ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Wednesday, January 11, 2017

ከመጥፋቴ ስመለስ

ሰላም ጤና ይስጥልኝ የተከበራችሁና የተወደዳችሁ ወዳጆቼ ፤

      እረጅም ጊዜ ሊባል በሚያስችል ሁኔታ ጥፍት ብዬ እረስታችሁኝ እንደነበር አሰብኩ፡፡ ይህም የሆነው  ከዚህ ቀደም እንደገለፅኩት በተለያዩ ምክንያቶች ሲሆን በስራ መደራረብ ፣ በትምህርት ፣ በፊልም ስራ ፣ ወዘተ. .. እንደቀድሞው ቶሎ ቶሎ መገናኘት አልቻልንም፡፡ በዋነኛነት ግን ለረጅም ጊዜ ለመጥፋቴ ምክንያት የሆኑኝን ጉዳዮች ዛሬ ልተንፍስ እና ቀሪውን ደግም ሌላ ጊዜ በሰፊው ማውራት እንችላለን፡፡

 ለዓመታት ሳልማቸው ከነበሩት ትልልቅ ህልም እና ዕቅዶቼ መካከል የ"ፊልም እና ፎቶግራፍ ፕሮዳሽን " ማቋቋም እና የጉዞ ማህበር መመስረት ነበሩ፡፡ በስተመጨረሻም ሁለትና ከዛ በላይ ዓመታት በላይ ፈጅተውብኝ፤  አሁን ግን ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል ሁኔታ ከግብ ለማድረስ ተችሏል፡፡

 የመጀመሪያው "እይታ ፊልም እና ፎቶግራፍ ፕሮዳክሽን " ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ " እይታ የመንፈሳዊ ጉዞ ማህበር " ናቸው፡፡  ሁለቱንም ለማቋቋምና ስራ ለመጀመር ሳስብ የራሴ አሻራ እንዲኖራቸው ከማሰብ ጀምሮ አብረውኝ እስከሚሰሩት ድረስ በተሻለ ጥንቃቄ  ስመርጥ የቆየሁ ሲሆን ቀላል የማይባል ድካም ነበረው ፡፡ ከዛም በላይ ከእናንተ ወዳጆቼ አራርቆኝ ነበር፡፡

          ወደቀደመው መነሻ ስመለስ በብዙ ፈተና ውስጥ ያለፍኩበትና ከአብዛኛዎቻችሁ ጋር ያስተዋወቀኝ  " የብስራት እይታ " (www.bisrat-views.blogspot.com) ድረገፅ እንደከዚህ ቀደም ሳይሆን መቀዛቀዝ ይታይበታል፡፡ ይኽም የሆነው ከላይ በገለፅኳቸው ምክንያት ሲሆን በተቻለኝ አቅምም ባለኝ ኃይል ወደቀደመው ተፅዕኖ ፈጣሪነቱና ተነባቢነቱ ለመመለስ እጥራለሁ፡፡ እዚህ ላይ የእናንተም ድጋፍና እርዳታ በጣሙን ያስፈልገኛል፡፡

በቀደሙት ጊዜያት በጣም የበዙ ፅሑፎች አዘጋጅቼ  ሳይወጡ የቀሩ ሲሆን ፤ አንዳንዶቹ በወቅቱ መነበብ የነበረባቸው ናቸው፡፡ ቀሪዎቹን ግን ቀስ እያልኩ አቀርብላችኋለሁ፡፡ አሁንስ እጅህ ከምን ለምትሉኝ እንደመታረቂያ የሚሆኑ በቅርብ ጊዜያቶች ውስጥ የተለያዩ ፅሑፎችን ለእናንተ ወዳጆቼ በእይታ መንፈስ ሃሳቤን በ"ብስራት እይታ " ድረገፅ ላይ  አካፍላችኋለሁ፡፡ አርዕስቶቹን ለመዘርዘር ያህል

* እኔና የሶስት ወሯ ሚስቴ (በተከታታይ  ለረጅም ጊዜ)

* የመንፈሳዊ ጉዞዎች መብዛት ጣጣ

* ደፋሮቹ አርቲስቶቻችን እና ቤተክርስቲያን

* ሐዊረ ሕይወት ጉዞ  እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሩጫ . . .መዝናኛ?


