ ብለህ ልታዝ አይገባህም፡፡ እንጨቱንም ቅጠሉንም ጠብቁ ብለህ እዘዝ እንጂ ይህ አይገባህም ያመነብህ ሁሉ ይህን ያየ ዘንድ፡፡ ማዳን የሚችል አምላክ ኑሮአቸው ቢሆን ከዚህ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ እንዳይጠራጠር፡፡
ዲያብሎስ ከባለስልጣኑ  ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኑም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ፡፡ ይህንን ፀለየ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማሁ እንዳይል አቤቱ የኃይል መንፈስ ለናቴ ስጣት አበርታት፡፡በዚያን ጊዜ ዲያብሎስ ከሷ ሸሽቶ ሄደ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ እንዲህ አለች፡፡ በመንግስተ ሰማያት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታህ ኃይል ስጠኝ፡፡
የሚጠብቀንን ገድላችንን እንፈፅምና ድል እንንሳ አለችው የብረት ጋኑን ሲነድ ሳየው በምንጭ ላይ በዝቶ እንደሚወርድ ጠል ሁኖ አየዋለሁና፡፡ ቅዱሳንም ይህንን ሲነጋገሩ አንስተው ከብረት ጋኑ ውስጥ ጨመሯቸው፡፡ በውስጡም አንገትን የሚቆለምም ልብን የሚያጣምም ሆድን የሚሰነጥቅ ስርንም የሚበጥስ መሳሪያ አለበት፡፡
ከዚህ በኋላ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደና የብረት ጋኑን እሳት አጠፋው ከቅዱሳንም አንዱን እንኳን ሳይነካው የብረት ጋን ማቃጠሉና መፍላቱ ፀጥ አሉ፡፡ እግዚአብሔር ኃጢያታቸውን ይቅር ይላቸው ዘንድ ለኃጥአንም ወደ እግዚአብሔር ይፀልይላቸው እኛም በየወሩ በዓሉን እያከበርን ይህን ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤልን አማላጅ ወዳጅ እናድርገው፡፡
ሹም እለእስክድሮስም አስራ አራት የተሳሉና የጋሉ ብረቶች  ያመጡ ዘንድ ዳግመኛ አዘዘ፡፡ ሰባቱን በእናቱ አካል ሰባቱን በሱ አካል ውስጥ ይተክሉ ዘንድ ከነዚሁም ሁለቱን በጆሮዎቹ ሁለቱን በዓይኖቹ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ አንዱን በልቡ ይተክሉ ዘንድ፡፡
ያንግዜ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደና እሳቱን አጠፋው እሳቱም እንደ በረዶ ቀዘቀዘ፡፡ ዳግመኛም የሕጻኑን እራስ ከነቆዳው ገፈው በእሳት ውስጥ ይጨምሩ አንድ ሹም አዘዘ፡፡ ዳግመኛው መልአክ መጥቶ ይህንን መከራ ከሱ አራቀለት፡፡
ዳግመኛም በመቃን ውስጥ ጨመረው በገመድ እንዲሰቅሉት አዘዘ፡፡ ከዚህም መልአኩ አዳነው፡፡
ልመናው አገልጋዩ ይጠብቀው፡፡ ለዘለዓለሙ አሜን!!


ይህ ነው እንግዲህ በታላቅ ድምቀት በዛሬው ዕለት የምናከብረው ፡፡ ሐምሌ 19፤
የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል በረከትና ተራዳይነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

የባለፈው ዓመት( ሐምሌ 19፣2003) ክብረ በዓል ድባብ ምን ይመስል እንደነበር ማንበብ ለምትፈልጉ ...የገብርኤል ድባብ.. ይጫኑ፡፡




5 comments:

  1. Ameeeen! Ye Melaku Ye Qidus Gebriel Amalajinet Ena tibeqa Ke Hulachinim Gar Yihun.

    ReplyDelete
  2. የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል በረከትና ተራዳይነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ አሜን::

    ReplyDelete
  3. Kalehiwot yasemalen.

    ReplyDelete