ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Friday, September 9, 2011

አዲስ አበባ እና ፍርክና

                                                                                    በብስራት ገብሬ

ፍሪክ ፍርክርክ
ጥሬ እየተመገብክ
አተርና ክክ
አትሁን ዝርክርክ
ክክክክክከ…ክክክ

What’s up Guys. . .
             
        ብዙዎቻችን ' ፍሪክ ' የሚለውን ቃል ስንሰማ በአህምሯችን የሚመጣው ከተለመደው ወጣ ያለና አስቂኝ አይነት አለባበስ የሚለብሱ፤ ከአካባቢው ስርዓተ አኗኗር ያፈነገጡ(odd) የሆነ የአለባበስ ዘይቤ ያላቸውን ሠዎች ነው፡፡ ለውሻ ሳይሆን ለአንበሳ የሚከብድ ሠንሠለት ፣ትልልቅ ሸራ ወይም እስኒከር ጫማ፣የተቆጣጠረና ከታደለም የረዘመ ፀጉር(ድሬድ) ፣ የጆሮ ጌጥ (ሴቶች እንኳን ትተዋል ፕሮግራም ከሌለባቸው) አድርጎ የሚታይ ሠው እንደፍሪክ ይቆጠራል፡፡ በእርግጥም  ፍሪክ ነው፡፡ እብድ ያለ ፍሪክ፡፡
' ፍሪክ 'የሚለው ቃል ለብዙዎቻችን ግልፅ ነው፡፡ በወጣቶች ዘንድ ሳይታወቁ የኛ ሊሆኑና ሊመስሉ ከተቃረቡ ቃሎች መካከል አንዱ ነው፡፡ፍሪክ፡፡ ይህ ቃል የ’እንግሊዘኛ’ ቃል ከመሆኑ ባሻገር ትርጉሙም ከነባራዊ ሁኔታ የወጣ፤የፈነገጠ እብድ ማለት ነው፡፡

