የአርሰናሉን አሠልጣኝ ከማንችስተር የ 8
ለ 2 ሽንፍት በኋላ ቃለ መጠይቅ እንዳደርግላቸው ስጠይቃቸው ፍቃደኛ መሆናቸውን ነግረውኝ ለዛሬ ቀጠሩኝ፡፡ ተገናኘን፡፡ ያው ኢትዮጵያዊ
ስለሆንኩ ቡና ልጋብዞት አልኳቸው፣ፈርተውኝ እንጂ ሊጠይቁኝ እንደነበርና ፍቃደኛ መሆናቸውን በፍርሀት ዓይን እያዪኝ ገለፁልኝ፡፡
አሣዘኑኝ፡፡ ባህላዊ ቤት በመሆኑ ያለነው አስተናጋጇ እንደባህሉና ስርዓቱ የተቆላውን ቡና በማንከሽከሻ ይዛልን መጣች፡፡ ማን እንዳስተማራቸው ባላውቅም ሶስት ጊዜ ወደ
አፍንጫቸው ሳብ ሳብ አደረጉና ጥሩ ነው. . . ጥሩ ነው. . . ብለው አመስግነው ሸኟት፡፡ ተመቹኝ…
ብስራት፡ “እንኳን አደረሶት አርሰን ቬንገር”
አርሰን ቬንገር ፡ “. . . ለምኑ?”
ብስራት፡ “. . .ለኢትዮጵያ አዲስ ዓመት”
አርሰን ቬንገር ፡ “. . ቂ.. . .ቂ. . .ቂ. . . እንኳን አብሮ አደረሠን”
ብስራት፡ “ ያው ኢትዮጵያ ውስጥ እንደአባት ስለሚታዩ ነው”
አርሰን ቬንገር ፡ “ ማን?. . . እኔ..?”
ብስራት፡ “ አዎ እርሶ! ብዙዎች ቬንገር. . .ቬንገር.
. .ይላሉ፡፡”
አርሰን ቬንገር ፡ “መቼም ቬንገር ቬንገር የሚሉት ይሰቀል ሊሉኝ አይመስለኝም፡፡”
ብስራት፡ “ እዚህስ ላይ እውነትዎን ነው፡፡” ፈገግ አልኩ “.
. . .እዚህ ሀገር ያሉ ደጋፊዎችና የስፖርት ገዜጠኞች እንደእናት ሀገራቸው ክለብ ወገባቸውን ያዘው እኮ ነው የሚከራከሩሎት ”
አርሰን ቬንገር ፡ “ደስ ይላል…! ኢትዮጵያውን በራሳችሁ ብቻ ስትኮሩ ነበር የማውቀው፡፡ ይልቅ ጅል አትሁኑ በላቸው፡፡”
ብስራት፡ “ እንዴት አገኙት የማንችስተርን 8 ለ 2 ሽንፈት? ”
አርሰን ቬንገር ፡ “ በጣም ጥሩ ነው፡፡”
ብስራት፡ “ማለት?”
አርሰን ቬንገር ፡ “ Well,አሁን የጀመርነውን ህፃናትን ማሳደግ ውጤታማ ለማድረግ እንደዚህ ዓይነት ቅስም ሰባሩ ሽንፈቶች
ማስተናገድ ወሳኝነት አለው፡፡”
ብስራት፡ “ አልገባኝም የማንችስተርን ጥንካሬ . . .” አላስጨረሡኝም
አርሰን ቬንገር ፡ “ ማንቼማ ማንቼ ነው! ደስ ይሉኛል፡፡”
ብስራት፡ “የፈርጉሰንን ዙፋን ይመኙታል?”
አርሰን ቬንገር ፡ “ መመኘት እመኘዋለሁ፡፡ግን ማንችስተር ለኔ ይከብደኛል፡፡ ይህንን ታላቅ ቡድን በህፃናት ፍቅሬ ማስወረር
አልፈልግም፡፡”
ብስራት፡ “አሁን በያዙት ወጣቶችና ህፃናት በሚሉት አካሄድዎ ደስተኛ አይደሉም ማለት
ነው?”
