በብስራት ገብሬ
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና። (፩ኛ ቆሮ 1፡18)
.
. . . የሁሉ መጀመሪያ 326 ዓ.ም. .
. . " መስከረም ባበባው
ሠርግ በጭብጨባው
ይታወቃል” ይላሉ
አበው። ክረምቱ አልፎ ሜዳና ተራራው በአበባ ሲሸፈን፣አዝመራው ሲያሸት አንድም
መስከረም ርዕሰ
ዓውደ ዓመት፣
የዘመን መለወጫ
በመሆኑ ወርኃ
አደይ ወወርኃ
ጽጌ ተብሏል።
እናም ኢትዮጵያውያን
በርዕሰ በዓልነት
ታላቅ ማዕዘን
ላይ ያስቀመጡት
ወርኃ መስከረም፣
ኃይማኖታዊና ባህላዊ
በዓላትን አቅፏል።
ከነዚህም ውስጥ
ከዕንቁጣጣሽ በዓል
ቀጥሎ በሠፊው
የሚታወቀው በዓለ
መስቀል
ነው።
ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ የሰው
ልጆችን ለማዳን
የተሰቀለበት ቅዱስ
መስቀል ሕሙማንን
በመፈወሱ ምክንያት
በርካታ አሕዛብ
ክርስቲያን እንዲሆኑ
አስችሏል፡፡ በተአምራዊነቱና
በክርስቲያኖች ዘንድ
ከፍተኛ ክብር
የተሰጠው በመሆኑና ይህን የተመለከቱ አይሁድ
ቅዱስ መስቀሉን
በአንድ የቆሻሻ
ማጠራቀሚያ ቦታ
እንዲቀበር አደረጉ፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች
በየቀኑ ቆሻሻ
ስለሚጥሉበት ቦታው
ወደተራራነት ተቀየረ፡፡
ምንም እንኳን
መስቀሉን ለማውጣት
ባይችሉም በኢየሩሳሌም
የነበሩ ክርስቲያኖች
ቦታውን ያውቁት
ነበር፡፡ በሰባ
ዓመተ ምሕረት
በጥጦስ ወረራ
ኢየሩሳሌም ስለጠፋች
በዚያ የነበሩ
ክርስቲያኖች ተሰደዱ፡፡
የተቀበረበትን ቦታ
የሚያውቅ ባለመገኘቱ
መስቀሉ ከ300
ዓመታት በላይ
ተዳፍኖ /ተቀብሮ/
ኖረ፡፡
ጉዞ ወደ ኢየሩሳሌም
በ326 ዓ.ም. የንጉሥ
ቆስጠንጢኖስ እናት
ንግሥት ዕሌኒ
ቅዱስ መስቀሉን
ለመፈለግ ወደ
ኢየሩሳሌም ጉዞ
አደረገች፡፡ እዚያም
ደርሳ. . .
ጉብታ የሆነውን ሁሉ ብታስቆፍር መስቀሉ ያለበትን ቦታ ማግኘት አልቻለችም፤ ሰውም ብትጠይቅ የሚያውቅ አልተገኘም፡፡ በመጨረሻም የመስቀሉ መገኘት የእግዚአብሔር ፈቀድ ነበርና አንድ ይሁድ አረጋዊ የታሪክ አዋቂና ሽማግሌ አግኝታ ቅዱስ መስቀሉ የተቀበረበትን ና የተጣለበትን አካባቢ ለማወቅ ። “አንቺም በከንቱ አትድከሚ ስውንም አታድክሚ እንጨትአሰብስበሽ እጣን አፍሽበት በእሳትም አያይዢው የእጣኑ ጢስ ወደላይ ወጥቶ ወደታች ሲመለስ አቅጣጫውን አይተሽ አስቆፍሪውበዚህ ምልክት ታገኚዋለሽ” አላት እርሷም ያላትን ሁሉ አደረገች። ዕንጨት ደምራ በዚያ ላይም ዕጣን ጨምራ በእሳት ለኮሰችው፤ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ መስቀሉ ያለበትን ቦታ በጣት ጠቅሶ እንደማሳየት ያህል አመለከተ፡፡ ንግሥት ዕሌኒም ጢሱ ያረፈበት ቦታ ቅዱስ መስቀሉ የተቀበረበት እንደሆነ አመነች፡፡ ይህ ይሁድ አረጋዊ የታሪክ አዋቂና ሽማግሌ በኋላ በክርስቶስ አምኖ ተጠምቋል፤ ስሙም ኪርያኮስ ተብሏል፡፡