       “… እኔ ይህንን አለባበሴን ቀይር ከምትለኝ . . .” አንዱ ጓደኛዬ ነው ስለአለባበሱ ጠይቄው የመለሠልኝ፡፡ ቀይር ከምትለኝ ራቁትህን ሂድ ብትለኝ ይቀለኛል ብሎኝ ነበር በአንድ ወቅት፡፡ ደግነቱ ሱሪውን በማንገቻ ይታጠቃል እንጂ… ሱሪው ካሁን አሁን ወለቀ፣ጉድ ፈላ የሚስብል ነው፡፡ሳያውቀው ቀሚስ የማድረግ ፍላጎት ይኖረው ይሆን? እኔ አላውቅም፡፡ ግን ይመስላል፡፡
  በአንድ ወቅት ሰው ልሸኝ ቦሌ አየር ማረፊያ ሄጄ(Bole Airport) አንድ አባት ከፍተሻ ሠራተኞች ጋር ፀብ ገጥመዋል፡፡ “እንዴት ! ቀበቶ ፍታ ትሉኛላችሁ፤እኔ ወንዱን…ምን ዓይነት ጊዜ መጣ? ” እያሉ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላሉ፡፡ በዚህ መሀል አንድ የጊዜው ወጣት የታዘዘውን ለማድረግ ሣያቅማማ ቀበቶውን ሲያወልቅ ያዪታል፡፡ይሄኔ ነበር ሁላችንንም ያሳቀንን ነገር የተናገሩት፡፡
“አሁን አንተን የወለደች እናት ወንድ ወለድኩ ትላለች ሴት አኩሪ! ብትሞት ይሻልሃል. . .” ልጁ መልስም ሳይሰጥ ተሸማቆ ሱሪውን በእጁ እንደያዘ ወደውስጥ ገባ፡፡እኛም ትንሽ ፈገግ አልን፡፡ እሳቸውም እኔ 'የመይሳው ካሳ ልጅ' በሚል ስሜት በአቋማቸ ፀኑ፡፡      
 እኚህ አባት አለባበሴን ቀይር ከምትለኝ ራቁቴን  . . . ያለውን ወዳጄም ቢያገኙት በጋሻ ደብድበው፤በጦር እንደሚወጉት አጠራጠርም፡፡ ከስፈለገም ሊቀብሩት ሁላ ይችላሉ፡፡
     ሁሌም የሚገርመኝና የሚደንቀኝ እነዚህ የእንዲህ ዓይነት አለባበስና አቀራረብ ያለባቸውን ፍሪክ የምንላቸው ወጣቶች የሆነ ነገራቸው ተመሳሳይነት፣የማንነት ቀውስ የሚባል ጣጣ አለባቸው፡፡ ይህን ለማረጋገጥ ወደ ከተማችን ክፍል ወደሆነው የማንነት ቀውስ ክፉኛ ያጠቃውን ቦሌ የሚባለውን አካባቢ ማየት በቂ ነው፡፡ ይህ አካባቢ ለእድገታችን ማሳያ ሳይሆን ለውድቀታችን ማሳያ ቦታ ነው፡፡ የህፃናቱ ከልክ በላይ መወፈር(እግዚአብሔር ይመስገን)፣ አማርኛ መናገር ኋላቀርነት የሚመስልበት ፊፍቲ ሴንት (50 cents) ቢዮንሴ (Beyonce) የነገሱበት ኢትዮጵያዊነት ፍፁም የጠፋበት የሞተና ማፈሪያ አካባቢ ነው፡፡እንደ ዕድል ሆኖ ጥቂት ኢትዮጵያውያን በአካባቢው ማግኘት ያቻል ይሆናል፡፡የምር ኢትዮጵያዊ የሆኑ፡፡ ‘ወንድ ከሆናችሁ በፊዚክስ(physics) ግጠሙኝ ’ እንዳለው የዪኒቨርሲቲ እንግሊዘኛ መምህር ከ ‘What’s up’ እስከ  ‘Keep in Touch’ ድረስ ያለው ጨዋታ በሙሉ በእንግሊዘኛ ነው፡፡ምንአልባትም አማርኛ ሆሄያትን መናገርም ሆነ ማንበብ አይችሉ ይሆናል፡፡ ታዲያ ይሄ ለማን ያጠቅማል? ለሀገር፣ለወገን የሚለውን ትተን እንኳን ለራሳቸውም አይጠቅሙም፡፡ እንግሊዘኛ መናገር ላይ ችግር ባይኖርም ቋንቋ መግባቢያ ነው፤ሌላ ምንም አይደለም፡፡ ባህል፣ስርዓት ግን ከመግባቢያነትም በላይ ነው፡፡የማንነት መገለጫ፡፡
       አንድ ጊዜ ከአንድ ጓደኛዬ ጋር የፈረደበት ቦሌ አካባቢ አለ የሚባለው ሲኒማ ቤት ፊልም ልናይ ሄድን፡፡የህፃናቱ እንግሊዘኛ ብቻ ተናጋሪ መሆን ሲያስገርመን አዋቂ ናቸው ያልናቸው(በሰውነት አቋም) ከህፃናቱ የባሱና ፍፁም አበሻዊነትን  አምርረው የሚጠሉ ይመስላሉ፡፡በዚህ የተናደደው ጓደኛዬ ‘እነዚህ የፈረንጅ አሻንጉሊቶች ይሄኔ እኮ ሒሳብ(Mathematics) ‘ F’ ነው ያላችው’ አለኝና ፈገግ አደረገኝ፡፡ በእርግጥም ለነሱ ሒሳብ፣ፊዚክስ፣ኬሚስትሪ አይምጣባቸው. . . ያው እሱ እንዳለው ‘ F ’ ነው!   
       የማይገባኝና የሚያስቀኝ ነገር ዘመናዊነት ሱሪ እታች በማውረድ መገለፁ ነው፡፡ሠፍቷቸው ይሆን ወይስ አሜሪካ ያሉትን እስረኛ ወንድሞቻቸውን ለማስታወስ ብለው ይሆን? ልረዳው አልቻልኩም፡፡ እዚህ ዴዴሣ እስር ቤት ያሉትን ቢያስታውሱ ከሁሉ ይቀላል፡፡
ዘመናዊነት እንደተባለው  የንጉስ ምኒሊክን ፎቶ ሲያሳዩን አለማወቅ ወይንስ አንድ የውጪ ሀገር ዘፈንን መዝፈን ይሆን? ደሀውም ገንዘብ ሳይኖረው ቦብ ማርሊን(Bob Marley) መሆን ይፈልጋል፡፡ የማይታጠብ ፀጉር ያሳድጋል፡፡ ገንዘብ አለኝ የሚለውም፣የሠለጠነውም፣ዘመናዊ ነኝ የሚለውም የውጪ. . . የውጪ . . .የውጪ. . . . ኢትዮጵያም ልታብድ ደርሳለች:: አዲስ አበባም በአበዱ አበቦች እየተሞላች ነው፡፡
    
