ፀሐፊ፡- ዮሴፍ ይልማ
yilmajoseph_1978@yahoo.com
የጨርቋን ጫፍ ጥለት፣
በአቧራ ነትቦ ባንዲራ ያለበት፡፡
ጭምድ ድ አርጎ ይዞ ህፃኑ ጠየቀ
ግራ ቀኝ እያየ እየተሳቀቀ
“አገራችሁ ሂዱ” ሰዎቹ የሚሉን
የት ነው አገራችን?
ጥለትሽ ላይ ያለው ያገርሽ መለያ
የት ናት ኢትዮጵያ?
የት ጋር ተጀምራ የት ጋር ነው ‘ምታልቀው?
አፈርና ወንዙ ባህል ሐይማኖቱ የት ጋር ነው ‘ሚለየው?
እዚህ አይደለችም? ወደምንሄድበት እዚያ ናት ኢትዮጵያ?
ወጥተን ነበር እንዴ ከናታቻን ጉያ?
ውስጥ ሆነን ውጭ ነበርን?
እንደዚ ጨክነው አጣድፈዉ ‘ሚገፉን
ወዴት ነው ምንሄደው?
ወዴት ናት አገሬ?
ወጥተን ነበር እንዴ ከአገር ከድንበሬ?
ኧረ ቆይ እማማ
እስቲ ልጠይቅሽ ጉዳችንን ልስማ
ታላቅ ወንድማችን እውጪ አገር ‘ሚኖረው
እሱም ይባረራል? ጦቢያን ይፈልጋል?
ንገሪኝ እማማ?
ይሄን ነገር ልስማ?!
ጭምድ ድ አርጎ ይዞ ህፃኑ ጠየቀ
ግራ ቀኝ እያየ እየተሳቀቀ
“አገራችሁ ሂዱ” ሰዎቹ የሚሉን
የት ነው አገራችን?
ጥለትሽ ላይ ያለው ያገርሽ መለያ
የት ናት ኢትዮጵያ?
የት ጋር ተጀምራ የት ጋር ነው ‘ምታልቀው?
አፈርና ወንዙ ባህል ሐይማኖቱ የት ጋር ነው ‘ሚለየው?
እዚህ አይደለችም? ወደምንሄድበት እዚያ ናት ኢትዮጵያ?
ወጥተን ነበር እንዴ ከናታቻን ጉያ?
ውስጥ ሆነን ውጭ ነበርን?
እንደዚ ጨክነው አጣድፈዉ ‘ሚገፉን
ወዴት ነው ምንሄደው?
ወዴት ናት አገሬ?
ወጥተን ነበር እንዴ ከአገር ከድንበሬ?
ኧረ ቆይ እማማ
እስቲ ልጠይቅሽ ጉዳችንን ልስማ
ታላቅ ወንድማችን እውጪ አገር ‘ሚኖረው
እሱም ይባረራል? ጦቢያን ይፈልጋል?
ንገሪኝ እማማ?
ይሄን ነገር ልስማ?!
ዬሴፍ ዘካናዳ 06/04/2013
ወደ” አገራችሁ” ሂዱ ለተባሉት ህፃናት መታሰቢያ ትሁን
Bisrat Gebre enameseginalen
ReplyDeleteyihew amarawim eyetebarere new. fetari yiredan
ReplyDeleteGod bless Ethiopia.
ReplyDelete