በዚህም መሠረት ከመስከረም 17 ቀን አስጀምራ እስከ መጋቢት 10 ቀን ሌሊትና ቀን ለሰባት ወራት ያህል የጉድፍን ኮረብታ ቆፍረው ቆሻሻውንም ካስወገዱ በኋላ ሦስት መስቀሎች ተገኙ ፡፡ የጌታም መስቀል ሙት በማስነሣቱ ተለይቶ ታውቋል፡፡ መስቀሉ የተገኘው መጋቢት 10 ቀን 326 ዓ. ም. ነበር፡፡ ቅድስት ዕሌኒ ይህን ተአምር በማየቷ እጅግ ደስ አላት፡፡ ሕዝቡም ሁሉ መስቀሉን እየዳሰሱ ኪርያላይሶን እያሉም በመዘመር ደስታና ሐሴት አደረጉ፡፡ ቀኑ መሽቶ ጨለማ በሆነ ጊዜም የኢየሩሳሌም ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስና ንግሥት ዕሌኒ፣ ሠራዊቱና ሕዝቡ በሰልፍ በችቦ መብራት መዝሙር እየዘመሩ ቅዱስ መስቀሉን ወደ ቤተ ክርስቲያን ወስደው በአንድ የጸሎት ቤት አኖሩት፡፡ በኋላም በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዕብነ መሠረት ተቀምጦ ለመሰቀሉ መታሰቢያ ቤተክርስቲያን ተሰርቶ ተመርቆ የገባው (ቅዳሴ ቤቱ) የተከበረው መስከረም 17 ቀን 326 ዓ. ም. ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ሁለቱም ዕለታት ይከበራሉ፤ በደማቅ ሁኔታና በመጀመሪያ ደረጃ የሚከበረው ግን መስከረም 17 ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት መጋቢት 10 ቀን ሁልጊዜም በዐቢይ ጾም ወቅት የሚውል መሆኑና ለመስቀሉ የተሠራው ቤተ መቅደስ የከበረው መስከረም 17 በመሆኑ ነው፡፡

የመስቀል ደመራ በዓል
ደመራ የሚለው
ቃል - ደመረ፣ ጨመረ፣ አንድ አደረገ፤ ከሚለው የግእዝ ቃል የተወረሰ ሲሆን መቀላቀልን፣ መገናኘትን፣መሰብሰብን፣ መጣመርን፣ መዋሐድን በአጠቃላይ ሱታፌን፣ አንድነትን እና ኅብረትን ያመለክታል፡፡ ቅዱስ መስቀሉ በተገኘበትቦታም ስለሆነም ደመራ ዕንጨቶች የሚደመሩበት የበዓለ መስቀል ዋዜማ ነው፡፡ቤተ
ክርስቲያናችን ከምታከብራቸው
ዘጠኙ የጌታችን
ንዑሳን በዓላት
አንዱ
በዓል ነው፡፡
መስቀል የሰላማችንና
የድኅነታችን የመቀደሳችን
አርማ፣ ኢየሱስ
ክርስቶስ የሰውን
ልጆች ለማዳን፥የዘላለም
ሕይወትን ለመስጠት
መስዋዕትነት የከፈለበት
ቅዱስ ሥጋውን
ክቡር ደሙን
ያፈሰሰበት መንበር፥
ሲሆን አምላካችንን
የምንመለከትበት መስታወት
ነው።
ይህ ዕለት ከ300 ዓመታት በላይ ጠፍቶ የነበረውን ቅዱስ መስቀል በንግሥት ዕሌኒ አማካኝነት መገኘቱን የምንዘክርበት በዚህም ደስ የምንሰኝበት ዕለት ነው፡፡
ይህ ዕለት ከ300 ዓመታት በላይ ጠፍቶ የነበረውን ቅዱስ መስቀል በንግሥት ዕሌኒ አማካኝነት መገኘቱን የምንዘክርበት በዚህም ደስ የምንሰኝበት ዕለት ነው፡፡
በዓለ
መስቀል፣
በክርስትና ኃይማኖት
ጌታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ በቀራንዮ
የተሰቀለበት መስቀል
በአይሁድ ከተቀበረበት
ሥፍራ መገኘቱን
ማስታወሻ በዓል
ሲሆን በምዕራብም
ምስራቅም አብያተ ክርስቲያት ይሄንን
መታሰቢያ መስከረም 3 ቀን
ሲያከብሩት የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ
በየዓመቱ መስከረም 17 ቀን
ታከብራለች።
መስቀል
ምንም እንኳ
በክርስትና ኃይማኖት
ተከታዮች ዘንድ፣
የራሱ የሆነ
ትርጉም ያለው
ቢሆንም ከኃይማኖታዊ
ክንዋኔው ባሻገር፣
ባህላዊ በሆነ
ገፅታ የሚያከብሩት
የኅብረተሰብ ክፍሎች
ቀላል የሚባሉ
አይደሉም። ለምሣሌ
በደቡብ ኢትዮጵያ የሚካኼዱት
ልዩ ልዩ
ዝግጅቶችና ሬቻ
ተብሎ የሚታወቀው
የኦሮሞ ህዝብ
በዓል በዋናነት
የሚጠቀሱ ናቸው።
በነገራችን
ላይ ስለመስቀል
በዓል ስናነሳ፣
ከላይ እንደተገለጸው
ሌሎችም አብያተ
ክርሲያናት ቢያከብሩትም
በልዩ ክብር
እና ደማቅ
ሁኔታ ግን
