ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Wednesday, May 1, 2013

የይሁዳ አንበሳ

ከዘማሪ ‹ይልማ ሀይሉ› መዝሙር የተወሰደ

ህማሙን ልናገር አንደበት ቢያጥረኝም
መቼም ምንም ቋንቋ ለዚህ አይገኝም
ከረጅሙ ባጭር ከሰፊው በጠባብ
ስለከፈለልኝ ስለጌታ ላስብ
በጌቴ ሰማኔ ባታክልቱ ቦታ
ምድሪቷ ተሞልታ በታላቅ ፀጥታ
የአዳምን ልጅ ስቃይ በደሉን ሊሸከም
ጌታችን አዘነ ተጨነቀ በጣም
ሐዋርያት ደክመው ተኝተው ነበረ
ይሁዳ ከአይሁድ እንደተማከረ
ጭፍሮች እየመራ ጌታውን ሊያስገድል
የተሰራለትን ቸርነት ሳይቆጥር
ፋና እያበሩ ጭፍሮቹ ሲመጡ
ጌታን ሊያንገላቱት እንደዛ ሲቆጡ
የአምላኩን ጠላቶች መንገድ እየመራ
ይሁዳ ብቅ አለ ከቀያፋ ጋራ

+ + + + + + + + 
ላቡ ከግንባሩ እንደውሀ ሲወርድ
በታላቅ ይቅርታ ጌታችን ሲራመድ
ምስኪኖችን ሊያድን ድሆችን ሊታደግ
እየሱስ ቀረበ እንደሚታረድ በግ
ይሁዳ ጉንጮቹን ሳመው በክህደት
የተማከረውን የማያውቅ መስሎት
የአይሁድ ጭፍሮችም ያዙት ተናጠቁት
በታላቅ ጭካኔ በሰንሰለት መቱት

+ + + + + + + +
በጲላጦስ ችሎት አቁመው ከሰሱት
ንፁሁ እየሱስ ይሙት በቃ አሉት
እጆቹን ቸንክረው በጠንካራ ብረት
በዕፀ መስቀሉ ቀራንዮ ዋለ
ወልደ ጋንሚያው  ተጠማሁ እያለ
አሞትና ከርቤ ቀላቅለው  አጠጡት
አረ እንዴት ጨከኑ በምሬት ላይ ምሬትፍጥረታት ተጨንቀው በአይሁድ ክፋት

በየተፈጥሯቸው ዕርቃኑን ሸፈኑት
ጨረቃም ደም ሆነች ፀሐይም ጨለመች
አልፋና ኦሜጋ ተሰቅሎ ስላየች
ከዋክብት እረግፈው ምድር ተናወጠች
መባርቅትም ታዩ ተቆጣ ባህሩ
መለሳቸው እንጂ ስለግሩም ፍቅሩ
ከወንበዴ ጋራ ከመሀል አድርገው
ጌታን አንገላቱት ከመስቀል ላይ ሰቅለው
በቀኝ የነበረው ወንበዴው ለመነው
በመንግስትህ ጌታ አስበኝ እያለው

+ + + + + + + +
ከመስቀሉ በታች ዩሐንስን አየው
እስከ መስቀል ድረስ ስለተከተለው
ታላቋን ስጦታ እናቱንም ሰጠው
ተፈፀመ አለ ጌታ ነፍሱን ሰጠ
ሞትንም ከህዝቡ በፍፁም ቆረጠ
እንደተለመደው ዲያቢሎስ ቀረበ
ነፍሳትን ለመብላት እርሱ እንታራበ
ፍጡር መስሎት ነበር በመስቀል ላይ ያለው
በአራቱም ማዕዘን በንፋስ ወጠረው
በሲኦል ወረደ በኃይሉ ብርሃን
ማረከ ጌታችን የአዳምን ልጆችን
በሶስተኛውም ቀን ጌታችን ተነሳ
ሞትን ድል ያረገው የይሁዳ አንበሳ
በቃ ተወገደ የሰው ልጅ አበሳ
በሶስተኛውም ቀን ጌታችን ተነሳ
ሞትን ድል ያረገው የይሁዳ አንበሳ
በቃ ተወገደ የሰው ልጅ አበሳ
በቃ ተወገደ የሰው ልጅ አበሳ
በቃ ተወገደ የሰው ልጅ አበሳ
በቃ ተወገደ የሰው ልጅ አበሳ
+ + + + + + + + +1 comment:

  1. good bless you . It is very intersting

    ReplyDelete