        ግልፅ ነው ማንም በሠዎች አስተሣሠብ፣አኗኗር ጣልቃ አይገባም፡፡ የሚገርመው ግን ሁሉም መጨረሻቸው ኢትዮጵያዊ መሆን፣የተረጋጋ መምሠል ነው፡፡ ያለሠንሠለት ልብስ፣አላደርግም የሚለውም ፍሪክ ነፍስ ሲያውቅ ያወልቀዋል፡፡ሱሬዬ ወርዶ ስራመድ የኋላ ኪሴን መንካት እፈልጋለሁ የሚለውም ትንሽ ህይወት ሲገባው ይተዋል፡፡ ፀጉርም ይቆረጣል፡፡ ታዲያ ‘መብሠሉ ላይቀር ማገዶ ይፈጃል’ እንደሚባል ከዚህ ሁሉ ዝባዝንኬ ንፁህ ሆኖ ቆንጆ፣ዘመናዊ ፤ ባህልና ስርዓት ያለው አካባቢን፣ማንነትን የማይረብሽ መሆኑ ይቻል የለ እንዴ?? መልሱን ለአንባቢው፡፡ ዘመናዊነት በአስተሣሠብ ቢለካ መልካም ነው፡፡ አረ መልካም ነው! 


መልካም ፍርክና
. . .Keep in touch

13 comments:

 1. Hahahaha....ante lije?

  ReplyDelete
 2. Interesting if any understand and change oneself.

  ReplyDelete
 3. Smart Explanation!!!.

  ReplyDelete
 4. Awesome!!! hahaha...

  ReplyDelete
 5. This is the negative impact of Globalization.

  ReplyDelete
 6. This is the negative impact of Globalization.

  ReplyDelete
 7. ....ታዲያ ‘መብሠሉ ላይቀር ማገዶ ይፈጃል’ እንደሚባል ከዚህ ሁሉ ዝባዝንኬ ንፁህ ሆኖ ቆንጆ፣ዘመናዊ ፤ ባህልና ስርዓት ያለው አካባቢን፣ማንነትን የማይረብሽ መሆኑ ይቻል የለ እንዴ?? መልሱን ለአንባቢው፡፡ ዘመናዊነት በአስሣሠብ ቢለካ መልካም ነው፡፡ አረ መልካም ነው!

  ReplyDelete
 8. i am happe is good news for ethiopan boys.

  ReplyDelete
 9. @ bisrat really good idea, but i have one question ur idea and daniel kibrets idea have a litle bit similarity maletm bole yehonu abat yemilew lay kahun befit daniel bezih guday tsfo silanebebhu yehasab sirkosh new weys yeneneroch medegagem yemi tiyake siletefeterebign new . katefahu sorry

  ReplyDelete
 10. እይታህ ተመችቶኛል…..ይህ ነገር ብዙ የተባለበት ግን የሚፈለገውን ያህል ሳይሆን ምንም ለውጥ ስላላመጣም ይመስለኛል……ማን ነበር በዚህ ጉዳይ ላይ እራሳችን እንድናይ ያረገን? ……እንትና እኮ ይህን ብሎ
  ነበር….የሚለውን የላይኛውን አይነት አስተያየት የምንሰማው……. እናም የሚፈለገው ለውጥ እስኪመጣ ዳጋግመህ ደጋግመህ ጻፍበት እላለሁ!!!!!

  ReplyDelete
 11. abo temechehegn!

  ReplyDelete