ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Monday, March 19, 2012

ክተት ወደ ዝቋላ


በዳንኤል ክብረት 

     ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የሚገኘው የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ደን በመንደድ ላይ መሆኑን የገዳሙ አባቶች እየተናገሩ ነው፡፡ እሳቱ መንደድ ከጀመረ ወደ ሃያአራት ሰዓት ሊጠጋ ነው፡፡ መንግሥት ከአካባቢው የውኃ ቦቴዎችን እና ወታደሮችንበማንቀሳቀስ ውኃውን ለማጥፋት ጥረት እያደረገ ቢሆንም እሳቱ ግን ወደ ገዳሙ በመጠጋት ላይ ነው፡፡

አሁን
 አማራጫችን አንድ ብቻ ነው፡፡ የዝቋላን ገዳም ከማጣታችን በፊት ያለንን ነገር ሁሉ ይዘን በተገኘው ትራንስፖርት ወደ ዝቋላ መትመም ብቻ፡፡ ወንበር ማርያም ድረስ የውኃቦቴዎቹ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ያለውን ባገኘነው ዕቃ ሁሉውኃውን ይዘን በመውጣት መረባረብ፡፡ ያለበለዚያ ግን የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ወደ ታሪክነት ይቀየራል፡፡

እነሆ
 ክርስትናችን የሚፈተንበት፣ ኢትዮጵያዊነታችንም የሚለካበት ጊዜ መጣ፣ በእሳትተቃጥለው ያቆዩትን ገዳም ከእሳት ማዳን ካልቻልን እንግዲህ የኛ መኖር ትርጉሙ ምንድን ነው?
መኪኖች ያሏችሁ አንቀሳቅሱ፣ ጉልበት ያላችሁ ተንቀሳቀሱ፣ ሌላም አማራጭ ያላችሁ በፍጥነት ተጓዙ፣እሳቱን በእምነት እንቅደመው፡፡

1 comment:

  1. ere fetare dereselen.ande bewaldeba ande bezekwala menew fetenachen beza.sel menenutena seltesewerute bahetaweyan belhe maren.[tg from canada]

    ReplyDelete