ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Sunday, July 17, 2011

ልብስ ሠፊውና........


ሲያያት ደነገጠ
ስታየው ፈጠጠ
መቼም መለካት አይደል ፈኑ?
ጠቀሳት ወደጐኑ
ሜትር አነሳ
ዘረጋው ባበሳ

አንገቷን ለካ
ፊቱ በውጤቱ ፈካ
ክንዷን በተራው ቀየሠ
ጡቶቿን በምክንያት ዳሠሠ
ወረደና ከወገቧ ደረሠ
ቀጠለና ዳሌዋን አሠሠ

ጠባብ ወገብ ሠፊ ዳሌ
ቢያጋጥመውም ሁሌ
ይህ ግን "....ሌላ" አለ ሣያስበው
"ምን አልክ የኔ ወንድም"አለች ኮረዳዋ
"እህህ... አዎ አልኩኝ እንዴ?"
ተደናገጠ ባንዴ

"እህህ..ነ..ገ ለሌላ ሙከራ
ትመጫለሽ ከዚህ ስፍራ"
አለና ፈገገ
ተስፋ እያረገ በነገ
ሊለካ ይችኑ ሎጋ
ሌላው ቀን ነገ ሲነጋ

1 comment: