ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Saturday, July 9, 2011

የመጀመሪያው ቀን.....


አየችው
ተያዩ
አየና ወደዳት
ቀኑ ማታ ነበር
ወደ ሆቴል ሄዱ

ሁለት እራት መጣ
ብርጭቆ ተጋጨ

አየችው
ተያዩ
አያት
ተሳሳቁ
በጠረጴዛው ስር
ጭኗ ጭኑን ነካው

ሲያያት
ፈገግ አለች
አየችው
ፈገገ
እጇን በእጁ ያዘ
ጠበቅ አደረጋት
ጠበቅ አረገችው
ከፈሉና ወጡ
በከሰለው ሌሊት
ሁለቱ ሊነዱ
ትንፋሻቸው ጋለ
ቤቱ ተቃጠለ
ፍራሹ ነደደ
ፍቅር ተያያዘ

(ገብረ ክርስቶስ ደስታ)

1 comment: