ቤቱ ያለ ወትሮው ብርሃን የሆነ መሠለኝ "... ነጋ እንዴ?..." ብዬ ግድግዳው ላይ ያለውን ትልቁን ሠዓት አየሁት:: ከጠዋቱ 12:40 ይላል:: ዋው በክረምት እንዲህ ዓይነት አየርና የፀሀይ ወጋገን ማየት ከእንቅልፉ ለሚነሣ ሠው ድካሙን አላቆ ኀይልን ይሠጣል:: ያው መነሣት አይቀርም ተነሣሁና ልብሴን ለባብሼ ወደሥራ ለመሄድ ሽርጉድ ጀመርኩ:: ዕለቱ ቅዱስ ገብርኤል ህፃን 'ቂርቆስ' እና እናቱን 'እየሉጣን' ከመከራ ና ሥቃይ ያዳነበት በመሆኑ በኢ.ኦ.ተ.ቤ. አማኞች ዘንድ በታላቅ ክብርና ድምቀት ይከበራል:: ገብርኤል ደግሞ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነው:: ጥሎብኝ በፍቅር እወደውለሁ:: ተመስገን ብዬ ወደ ስራዬ ለመሄድ ከቤት ወጣሁ:: ከዚህ በኃላ ነው ይህን ፅሑፍ እንድፅፍ ያነሣሣኝ ነገር የተጀመረው:: አካባቢው በሚያምር ደመና ይሁን ጭስ ተሞልቷል:: ጭሱ ከየት ይምጣ ወይም ደመናው ለጊዜው ግልፅ አይደለም:: ያም ቢሆን የሆነ አዲስ ነገር እየተካሄደ እንዳለ ያስታውቃል:: ... መዓዛ...'ጥንታዊ' ድባብ...ዝም ያለ ጩኸት::
"...እንኳን አደረሠህ ልጅ ብስራት..." የጐረቤታችን የወ/ሮ ፈለቁ ሠላምታ ሁሉን ነገር በአንዴ ግልፅ አደረገልኝ ::
"..እንኳን አብሮ አደረሠን ፈሌ ::" መልስ ሠጠኹ:: ኡፎይይ...በመላ ሠውነቴ ደስ የሚል ስሜት ተሠማኝ:: ቅልል አለኝ:: ... ለምን?.. አላውቅም::
ወደዋናው ጐዳና እንደደረስኩ በዓሉን ሊያከብሩ ወደ 'ጊቢ ገብርኤል' የሚሄዱ በጣም ብዙ ሠዎች የመንገዱን ግራና ቀኝ ይዘው በእንኳን አደረሠን ስሜት ይሄዳሉ:: የሚገርመው ሁሉም ፊት ላይ ደስታ ይታያል:: ውስጤ ወደስራ ሳይሆን ወደ ገብርኤል ሂድ... ሂድ... አክብር... አለኝ:: በዚህ መሠል ስልኬ ጠራ::
"ሄሎ"
"Good Morning Mr.Bisrat" የአንድ ሴኔጋላዊ ወዳጄ ስልክ ነበር:: ሠላምታ ከተለዋወጥን በኃላ የገረመውን ነገር አጫወተኝ::
"...am on my way to office and there are a lot of people who covered in white cloths, shirts and hats! Is there any special occasion or ceremony in Addis...?"
(ወደ ቢሮዬ እየተጓ ዝኩኝ ነጭ የለበሡ የበዙ ሠዎች መንገድ ላይ አያለሁ:: የተለየ አዲስ ዝግጅት አለ እንዴ?) አለኝ::
ለሀገሩ እንግዳ እንደሆነና በቅርቡ ወደ ኢትዮዽያ እንደመጣ ስለማውቅ ሁሉን ነገር አጫወትኩት:: ደስም አለው::
"...you know, you Ethiopian are so honest & religious. God'll bless & care of you all the the time. You've your own history...belief.. & culture: me and my whole family has a good feeling about you....by the way am so happy if you take me to your church only when you are free...)
(እናንተ ኢትዮዽያውያን ሀይማኖተኛ ህዝቦች ናችሁ :: እግዚሐብሔር ሁሌም ይጠብቃችኃ.ል:: ባህል..ታሪክ.. እምነታችሁ ሁሉ ከሁሉ የተለየ ነው:: ... ቤተሠቦቼም እኔም ለእናንተ...ለባህላችሁ ክብር አለን::)
ይህን ብሎ ወደ ገብርኤል ቤ/ክ ይዤው እንድሄድ ጠየቀኝ:: ውስጤ ደስታ ተሠማው:: ምክንያቱም የውጭ ሀገር ዲፕሎማት (Diplomat) ከመሆኑም በላይ ሙስሊም ነው:: በኢትዮዽያዊነቴ ኮራኹኝ:: እምነቴ አኮራኝ:: ህይወቴ አኮራኝ:: በፍጥነትም ደስተኛ መሆኔን ነግሬው ስልኩ ተዘጋ::
ከፊት ለፊቴ እዛው ከደብሩ አድረው ይሁን ለሊት ሄደው የሚመለሡ እናቶች የባህል ልብሳቸውን ለብሠው ይመጣሉ:: "...የህዝቡ መብዛት... የወጣቱ ሃይማኖተኛና ታዛዥ መሆን እየተጯጯሁና በአግራሞት ያወራሉ:: በመሐላቸው ትንሿ ሴት ልጅ ወደፊት ወደጐን ትሮጣለች:: .... ያምራሉ:: አረንጓዴ ቀጤማ ና ነጭ በነጭ ማድረጋቸው ኢትዮዽያዊትን አላብሷቸዋል:: 'እግዚአብሔር' ይመስገን አልኩ:: በውስጤ ጥለውኝ አለፉ:: ዞሬ ድጋሚ ተመለከትኳቸው::
ቢሮዬ እየደረስኩኝ ነው.... ዐይኔ ሌሎችን ተመለከተ:: ሁለት ወንዶችና አንዲት እንስት ከፊት ለፊቴ ዘና ብለው እየሣቁ ነው እርግጠኛ ሆንኩ ወደ ቤተክርስቲያን እየሄዱ እንደሆነ:: ልጅቷ ነጠላ አድርጋ ሽፍንፍን ብላለች:: ......ሌላ ውበት!!!:: ሥራ ባልኖረ! ይህ ሁሉ በጠዋቱ.... ?
ከቤቱ... ከደብሩ ደግሞ ምን ያህል ያምር ይሆን? ብዬ እራሴን ጠየኩኝ:: ልጆቹን ወደኃ.ላ ጥያቸው ሄድኩ:: ሣቃቸው ባይርቀኝም::!
"....ደህና አደርክ? እንኳን አደረሠህ::" አልኩት አለቃዬን ::
ፍፁም ንቁ ሆኛለሁ:: የገብርኤል ድባብ ውስጤን ስለሞላው:: "ተመስጌን!" አልኩ ወንበሬ ላይ ተመቻችቼ በመቀመጥ::
nice topic... keep it up brother... May God help u...
ReplyDeleteሌላኛው ምርጥ ተተኪ::
ReplyDeleteWow I am also sooooo proud to be an ethiopian and also orthodox christian.God bless you
ReplyDeleteHulachihunim ameseginalehu! Yeteshalena Yechalikutin lemaderge emokeralehu. Lelaw yaligebagn yeman mitik new yemehonew? Erigitegna negn melikam sew yihonal. Any way Egize'habihe're yakibirilign.
ReplyDeleteብስራትዬ በርታ በርታ በርታ እግዚአብሔር መንገድህን ሁሉ ቀና ያድርገው !!!!!!!!!!!
ReplyDeletejust wonderful.keep it up...
ReplyDeletegood job keep it up May God bless u !!
ReplyDeleteBisrat betam des yemele nea egziyabher amelake eske mechershaw yeredeh
ReplyDeleteselam