* አራዶቹ ቄሶች

* የጋዜጠኞቻችን ምላስ

* ተከታታይ ድራማዎቻችን

* ተሐዶሶ በተሐድሶ ሲታደስ

* ስዕሎቼን ጎብኙልኝ

* ሕንፃ ቤተክርስቲያኖችን ወዴት?

* አስራት በኩራታችንን . . .  ለማን?

* የቤተክርስቲያን ጉዳይ እንጂ ማዕበረ ቅዱሳን አይመለከተኝም

* አዲስ አበባን  ለሸገሮች

እንዲሁም ሌሎች
እናንተ በአድራሻዬ የላካችሁልኝን ሰብስቤ የተሻሉትን ፤ እናንተንም እኔንም የሚመጥኑትን መርጬ አቀርባለሁ፡፡  ሃሳባችሁን አካፍሉኝ፡፡
                                          * * * * * * * * * * * * *
      ሀሳቤን ከመቋጨቴ በፊት ቀድሞ ለምታውቁኝ  ፣  ለአዲስ ወዳጆቼ እንዲሁም በእኔ ደስስስ ለማይላችሁ  እራሴን በድጋሚ ላስተዋውቅ ፡፡

(ትንሽ ኮፈስ እንደማለት ብዬ) ሙሉ ስሜ ፡ ብስራት ገብሬ እባላለሁ፡፡ እዚሁ አዲስ አበባ ነው የተወለድኩት ፡፡ ጥቂት በማይባሉ ሙያዎች. . .በርታ ተብዬ ተሰይሜ ፣ ተስሜ ፣ ተመርቄ ፣ ተሸልሜ  በስራ ላይ እገኛለሁ፡፡

እንደ ቀድሞው ፓትሪያሪክ የእኔንም ስም ስትጠሩ ከፊት እነዚህን ማስቀደም እንዳትረሱ
ሰዓሊ ፣ ፎቶግራፈር (Photographer )፣ የፊልም ዳይሬክተር እንዲሁም ኤዲተር (Film Director & editor) ፣ የብርሃን የእናቶችና ህፃናት መርጃ ማዕከል መስራች እና የቀድሞ ስራ አስኪያጅ ፣ የሒሳብ ሰራተኛ ፣ አዲስ ድረ-ገፅ ለሚከፍቱ ድርጅቶች አማካሪ ፣ ፀሐፊ (blogger)  ፣ ጋዜጠኛ ፣ የንድፍ ሞዴል አውጪ (Graphics Designer ) ፣ የብስራት እይታ ድረገፅ ዋና አዘጋጅ... በቅርቡ ደግም በ M.A ደረጃ በ film production እንግሊዝ ሀገር ለንደን ከተማ  በሚገኘው NFTS (National film and television School) ተማሪ፡፡

ቀደም ባሉት ጊዜያት ደግሞ የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋይ ፣ መንፈሳዊ የትምህርት ተቋም ገብቼ ያቋረጥኩ ፣ የበጎ ስራ  አድራጎት አምባሳደር እንዲሁም የባንክ ሠራተኛ የነበርኩ አስቂኝ ልጅ ነኝ፡፡

ምንም ማድረግ አይቻልም ነው ያለው ዲጄው


ስለተተዋወቅን ደስስስስስ ብሎኛል፡፡

በነገራችን ላይ ከላይ ከተዘረዘሩት አርዕስቶች ውስጥ የትኛው ፅሑፍ ቀድሞ ይቅረብላችሁ ? በውስጣችሁ የያዛችሁት ጥያቄ ይኖር ይሆን አካፍሉኝ፡፡

እፎይይይይ
አመሠግናለሁ ፡፡

3 comments:

 1. አራዶቹ ቄሶች
  ተሐዶሶ በተሐድሶ ሲታደስ
  አስራት በኩራታችንን . . . ለማን?

  ReplyDelete
 2. * ተሐዶሶ በተሐድሶ ሲታደስ

  ReplyDelete
 3. አስራት በኩራታችንን . . . ለማን?
  የቤተክርስቲያን ጉዳይ እንጂ ማዕበረ ቅዱሳን አይመለከተኝም

  ReplyDelete