ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Sunday, September 20, 2015

እነሆ ባቡሩ...


     ዛሬ ነው መስከረም 8 , 2008 ዓ.ም
   
    ንጋት ላይ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን (ፒያሳ) አካባቢ  ነበርኩ፡፡ በእሳት አደጋ መ/ቤት አካባቢ ባለው የቤተክርስቲያኑ በር የተወሰ ግርግር ነበርና ምናልባት ሰንበት ስለሆነ የሚያስቀድሱ ሰዎች ይሆኑ ብዬ አሰብኩ፡፡ ግን ፖሊሶች (ፌደራሎች) በዛ ብለው ሳይ ምን ተፈጥሮ ነው ብዬ አንዲት ነጠላ የለበሱ እናትን ጠየኳቸው ' ባቡሩ. . . መሠለኝ" አሉኝ

  " ባቡር ስራ ይጀምራል" የሚለው ትዝ አለኝና ወደ ጉዳዬ አዘገምኩ፡፡

     ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ ጉዳዬን ፈፅሜ ስመለስ በግምት ከሁለት መቶ እስከ ሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሰልፍ ይዘዋል፡፡ ተጠማዞ ተጠማዞ እረጅም ሰልፍ ሆኗል፡፡ የባቡሩን ነገር እረስቼው ስለነበር ምን ተፈጠረ ብዬ ሁኔታውን ለማጣራት ቆምኩኝ፡፡ ባቡር ሊሳፈሩ እንደሆነ
አንዱ ሠልፈኛ ነገረኝ፡፡ ይሄ ሁሉ ህዝብ በአንድ ግዜ ለባቡሩ እንዴት
ሊሆን ይችላል አልኩ ለራሴ፡፡ ዝንጥ ያሉ ወጣቶች ፣ እናቶች አባቶች ጎረምሶች ፣ ቀበሌ ፊት ፣ ክፍለ ከተማ ፊት ተብሎ በልምድ የሚነገሩ ፊት ያላቸው ሰዎች . . . ብቻ ብዙ ዓይነት ሰዎች ተሠልፈዋል፡፡ ሠልፉን ከፊት የሚመሩት ትኬት መቁረጫ ይመስለኛል አንድ ትልቅ ኮንቴነርን ከበዉታል፡፡

 ገርሞኝ ትንሽ እንዳለፍኩ ካሜራዎች ተደርድረው ቀረፃ ላይ ናቸው ፡፡ 'ኢንተርቪው' የሚደረጉ ሰዎች ካሜራው አካባቢ ቆመዋል፡፡ ኢቲቪ ጀግናው ስራውን በአግባቡ እየሠራ ነው አልኩ ለራሴ ፡፡

የባቡር ስራው መጀመሩ መልካም ቢሆንም ሰውን የሚያክል ነገር
አሰልፎ የፖለቲካ ማስፈፀሚያ ማድረግ ግን ተገቢ ነው ብዬ አላምንም ፡፡ የሠልፉ ግርግር የውሸትም ይሁን የእውነት ለአዲስ አበባ ህዝብ አይጠቅመውም ፡፡ ምክንያቱም ከጅማሬው ይህን ያህል ህዝብ ከተሠለፈ በቀጣይ ደግሞ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰብ ቀላል ነው ፡፡ ታክሲዬ የኔ ፍቅር ብሎ ከታክሲው ጋር ወዳጅነቱን መቀጠል ነው የሚጀምረው ፡፡ የትራንስፖርት ችግርን ይቀርፍልካል ተብሎ ሲሰበክ ለኖረ ህዝብ ገና ከመጀመሪያው ይህን የመሰለ ረጅም ሰልፍ ከተመለከተ ባቡሩ ላይ የተመኘውን ተስፋ በመጀመሪያው ቀን ይጥለዋል፡፡ ባቡሩ ስራ ጀመረ ተብሎ ብሎ ማክበር ባይከፋም የህዝብ ጋጋታ ማሠለፍ ግን ላሰራው አካል ትልቅ ፖለቲካዊ ኪሳራ ነው፡፡

