የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: የዓለም የጦማሪዎች ቀን:
ነሐሴ 25 ቀን 2003 ዓም [August 31, 2011]
የኢትዮጵያውያን ጦማሪዎች ጉባኤ
የዓለም የጦማሪዎች ቀን በዚህ ዓመት ነሐሴ 25 ቀን 2003 ዓም [August 31, 2011] ይከበራል፡፡ በተለያዩ ድረ ገጾች እና የማኅበራዊ ሚዲያዎችላይ እንደምናየው የየሀገሩ፣ የየከተማው እና የየክፍለ አህጉሩ ጦማሪዎችየተለያዩ ዝግጅቶችን በአንድ አካባቢ በማዘጋጀት ዕለቱን ለማክበርተዘጋጅተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እና በኢትዮጵያውያን አካባቢየሰማሁት ነገር የለኝም፡፡
በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያውያን ጦማሪዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ ኑሮ፣ በእምነት፣ በኪነ ጥበብ ወዘተ ላይየሚያተኩሩ ጦማሪዎች ብቅ ብቅ እያሉ ነው፡፡
ሰዎች ሃሳባቸውን መግለጣቸው፣ መረጃ መለዋወጣቸው እናመገናኘታቸው መቼም ቢሆን በሥዕለት የሚገኝ ዕድል ነው፡፡ «አህያቢራገጥ ጥርስ አይሳበርም» የሚለውን ብሂል «ሃሳብ ቢቧቀስ ጥርስአይሳበርም» ወደሚለው ለመቀየር የሚቻለው የሃሳብ መግለጫ መንገዶችሲበዙም ሲጠነክሩም ነው፡፡ ከእነዚህ መንገዶች ላይ ዘመኑ ብሎግንጨመረልን፡፡
በሀገር ውስጥ ያለው የኢንተርኔት ተደራሽነት ማነስ እና የጥራት ችግርእንዳለ ሆኖ ብቅ ብቅ ያሉትን ጦማሪዎችም ሆነ ሊመጡ ያሰቡትንጦማሪዎች የሚያሳስቡ ወይንም ሊያሳስቡ የሚገቡ ነገሮች ግን አሉ፡፡
የመጀመርያው የማስተዋወቂያ መድረክ እጦት ነው፡፡ ብሎጎቹመጀመራቸውን፣ መኖራቸውን እና የሚያ ወጧቸውን ጉዳዮችየሚያስተዋውቁ መድረኮች እምብዛም አይገኙም፡፡ እኔ ለምሳሌአንዳንዶቹን ብሎጎች ማወቅ የቻልኩት ከተጀመሩ ከዓመታት በኋላነው፡፡ እነዚህን የሃሳብ መንሸራሸርያ መንገዶች በአንድ ቦታየምናገኝበት፣ ሲጀመሩም ዜናቸውን የምንሰማበት መንገድ ቢኖር እኛምከመረጃው እና ከሃሳቡ እንጠግብ፣ አዘጋጆቹም «የደገሰውን ሲበሉለት፣የወለደውን ሲስሙለት» በሚለው መሠረት ይደሰቱ ነበር፡፡
ሁለተኛው ደግሞ የልምድ መለዋወጫ መንገድ አለመኖሩ ነው፡፡አዳዲሶቹ ጡመራዎች የቀድሞዎቹን ስሕተት የሚደግሙት፣ በተሻለአሠራር እና ገጽታ የማይመጡት፣ አዲስ ነገርም የማያሳዩት ምናልባትለምድ የሚቀስሙበት መንገድ ከማጣት ይመስለኛል፡፡
ሦስተኛው የጋራ የሆነ አካል አለመኖሩ ነው፡፡ ማንኛውም ክዋኔ ደረጃ፣የሥነ ምግባር ደንብ፣ የመረጃ ማዕከል፣ ወዘተ ያስፈልገዋል፡፡ የዚህዓይነቱ አካል መኖር የጡመራዎቹ የሞያ ደረጃ እንዲሻሻል፣ የልምድመለዋወጫ መንገዶች እንዲኖሩ፣ ቅሬታዎች በመግባባት እንዲታረሙ፣ጦማሪዎች እና ጡመራች የሚመ ሩባቸው የሥነ ምግባር ደንቦች በጋራእንዲወጡ፣ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
ዛሬ ያለው የዓለም ሥርዓት አንድን ሥራ ለመሥራት የግድ በአንድቦታ መገናኘትን የማይጠይቅ እየሆነ ነው፡፡ የመረጃ መረብ ቴክኖሎጂንየሚጠቀሙት ጦማሪዎች ከላይ የተነሡትን ነገሮች ለመተግበር የግድመገናኘት አያስፈልጋቸውም፡፡ ያንኑ መረብ ተጠቅመው ነገሮችንመሥራት ይችላሉ፡፡
እናም «የኢትዮጵያውያን ጦማሪዎች ጉባኤ» (Society of Ethiopian bloggers) ቢኖረን ምን ይመስላችኋል? እስኪ ሃሳብ ስጡበት፡፡
No comments:
Post a Comment