ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Thursday, November 8, 2012

የእርዳታ ጥሪ ለታሪካዊው እና የጥንታዊው የጋዴና ደብረ ነጎድጓድ ቅ/ዮሐንስ ቤተክርስቲያን


     ይህ ቤተክርስቲያን የሚገኜው በድቡብ ወሎ ሐገረ ስብከት በደሴ ዙሪያ ወረዳ ቤተ ክህነት ከደሴ ከተማ ወደ ወራኢሉ እና ለጋምቦ ወረዳ አቅጣጫ 64 . ርቀት ላይ የሚገኝ ነው
 
በሐገራችን ብሎም በሐገረ ስብከታችን በውጭ ሀገራት ሁሉ የሚታወቁ 3ታላቅ አድባራት አሉ እነርሱም 1. በሐይቅ አስተዳደር  የሚገኜው ደብረ እግዚአብሔር
2
. በደሴ ዙሪያ የሚገኙት መካነ ሥላሴ እና ደብረ ነጎድጓድ /ዮሐንስ ናቸው፡፡
 
     ይህ ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተው በአፄናኦድ ዘመን በከበሩ ድንጋዮች እና እነ /ላሊበላ ባነጹበት ተመሳሳይ ድንጋዮች የታነጸ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን በዚህ ቤተ ክርስቲያን የነበሩት  ካህናት ብዛት 1000/አንድ / ነበሩ፡ በዚህ ቤተ እግዚአብሔር በምላት መንፈሳዊ አገልግሎት እየተሰጠበት በገቢረ ተአምራቱ ካህናቱና ምዕመናኑ እየተጠቀሙበት ከኖረ በኋላ ክፉ ዘር የሆነ ሰይጣን የግብር ልጁን ግራኝ አህመድን በማስነሳት ህዳር 7ቀን 1524 . ይህን ቤተ ክርስቲያን አቃጥሎ ከካህናቱ አንዱ ሲተርፉ 999 ካህናት በአንድ ቀን ሰማዕት ሆነዋል በተለይም 5 ካህናት በቤተ መቅደስ በአገልግሎት ላይ እንዳሉ በደንደሳቸው አርዶአቸዋል የእነርሱም ደም እንደጎርፍ ፈሶ የተቀላቀለበት ወንዝ ደም ባሕር ተብሎ እስካሁን ይጠራል ሲጠጡት ጨው ጨው ይላል ምክንያቱ የእነዚህ የሰማዕታት ደም ስለተቀላቀለ ነው ፡፡

የጥንቱ ቤተ ክርስቲያን ከቃጠሎ የተረፉ 4ትክል አምዶች እና ዙሪያውን የተቃቀፉ 13 የጥድ አጸዶች ከዚህ ደብር መካነ ሥላሴ የሚያገናኝ የተዘጋ ዋሻ ያለው ሲሆን ይህን ቦታ ሄዶ ላየው ቤተ ክርስቲያኑ ቢቃጠልም ጸጋ እግዚአብሔር ያልተለየው  ከነ ግርማው ጉብ ብሎ የሚታይ ቦታ ነው ፡፡
600 ዓመት በላይ መስዋዕተ እግዚአብሔር ሳይሰዋበት የእጣኑ መዓዛ ሳይሸትበት የኖረ ሲሆን አሁን በእግዚአብሔር  ፈቃድ እሱ ወዶ ባስነሳቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች አነሳሺነት በሐገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ አትናቴዎስ እና በሐገረ ስብከቱ እና በደሴ ዙሪያ ቤተ ክህነት  የክፍል  ኃላፊዎች መልካም ፈቃድ ኮሚቴ ተዋቅሮ ከምዕመናን በሚገኝ ድጋፍ 3ወር ባልሞላ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ ወደ መጠናቀቅ ደርሶአል፡፡

ይህንን ቤተ ክርስቲያን ሁሉን ነገር አጠናቆ በዚሁ ዓመት በቅርብ ጊዜ  እንደሚመረቅ ይጠበቃል ፡፡
ስለዚህ አሁን እንደ አዲስ የሚቋቋም ቤተ ክርስቲያን በመሆኑ ብዙዎች ለዚህ ጥሪ ቀልጠፍ ብለው ምላሺ ሰጥተዋል  እርስዎም ለዚህ ጥንታዊ ደብር በገንዘብዎ፣በጉልበትዎ፣በጸሎትዎ፣በሙያዎ የበኩልዎን ድርሻ እንዲወጡ ይጠበቃል ፡፡
አሁን የሚቀሩን ስራዎች
  • ·         የቤተ ክርስቲያኑ የማጠናቀቂያ ስራዎች
  • ·         የቤተ ክርስቲያኑ ዕቃ ቤት/ሙዜም /መገንባት
  • ·         ለካህናት ማረፊያ ቤት
  • ·         የቤተ ክርስቲያኑ አጥር
  • ·         መንገድ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ 4ኪሎ ሜትር መንገድ ስራ
  • ·         ንዋየ ቅድሳት


ዙሪያውን በአሕዛብ የተከበበ 3ቤተ ሰብ ምዕመናንብቻ ያሉት በመሆኑ እና  ካህናት ከሌላ ገዳማት በማስመጣት ለካህናት ደመዎዝ በዚህ ስሪት ለመስራት ዘላቂ የልማት ስራ አስፈላጊ በመሆኑ እነዚህን ስራዎች ለመስራት በርካታ ገንዘብ የሚያስፈልግ በመሆኑ እርስዎም በሚቻልዎት አቅም ለመለገስ  ፈቃደኛ በመሆን በደብሩ ስም የተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደሴ ጦሳ ቅርንጫፍ ደብተር ቁጥር 36 ብለው መለገስ ይችላሉ፡፡
በአካል መርዳት ከፈለጉ የኮሜቴዎች ስልክ ቁጥር 0910139967 0913821001 0914715828 0920128536
በእነዚህ መንገዶች የተቻለዎትን ትብብር እንዲያደርጉ በቅ/ዮሐንስ ስም ፡፡


   የጋዴና ቅ/ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ

1 comment:

  1. do you have picture of the church please post it

    ReplyDelete