ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Saturday, June 25, 2011

ዘማሪ እስጢፋኖስ ሣህሌ (ቄሴ) ምእመኑን ይቅርታ ጠየቀ::

ዘማሪ እስጢፋኖስ ሣህሌ (ቄሴ) ምእመኑን ይቅርታ እየጠየቀ ነው
(ደጀ ሰላም፤ ጁን 24/2011)፦


“እኛ የአባቶችን አገልግሎት ለማስረሳት ሠራን፤ የእነርሱም ኀዘን እኛን ጣለን፡፡›› (እስጢፋኖስ ሣህሌ)
በተለያዩ አህጉረ ስብከት ሕገ ወጥ ሰባክያንንና እና ዘማርያንን የመከላከሉ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፤
በጋሻው ደሳለኝ “በቪሲዲ የተሰራጨብኝ ማስረጃ በአኒሜሽን የተቀናበረ ነው!!›› አለ
በቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ዋዜማ በሜጋ - ሞያሌ መንገድ የመኪና አደጋ የደረሰባቸው ምርትነሽ ጥላሁን እና አሰግድ ሣህሉ በሕክምና ላይ ናቸው
በደብረ አሚን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ወጣቶች ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም የአካላዊ ቅጣት ርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል አንዱ የነበረው ዘማሪ እስጢፋኖስ ሣህሌ (በቅጽል ስሙ ቄሴ)
የሕገ ወጥ ‹ሰባክያን› እና ‹ዘማርያን› አካል እና አባል በመሆን ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች የተጸጸተ መሆኑን በመግለጽ ካህናት እና ምእመናን ይቅርታ እንዲያደርጉለት እየጠየቀ ነው፡፡ “እኔ ከእነርሱ የተለየሁት ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ነው፤በዘማሪ ፈቃዱ አማረ የጋብቻ ሥነ ሥርዐት ዕለት ወጣቶቹ የወሰዱት ርምጃ ስለ ቅንዐተ ቤተ ክርስቲያን የፈጸሙት እንጂ በግል ጥላቻ ወይም በስሜታዊነት ተነሣስተው አለመሆኑን አምኜበታለሁ” ያለው ዘማሪ እስጢፋኖስ ከሕገ ወጥ ቡድኑ ጋራ ለረጅም ጊዜ አብሮ ስለቆየበት ሁኔታ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ “ከዛሬ ነገ የተሻለ ነገር አያለሁ በሚል ተስፋ በማድረግ ነበር” ብሏል፡፡

ዘማሪ እስጢፋኖስ ሕገ ወጥ ‹ሰባክያኑ› እና ‹ዘማርያኑ› ዐውደ ምሕረቱን የሣቅ ቀን/መድረክ ሲያስመስሉ፣ ካህናቱን እና መሪጌቶቹን በስድብ ሲያሸማቅቁ፣ ራስን ባለመግዛት የተለያዩ አስነዋሪ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ በግልጽ ይቃወማቸው እንደ ነበር ለማስረዳት በመሞከር ላይ ይገኛል፡፡ ከሁሉም ነገር በላይ ለሰዓታቱ፣ ለማሕሌቱ እና ለቅዳሴው እንዳይተጋ “ባዶ ቤተ ክርስቲያን ሄደህ ምን ታደርጋለህ?›› እያሉ ያደረሱበት ጫና፣ ይሄዱባቸው በነበሩ አጥቢያዎች በአብዛኞቹ ካህናቱ እና መዘምራኑ የእነርሱን ሽሙጥና ዘለፋ በመሸሽ በመንደር ርቀው ይቆዩ የነበሩበት ሁኔታ በእጅጉ እንደሚያሳዝነው ተናግሯል - ዘማሪ እስጢፋኖስ፡፡ መሠረተ እምነትን በማፋለስ፣ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ በሚፈጽሙት ድርጊት መቼም ተባብሯቸው እንደማያውቅ ያስረዳው ዘማሪው፣ “በየዋህነት፣ በትምህርት ማነስ ምክንያት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አብሬያቸው በመቆየቴ በፈጸምሁት ስሕተት ቤተ ክርስቲያኔን አሳዝኛለሁ፤ በውስጣቸው ብቆይም በአቋም መለየቴን ገልጬ ማሳየት ነበረብኝ” ብሏል፡፡

“ተሐድሶ የለም›› እያሉ በዐውደ ምሕረት ለማስተባበል የሚሞክሩትን የሕገ ቡድኑን አባላት የተቃወመው ዘማሪ እስጢፋኖስ፣ “የእነርሱ ዋነኛ ዓላማ የአባቶችን አገልግሎት ማስረሳት ነው፤ እኛ የአባቶችን አገልግሎት ለማስረሳት ሠራን፤ የእነርሱም ኀዘን እኛን ጣለን” በማለት የተሰማውን ቁጭት ገልጧል፡፡ የይቅርታ ጥያቄውን ለብዙኀን መገናኛዎች በሚሰጣቸው ቃለ ምልልሶችና በተለያዩ አጋጣሚዎች እያቀረበ የሚገኘው ዘማሪ እስጢፋኖስ ከጥቃቱ ወዲህ በተለይም አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ የተቋረጠ መሆኑን በመግለጽ ወደ አገልግሎቱ ተመልሶ ለበደሉ መካስ እንደሚሻ ተናግሯል፡፡

በደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል እና በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ሰበካዎች ባሉ ካህናት እና ምእመናን ዘንድ የሚታወቀው ዘማሪ እስጢፋኖስ ሦስት ካሴቶች ለብቻው፣ አምስት ደግሞ በጋራ የሠራቸው የ”መዝሙራት›› ሥራዎች አሉት፡፡ “ቄሴ” የሚለውን ቅጽል ስም ያገኘው በልጅነት ዕድሜው በአምሳለ ካህን ጠምጥሞ ጠበል በመርጨቱ፣ በክብረ በዓላት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እየዞረ በመዘመሩ መሆኑን በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ፡፡ በማለዳው ባጣቸው ወላጆቹ ምትክ የሁለቱ አጥቢያ ምእመናን አባትም እናትም ሆነው ያሳደጉት ዘማሪ እስጢፋኖስ ወደ ገዳማት በሚደረጉ ጉዞዎች ላይ በጨረታ በሚሰበሰቡ የርዳታ ማስተባበር ተግባራት የተመሰገነ ስጦታ እንዳለው ብዙዎች ይመሰክሩለታል፡፡ “ለአገልግሎት መሰሰት አይታይበትም፤ ልግመኝነትን አያውቅም›› የሚሉት የቅርብ ወዳጆቹ በሐመረ ኖኅ ማኅበር በኩል ለቅዱስ ፊልጶስ ቤተ ክርስቲያን/አዲስ አበባ/፣ በማኅበረ አቡነ አሮን መንክራዊ አማካይነት ለአቡነ አሮን ገዳም በተደረገው የርዳታ ማሰባሰብ ሥራ ያደረገውን ተሳትፎ ያስታውሳሉ፡፡

በሌላ በኩል በጋሻው ደሳለኝ በበኩሉ በተለያዩ ሚዲያዎች እየወጡ ያሉ የስሕተት ትምርቶቹን እርሱ እንዳልተናገራቸው ይልቁንም እርሱ እንደተናገራቸው ተደርጎ “በአኒሜሽን” መቀናበራቸውን ለማስተባበል በመሞከር ላይ ነው።

9 comments:

 1. egziabher amlak libona yistachew yisten !!!!!!

  ReplyDelete
 2. Egziyabher ameleke mechershchenen yasamerew fiker yesetn

  ReplyDelete
 3. OH God....egziabeher yisteh bezu gize tehadiso sibal bizum tikuret alsetehutem yeneber ena yebegashawun mekelkel lemin endehone bedenb mawok efeleg neber ahun negeru bedenb eyegebagn new maletem betekrstian wust hunew lela haymanot yemisebku alu malet new. gin estifanos egiabeher yibarkeh. you know what God will reveal what is true. "reformation" is not for the church rather those who believe in reformation need to reformed by church. this reformation is drive from foreigners like re- engineering (BPR) so do you think(who believe in reformation) is need for our church?
  any ways thank you bisrat and estifanos.

  ReplyDelete
 4. egziabher yisteh .gen bawdemeheret bizu meneger yinorebetal bezuwochachen kmerrej rekenenal tewat na mata dejeselm benehnem gen yehen hulu gud yeminegren yelem .ante gen berta EGZIABHER YABERTAH

  ReplyDelete
 5. enkwen Egizabher lebonhen melaselhe. Bagelgelothem yatsnhe, mewdake syhone mensate yekabedal yanta metstset lebezhanoch mesale newe. egziabher yaberthe

  ReplyDelete
 6. temles GOD yekebelehal AMEN SELMUN YESTEN AMEN.

  ReplyDelete
 7. mahibere kidusanochin yemimekir tefasa minew? endekidusanyasibu zenid linegerachew yigebal

  ReplyDelete
 8. በደብረ አሚን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ ወጣቶች ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም የአካላዊ ቅጣት ርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል .............ክርስቶስ ሲመቶት መልሶ አልተማታም.....ዛፍ ክፍሪው ይታውቃል .......አግዚአብሂር ማስተዋል ይስጣቹሁ

  ReplyDelete
 9. Its like you learn my thoughts! You seem to understand a
  lot approximately this, such as you wrote the guide in it
  or something. I think that you just can do with some p.c. to drive the message home
  a little bit, however instead of that, this is great blog.
  An excellent read. I will definitely be back.
  Feel free to visit my blog : Bonuses

  ReplyDelete