አርሰን ቬንገር ፡ “ምን ላድርግ ብለህ ነው? ‘shame’ ይዞኝ ነው፡፡ ሃሳቤን የቀየርኩ ከመሰልኩ ውርደቱ እራሱ…..
“
ተርገፈገፉ
ብስራት፡ “ ትህትናዎ ደስ ይላል::”
አርሰን ቬንገር ፡ “ ከፈርጉሠን የተማርኩት ነው:; ”
ብስራት፡ “ትንሽ ግትርነት አለቦት ይባላል”
አርሰን ቬንገር ፡ “ማነው ትንሽ ያደረገው . . . .ግትር ብቻ አይገልፀውም!”
ብስራት፡ “ ዘንድሮ ዋንጫውን እንበላዋለን ብለው ያስባሉ?”
አርሰን ቬንገር ፡ “እንዴታ!! እንኳን እኛ ማንችስተርም እየበላ አይደለም እንዴ!?? ”
ተቆጡ! አስተናጋጇን ጠሯት፤ ወተት አዘዙ፡፡
"ሠማሽ ቡና ለብቻው!! ደሞ ቅቤ ይኑረው!!!"
"ሠማሽ ቡና ለብቻው!! ደሞ ቅቤ ይኑረው!!!"
ቅቤ???? ሳቄ መጣ . . . ፊታቸው በርበሬ መሰለ፡፡
ብስራት፡ “ ቬንገር ፊቶት ተቀያረ ምን ሆኑ?”
አርሰን ቬንገር ፡ “እሠይ ደግ አረገ”
ለተወሰነ ሠዓት ዝምታ ሆነ
አርሰን ቬንገር ፡ “አንድ ነገር ልንገርህ በሚስጢር. . ,”
ብስራት፡ “ ደስ ይለኛል”
አርሰን ቬንገር ፡ “ ስምንት ሲያገቡብን ደስ ብሎኝ ነበር”
ብስራት፡ “ ለምን?”
አርሰን ቬንገር ፡” የኔ ልጀች መስለውኝ! ጨዋታቸው መስጦኝ. . .”
ብስራት፡ “ፈርጉሰን እኮ ለእርሶ መቆርቆር ጀምረዋል”
አርሰን ቬንገር ፡” ምን ያድርግ ታዲያ እየደከምኩ እየደከምኩ ስመጣ . . . የድሮ ጠላቴ፤ወይኔ ጀግናው. . .የሄነሪ
አባት! “
ብስራት፡ “ከ100 ዓመታት በላይ ያልተደፈረና ስምንት ጎል
ማስተናገድ በእርሶ ዘመን ይሆናል ብለው አስበው ያውቃሉ?”
አርሰን ቬንገር ፡ “አዎ . . . ! ብርቅ ነው እንዴ ስምንት ጎል ማስተናገድ? ገና አስራ ስምንት ይገባብን የለ እንዴ!?”
ብስራት፡ “ ለነገሩ ብርቅ አይደለም. . . አርሠን ቬንገር
. . .ከአሁን በኋላ ደጋፊውና የስራ አመራሩ በእኔ እምነት ይኖራቸዋል ብለው ያስባሉ?”
አርሰን ቬንገር ፡ “ እኔ ምን አገባኝ ስምንት ዓመት የረባ ዋንጫ አለመብላትና ስምንት ጎል ማስተነገድ ካስከፋቸው ምን
ማድረግ እችላለሁ ገደል መግባት ይችላሉ ለዛውም አሞራ ገደል!!”