       አዲስ አበባ ህዝብ ካለበት ችግሮች አንዱና ዋነኛው የትራንስፖርት እጦት ነው፡፡ " ይኸው ተመልከት. . . ሠልፉን . . . የባቡርን ስራ መ'ጀመር በጉጉት ሲጠብቅ የነበረ ህዝብ በደስታ ወጥቶ ተሠለፈ ፤ ከታክሲ ችግር አይበልጥብንም ብሎ ገና በጠዋቱ ተሠለፈ " ብለን ብንደሰኩር ማንም አይሠማም፡፡ የአዲስ አበባ ህዝብ ችግርን ከመላመዱ የተነሳ የማንንም እርዳታ ሳይሻ በራሱ የህይወት አመራርና መንገድ መኖር ከጀመረ ቆይቷል፡፡
መንገድ ትራንስፖርት የሚባለው መስሪያ ቤትም አይደለም የህዝቡን ችግር ሊፈታ. . . የሚያወጣውን ህግና ስርዓት ከህዝብ ጋር ተባብሮ መቆጣጠር ያልቻለ ሚኒስተር መ/ቤት ነው፡፡

ይህን ሁሉ ችግር ችሎና ታግሶ ፣ ተጣልቶና ተስማምቶ የሚኖርን ህዝብ ይኸው ባቡርክ ስንለው በምን መልክ መሆን እንዳለበት ማሠብ ነበረብን ፡፡ አሁንም አለብን፡፡ ልንዋሸው ልናታልለው አይገባም ፡፡

ለዛሬው በዚሁ አበቃሁ፡፡


ኢትዮጽያ ለዘለዓለም ትኑር!

2 comments:

 1. Conflict at Toronto Ethiopian orthodox Cathedral
  በቶሮንቶ ቅድሥት ማርያም ቤተከርስቲያን የተነሳው የሃይማኖት ውዝገብ ና መንስኤው

  የውዝገቡ መንስኤው የሆነው የቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ ትምሀርት የተሰጠው በሰሜን አሜሪካ ሰንበት ት/ቤቶች 13ኛ ዓመታዊ አንድነት ጉባኤ ላይ ሲሆን የትምህርቱ ርእስ “ሁልጊዜም ዝማሬዬ ለአንተ ነው” የሚል ሲሆን በዚህም ትምህርታቸው ላይ “ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏልና”በሚል ንኡስ ርእስ "ዝማሬ ለአምላክ ብቻ ሊቀርብ እንደሚገባ በመናግራቸው ክቶሮንቶ በቦታው ከተገኙት ምአመናን በቦታው ከፍተ ተቃወሞ አስምተዋል

  የቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ ትምሀርት እንዳበቃ በጉባኤው በተደረገው ውይይትም ላይ "“ድጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምሕረትን ተጽናናሁኝ ረሳሁ ሐዘኔን” ብሎ መናገር በራሱ ምመጽሐፍ ቅዱስ የማይደገፍ ነው ተብሎ በድፍረት በጉባኤው በስፋት ተነግሮአል የዚህን ጉባኤ ዝርዝር በበለጠ ለመረዳት ክዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይመልከቱ

  http://www.abaselama.org/2015/09/13.html#more

  እነዚሁ የእመ ቤታችን እና የቅዱሳን ፍቅር የአንገበገባቸው የቶሮንቶ ምአመናን በአንድነት ጉባኤው ላይ በቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ የተስጠውን የስህተት ትምህርት እርምት እንዲደርግበት በመጠየቃቸውና ትምሀርቱ ምንም ስህተት የለውም ተብሎ ከካቲድራሉ አስተዳዳሪ ጉዳዩን ለማስተባበል በመሞከሩ ክፍተ አልመግባባት አስነስቶአል ::አስትዳዳሪው l ሊቀ ካህናት ምሳለ እንግዳ ለብዙ ዘመናት የደክሙበት ቤተከርስቲያን የመናፍቃንና የተሃድሶ መ ታጎሪያ እንዲሆን ይፈልጋሉ ብሎ ማመን ቢክብድም " ኪዳነ ምሕረትን ድጅ ጠናሁ" ማለት ስህተት ነው የተባልበትን ትምሀርት ክግርማ ሞገሳቸው ከእመ ቤታችን መንበር ፊት ቆመው ትምሀርቱ ስህተት የለውም ማለታቸው ለምን ይሆን?

  ReplyDelete
 2. Please mr Bisrat can you tell me about Abune Gebre Menfes Kidus Teamer.
  Thank you

  ReplyDelete