አንድ ወዳጄ በፌስ ቡኬ ላይ ይህንን መልዕክት ላከልኝና እኔም ለናንተ አልኩት፤እስቲ ያንብቡትና አንዳች ነገር ያግኙበት፡፡
አሁን ክርስትናችን የምትታይበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው፣ ከአመለካከት ጀምሮ በሀይማኖት ነቅተን መቆም እንዳለብን ተምረናል፡፡ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በልዩ ልዩ ፈተና ውሰጥ ነች፡፡ እባካችሁ ምዕመን ነቅተን እንቁም፤የቆምን የመሰለንም ደግሞ እንዳንወድቅ እንጠንቀቅ፡፡እራሳችንንም እንመርምር፡፡
ባለፈው ያከበርነው የደብረዘይት በዓል በእውነት ክርስቶስ የሚመጣበት ቀን ቢሆን ኖሮ ስንቶቻችን ነን ተዘጋጅተን ስንጠብቀው የነበርን? አሁን ቃሉ ትንቢቱ እየተፈፀመ ብቻ ሳይሆን እየተፈፀመብን ነው፡፡ ‹‹ ይህ ህዝብ በከንፈሩ ያመልከኛል›› ነው ያለው፡፡ ሁላችንም ዳር ቆመን ቲፎዞ የሚመሰጥ የስታዲየም ደጋፊ መሆን አይገባንም፡፡ አንድ ነገር ለሁላችንም ግልፅ ነው፤ ይኸውም ‹‹ስጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ›› ምን እንደሚያገኝ፡፡ አዎ ዛሬም የምንጠየቀው ይህ ነው!! እራሳችንን ምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንዳለን እንጠይቅ፡፡ ዲያብሎስ ውስጣችን እንዳናይ ዙሪያችንን በተለያዩ ስጋዊ ችግሮች ወጥሮ ይዞ ስለነፍሳችን እንድንዘናጋ እያደረገን ነው፡፡ ስለሆነም በፈተናው ሳንደናገጥ በአንድ ልብ ሆነን ‹‹ እግዚኦ መሐረነ ›› እንበለው፡፡
በአንዳንድ ደብሮች ላይ ‹‹እግዚኦ›› ለማለት እንኳን
የተከለከለበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው፡፡ ለምንድነው የማንለው !!?? ከዚህ በላይ ምን ይምጣብን?? በፊት በፊት ዝናብ እንኳን ትንሽ ሲጠፋ አምላክ አዝኖብናል ብለን ፊቱን ይመልስን ዘንድ፣ በምህረት ይጎበኘን ዘንድ ‹‹ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ. . . . በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ›› ስንል ወዲያው ይመለስልን ነበር፤ አሁን ግን ቤተክርስቲያን እየተቃጠለ፣ ቅዱሳን መካናት እየተደፈሩ፣ ምዕመን እየታሰሩ፤ እየተገደሉ፣ ቤተክርስቲያን እየተዘረፈች፣ መናፍቃን ከውስጥም ከውጭም ፈተና እያፀኑባት . . . . . .እስከመቼ ነው ‹‹ እግዚኦ›› ብለን በአንድ ልብ ሆነን የማንጮህ!!!??
እመኑኝ አሁንም በአንድ ልብ ሆነን ወደ አምላካችን፣ ወደ ድንግል ማርያም፣ . . . ወደ ቅዱሳን መላዕክት እና ወደ ፃድቃን ሠማዕታት ካልጮህን ፈተናው በጣም ይከብዳል፡፡ እዚህ ጋር የነብዩ ‹‹ጌዲዮን›› ሠራዊትን መመልከት ያስፈልጋል፡፡ እሩጫው መሆን ያለበት ከነዛ ከተመረጡት ሠራዊቶች መሀል መሆን ነው፡፡ እራሳችንን እናዘጋጅ፣ ንስሀ እንግባ፣ ቅዱስ ስጋና ደሙን ተቀብለን እንጠብቅ፡፡ ከዚህ በኋላ እግዚአብሄር በምህረት ያየናል፤ ይታረቀናል ብሎን የኢትዮጵያን ትንሳዔዋን ለማየት እንበቃለን፡፡ ያቆየን!!
‹‹ መንግስተ ሠማያት ቀርባለችና ንሰሀ ግቡ!!›› የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላዕክት ረድዔት እና በረከት የፃድቃን ሠማዕታት ፀሎትና ምልጃ አይለየን፡፡
No comments:
Post a Comment