የታሰበው በተዋህዶ
ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች
ዘንድ ብቻ
መሆኑን ማውሳት
ያስፈልጋል። የፕሮቴስታንት
እምነት ተከታዮች
ወይም ክርስቲያኖች
በኢየሱስ ተሰቅሎ
መሞትና በመስቀሉ
የማይረሳ ውለታ
የሰው ልጅ
መዳኑን ቢያምኑም
እንደ ኦርቶዶክስና
ሌሎች ጥንታውያን
አብያተ ክርስቲያናት
ትውፊትን ስለማይቀበሉ፣
የመስቀል በዓልን
ኃይማኖታዊ በዓል
አድርገው አይመለከቱትም።
ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም
‘’መስቀሌን በመስቀልያ ሥፍራ አስቀምጠው”
‘’መስቀሌን በመስቀልያ ሥፍራ አስቀምጠው”
በ15ኛው
መቶ ክፍለ
ዘመን በአገራችን በተደጋጋሚ ያስቸገረውን ረኀብ እና በሽታ ለማስወገድ በአፄ
ዳዊት ዘመነ
መንግሥት፣ ኢየሱስ
ክርስቶሰ በቀራንዮ
የተሰቀለበት ቀኝ
እጁ ያረፈበት
ግማደ መስቀል
ወደ ኢትዮጵያ
መጥቶ መቀመጡ
ነው።ይህም የሆነው መስከረም 10 ቀን ነው፡፡ ስለዚህ
መስቀል መምጣት
የቤተክርስቲያኗ ጸሐፍት
በተለያዩ ሠነዶቻቸው
የተረኩ ሲሆን፣
ንጉሡ አፄ
ዳዊት ግማደ
መስቀሉን አስመጥተው
በኢትዮጵያ አድባራት
ሁሉ በመዞር፣
ሊያሳርፉበት ያልሞከሩበት
ቦታ አልነበረም፤
ነገር ግን
መሬቱ እየተንቀጠቀጠ
አስቸገረ። በመጨረሻ
ግን “አንብር
መስቀልዬ በዲበ
መስቀል። (መስቀሌን
በመስቀልያ ሥፍራ
አስቀምጠው)” የሚል
መለኮታዊ ምሪት
ስለደረሳቸው፣ አሁን
ግሼ አምባ
በሚባለው ሥፍራ
ላይ መስከረም
21 ቀን 1446 ዓ/ም ደብረ ከርቤ እንዲያርፍ ተደርጓል፡፡የግሸን
ደብረ ከርቤ ማርያም ሥፍራ መስቀልያ
መልክዐ ምድራዊ
አቀማመጥ ያለው
ነው።
ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ የሚያሻግረው ብቸኛው መንገድ
|
ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም፡- በአሁኑ ወሎ
ክፍለ ሃገር፣ አምባሰል ወረዳ ውስጥ ግሸን ተራራ
አናት ላይ የምትገኝ ቤ/ክርስቲያንናት። ለዚች ቤ/ክርስቲያን መግቢያ አንድ መንገድ ብቻ ነው። እንደ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ይህችቤተ
ክርስቲያን በየዘመኑ የተለያየ ስያሜን አግኝታለች።
- ከአጼ ድልናአድ ዘመን (866 ዓ.ም) እስከ 11ኛው ክፍለ ዘመን በአሁኑ ስያሜ (ደብረ ከርቤ) ትታወቅ ነበር።
- በ11ኛው ክፍለ ዘመን አጼ ላሊበላ ከቋጥኝ ድንጋይ ፈልፍለው እግዚአብሔር አብ የተሰኘ ቤ/ክርስቲያን በዚሁ ቦታ ሲያሰሩ ደብረ እግዚአብሔር በሚል ስም ታወቀች። ብዙ ሳይቆይ ግን ደብረ ነገስት ተባለች።
- በ1446 አጼ ዘርአ የዕቆብ ግማደ መስቀሉን በዚህ ስፍራ ሲያርፍ ደብረ ነገስት መባሏ ቀርቶ ደብረ ከርቤ ተባለች። በዚህጊዜ የነበረው የቤ/ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ መምህረ እስራኤል ዘ ደብረ ከርቤ ይባል ነበር።
- አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ግማደ መስቀሉን ይዘው እየገሰገስገሱ ስለመጡ በግዕዙ "ገሰ" ወይም በአማርኛው "ገሰገሰ" የሚለው ቃልለቦታው ስያሜ ሆነ። በዘመናት ሂደት ገስ ወደ ግሸን የሚለው ስያሜ ተዛወረ። አካባቢው በዚህ ስም ታወቀ።
የደብሩ መመስረትና
የመስቀል በዓል
እንደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ትውፊት፣ የግሸንን ደብር የመሰረታት አንድ ጻድቅ መነኩሴ ነበር። ይኽውም በ514 ዓ.ም፣ ከዘርዓ ያዕቆብ መነሳት
900 አመት በፊት ነበር። የሆኖ ሆኖ አካባቢው በአሁኑ ዘመን የሚታውቀው የኢየሱስ ክርስቶስን ግ ማደ መስቀል በማኖሩ ነው። አጼ ዘርአ ያዕቆብ በነገሱ ዘመን ወደ ሰናር ሄደው ግማደ መስቀሉንና ሌሎች ብዙ የቤ/ክርስቲያን ውድ ንዋያትን አምጥተው መስከርም
21፣ 1446 ዓ.ም ወደ ደብሩ በመውጣት በዘመኑ የነበሩትን አብያተ ክርስቲያናት እንደገና በማነጽ፤ በኋላም በእግዚአብሔር አብ ቤ/ክርስቲያን ጥግ በጥንቃቄ ጉድጓድ አስቆፍረው መስቀሉን በማስቀበርና
ባለቤታቸው ንግስት እሌኒ ደብረ ከርቤ ማርያም ቤ/ክርስቲያንን እንደገና በማሳነጽ ከፍተኛ ስራ አከናወኑ። ከ5 አመት በኋላ መስከርም
21፣ 1449 ጀምሮ የመስቀል በዓል በዚህ ዕለት መከበር ተጀመረ።
***************************************************************************************************** ምስጋና
·
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በብፅ አብነ ጎርጎርዮስ የሸዋ ሊቀ ጳጳስ፣
·
ለዲ/ን አሉላ መብራቱ
“ ……… ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሥጋውን የቆረሰበት፣ ደሙን ያፈሰሰበት እና ነፍሱን የካሰበት ቅዱስ መስቀል የፍቅር ፍጻሜ፣ የሰላም ማረጋገጫ እና የአንድነት ዙፋን ነው፡፡ ክርስቶስ በደሙ ለዋጀው ሕዝብ ቀዋሚ ዓርማ በሆነው ቅዱስ መስቀል ሰማያውያን እና ምድራውያን ታርቀዋል፡፡ መስቀል ለመላእክት እና ለሐዋርያት የስብከታቸው ማእከል፣ ለእኛ ለምናምንበትም ኀይል እና ጽንዕ ነው፡፡ ከአበው እንደ ወረስነው መስቀል በደረታችን ላይ፣ መስቀል በጣታችን ላይ፣ መስቀል በየልብሳችን ላይ፣ መስቀል በአብያተ ክርስቲያን ጉልላት፣ በር እና መስኮት ላይ፤ መስቀል በንዋያተ ቅድሳት ላይ፣ መስቀል በካህናት እጅ ላይ፣ የመስቀሉ ባለቤት እግዚኣ ሕያዋን ወሙታን ነውና መስቀል በሙታን መቃብር ላይ ሳይቀር ይገኛል - በዚህም ዘወትር እንሳለመዋለን፤ እንባረክበታለን፤ በረከት እና ረድኤትም እናገኝበታለን (ማቴ.10÷38)፡፡………………”
ደጀ ሰላም
enkwane abro adresen ejge btam dese ymile ngre nwe bzu ymalweqachwen ngre endaq redtognale breta egzabre ychemrelk
ReplyDeleteEjig merte aqerareb new ayeselechim. Bizuwoch attention lesetuke yigebale!! Tichelalehe Bisrat Ejig merte aqerareb new ayeselechim. Bizuwoch attention lesetuke yigebale!! Tichelalehe Bisrat
ReplyDeleteEgziyabher yeseteleg bezu negr new yawekubet yetemarekubet egziyabher ameleake kezeh yebelet endetesera yeredeh tebebuen yegelseleh bereta bereta Bissrat
ReplyDelete