ገጣሚ አቤል ምሕረቴ
ምን ያደርጋል ሀገር፣ ….
ምን ሊበጅ ዜግነት፣
ወልደው ካልሳሙበት፣….
ወልደው ካልሳሙበት፣….
ዘርተው ካልቃሙበት፣
ህጻናት በመስኩ፣…. አዛውንት በሸንጎ፣….
ህጻናት በመስኩ፣…. አዛውንት በሸንጎ፣….
ደምቀው ካልታዩበት፣
እምቦሳን በጓሮ፣…. ጥገትቱን ከጨፌው፣…
እምቦሳን በጓሮ፣…. ጥገትቱን ከጨፌው፣…
ታስረው ካልዋሉበት፣
ጋማ ከብቱ በመስክ፣… አውሬም በውርማ፣…
ጋማ ከብቱ በመስክ፣… አውሬም በውርማ፣…
ሞልተው ካልታዩበት፣
ፏፏቴው በዳገት፣… ጅረት በሸለቆ፣…
ፏፏቴው በዳገት፣… ጅረት በሸለቆ፣…
ሲፎክር ካልሰሙት፣
ተራራውም በደን፣… ክምሩ ባውድማ፣….
ተራራውም በደን፣… ክምሩ ባውድማ፣….
ገኖ ካልታየበት።
ከሰው ተወዳጅተው፣… ከሰው ተዋውለው፣….
ህይወት ካልመሩበት፣
ቅጠሉን በጥሰው፣… አፈሩንም ልሰው፣….
ቅጠሉን በጥሰው፣… አፈሩንም ልሰው፣….
ቆመው ካልሄዱበት፣
አርሰው፣ አሳርሰው፣…. ነግደው፣ አትርፈው…
አርሰው፣ አሳርሰው፣…. ነግደው፣ አትርፈው…
ሐብት ካልደረጀበት፣
ከእውቀትም ጨልፈው፣… በሳይንስ ተራቀው፣…
ከእውቀትም ጨልፈው፣… በሳይንስ ተራቀው፣…
ለድገት ካልሰሩበት፣
እናቶች፣ ህጻናት፣… መበለት፣ አዛውንት፣…
እናቶች፣ ህጻናት፣… መበለት፣ አዛውንት፣…
ካልተከበሩበት፣
ታመው ካልዳኑበት፣… አርጅተው አፍጅተው፣…
ታመው ካልዳኑበት፣… አርጅተው አፍጅተው፣…
ካልተቀበሩበት።
ወጥተው ካልገቡበት፣….
ሰርተው ካልኖሩበት፣
ከሸንጎው ዳኝነት፣…. ከወንበሩ ፍትህ፣….
ከሸንጎው ዳኝነት፣…. ከወንበሩ ፍትህ፣….
ነጥፈው ከጠፉበት፣
መብት ሚዛን አጥቶ፣…. ስርዓት ባገር ጠፍቶ፣…
መብት ሚዛን አጥቶ፣…. ስርዓት ባገር ጠፍቶ፣…
እብሪት ከገዛበት፣
ዜግነት ከሀገር፣…. ማንነት ከአንድነት፣….
ዜግነት ከሀገር፣…. ማንነት ከአንድነት፣….
ሰላም ከመቻቻል፣… ከተለያዩበት፣
ባሳብ ተደራጅተው፣… ደግፈው ተቃውመው፣…
ባሳብ ተደራጅተው፣… ደግፈው ተቃውመው፣…
ውለው ካልገቡበት፣
በልዩነት ደምቀው፣… በባህል፣ በእምነት፣…
ካልተከበሩበት።
ምን ያደርጋል ሀገር……?
No comments:
Post a Comment