ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Thursday, January 7, 2016

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ

  የአለም መድኀኒት ጌታ ዛሬ ተወለደ !! መድኀኒት ክርስቶስ ፤ የተዋረደውን ማንነታችንን ሊያከብር ፣ የተጎሳቆለውን ፀጋችንን ሊያድስ ፣ ከተጣልንበት በክብር ሊያነሳን ፣ የልጅነት ስማችንን ሊመልስ፣

"አባ...አባት ! ብለን የምንጠራበት መንፈስ ሊሰጠን ትንቢት አስነግሮ ... ቀን ቆጥሮ ቀን አስቆጥሮ ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ስጋ እና ነፍስ ነስቶ በድንቅ የተዋህዶ ሚስጢር ተወለደ ፡፡ ዕለቱም ዛሬ ነው !!

ሰብዓሰገል ስጦታን ያመጡልህ ፣ እረኞች ከመላዕክት ጋር ያመሰገኑህ ፣ እንስሳት ትንፋሻቸውን የገበሩልህ የቤተልሔሙ ጌታ ሆይ ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን ፡፡


እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል  በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ፡፡

No comments:

Post a Comment