ከቦታው በደረሰን መሰረት
ዝቋላ አቦ የተከሰተውን እሳት የማጥፋትና የማቆም
ሂደት በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠናከረ ነው፡፡ እርግጥም በመስቀል አደባባይ፣ በደብረዘይት እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ወደ ቦታው የሚሄዱ
ወጣቶች እየበዙ ነው፡፡ በዋነኛነት ግን እሳቱን ለማጥፋት ያለው የሰው ሀይል የበዛ ቢሆንም ሁኔታውን ለመቆጣጠር የከበደበት ሁኔታም
አለ፡፡ እርዳታ ለማድረግ በቦታው ያለው ከ 300 በላይ የሆኑት የሠራዊት አካላትም ሁኔታው ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡ በሰው ኃይል ያልተቻሉና ከገደሉ በታች ከባድ የሆነ እሳት አለ፡፡ ነገርግን በመንግስት እና በአንዳንድ የግል የሚዲያ አካላት እየተገለፀ ያለውና ችግሩ ወይም እሳቱ በቁጥጥር ሥር መሆኑን ነው፡፡ እውነታው ግን ይህ አይደለም፤ ከገደሉ ስር ያለው እሳት ለማጥፋት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ በአውሮፕላን አልያም በኢሊኮፕተር ካልሆነ በቀር ሊጠፋ አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ ስለሆነም የሚመለከተው አካል ወይም አቅሙ ያላችሁ እባካችሁን የሚደረገውን እንድታደርጉ በእግዚአብሄር ስም እንጠይቃለን፡፡
ወደ ቦታው የምትሄዱም በተቻለ አቅም ምግብ እንዲሁም የሚጠጡ ነገሮችን ወደ ቦታው ይዛችሁ ብትጓዙ መልካም ነው፡፡ ይህንን መልዕክት የምታነቡም ለወዳጆቻችሁ ትነግሩ ዘንድ በትዕትና እገልፃለሁ፡፡ ምክንያቱም ብዙ ወጣቶች ያለምግብ እየለፉና እየደከሙ ስለሆነ፡፡
በተረፈ የተቀረን ፀሎታችንን አናቋርጥ፡፡ መገረግ ያለበት ሁሉ እየሆነ ነው፡፡ ሁላችንም በተረጋጋ ስሜት ማሰብ ይኖርብናል፡፡ የመገናኛ ብዙሀንም ጥንቃቄያችሁ ቢገባኝም ታሪክ እየጠፋ ችላ አንበል፡፡
እግዚአብሄር ይርዳን!! አሜን
ሁላችሁንም እግዚአብሄር ይባርካችሁ
ሁላችሁንም እግዚአብሄር ይባርካችሁ
No comments:
Post a Comment