አስተናጋጇ የታዘዘችውን ወተት በቡና ይዛ
መጣች፡፡ አመስግነዋት አጠገባቸው ያለውን ስኳር አነሱና ወተቱ ውስጥ
ከተው ማማሰል ጀመሩ፡፡ እንባ አይናቸውን ሞላው፡፡ ሠው አየኝ አላየኝ በሚል አካባቢውን ገልመጥ ገልመጥ አደረጉና ወተታቸውን መጠጣት
ጀመሩ፡፡ አሣዘኑኝ ግና እዚህ አዲስ አበባ ብዙዎች በእርሳቸው ምክንያት እያለቀሱ እንዳሉ ስለማውቅ ትንሽ ቢያለቅሱ ብዬ ተመኘሁ፡፡
ብስራት፡ “ከሽንፈቱ ምን ተማሩ?”
አርሰን ቬንገር ፡ “ ምኑን እንድንማር ፈቀዱልን ክፉኛ ቀጥቅጠውን፡፡ ያም ቢሆን ከአሁን በኋላ ዘጠኝ እንዳይገባብን እንድንጥር አሳስባለሁ፡፡”
ብስራት፡ “ማንን ነው የሚያሳስቡት?”
አርሰን ቬንገር ፡ “በረኛችንን!”
ብስራት፡ “በመጨረሻ የሚሉት ነገር ካለ?”
አርሰን ቬንገር ፡ “መልካም! እቅዴ. . . ከዚህ ታላቅና ታሪካዊ ውርደት በኋላ አገግመን እንዴት ዋንጫ እንደምንበላ
የህፃናቱን ወላጆች ማማከር ነው፡፡ወደፊትም ብዙ አቁስል ህፃናት እንዲኖሩኝ እፈልጋለሁ፡፡”
ብስራት፡ “ጥያቄዬን ጨርሻለሁ፡፡ ለነበረን ቆይታ አመሰግናለሁ፡፡”
አርሰን ቬንገር ፡ “እኔም አመሰግናለሁ‹፤ ቡናችሁን ወድጄዋለሁ፡፡እንግዲህ . . . . ያው አስር ገብቶብን ለመገናኘት
ያብቃን፡፡”
ብስራት፡ “አሜን!!!ያሰቡት ይሳካሎት!! ሽንፈትን በሽንፈት ይደራርብሎት፡፡የቡናውንም ነገር የኢትዮጵያ መንግስት እንዲውቀው
አደርጋለሁ፡፡ምክንያቱም እርሶ ጥሩ ነጋዴና አስመጪና ላኪ ስለሆኑ እንዴት አብራችሁ እንደምትሰሩ . . . " አላጨረሱኝም……
አርሰን ቬንገር ፡ “ተው እንጂ በቃአ . . . አሠልጣኝነቴን ልተወው . . . . “
ይሻሎታል አልኩኝ በውስጤ
ደህና ሁኑ፡፡፡፡፡፡፡፡
እኔ የግል ብሎግ ማንበብ እወዳለሁ፡፡ ያንተንም ሳገኝ ደስ ብሎኝ ነበር ነገር ግን የገጹ ጥቁረት፤ የፊደላቱ ድምቀት ተፈታተነኝ፤ ፎርማቱም ትንሽ ተዝረከረከብኝ (ሶሪ) እና ብዙ ሳላነብ ወጣሁ፡፡ እባክህ ትንሽ የተጨናነቀውን ገጽ ቀለል፤ ፈታ አድርገውና የምትለውን ላንብብ፡፡
ReplyDeleteYamirhal, Keldegna neh.
ReplyDeleteawareden hihe sewiye....anyway I like your interview and really funny.keep it up
ReplyDeletebalege neh...ምናብህ ትንሽ ነው
ReplyDeleteስለ ፍሪኪው ሳደንቅክ ከዚጋ ደግሞ ይበልጥ አጋነንከው::
ReplyDeleteበጣም ደስ ይላል ያዝናናል!
ReplyDeleteጥሩ የማንቸ ደጋፊ እንደሆንኪ ተርድቻለሁ
ReplyDelete