ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Friday, December 27, 2013

ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኡል ፡ ታህሳስ 19

       

  
           ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል ጌታና አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ብርሃናዊ መልዓክ ቅዱስ ገብርኤል ፤ ቅዱሳን ሰማዕታት ገድላቸውን እንዲፈፅሙ እሳቱን እና ስለቱን ፈርተው ወደኋላ እንዳይመለሱ ይረዳቸዋል፡፡
ከሰባቱ ሊቃነመላዕክት በተራዳዒነቱና በአማላጅነቱ ያዘኑትን ለማፅናናት ፤ ምስራች ለመናገር ከእግዚአብሄር የሚላከው አንዱና ዋነኛው በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው መልዓክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ 
ታህሳስ 19 ብርሃናዊው መልዓክ ቅዱስ ገብርኤል ሰለስቱ ደቂቅን ከዕቶን እሳት ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ በዓል በመባል በፀሎትና በምስጋና በደማቅ ሁኔታ ታከብራለች፡፡

           የታሪኩ መነሻ . . .


     ባቢሎንን ይመራ የነበረው ናቡክደነፆር በእግዚአብሔር የማያምን ጣዖትን የሚያመልክ ንጉስ ነበር፡፡ በወቅቱም ቁመቱ ስልሳ ወርዱ ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቅ ምስል በማሰራት ሕዝቡ እንዲሰበብ በማዘዝ ሁሉም ሰው ላሰራው ጣዖት መስገድ እንዳለባቸው ይህን በማይፈፅሙት ላይ ቅጣቱ ከባድ እንደሆነ አዋጅ አሳወጀ፡፡



የንጉሱ አስተሳሰብ ለእግዚአብሔር ወዳጆች ከባድ ፈተና ቢሆንም እውነተኛዎቹን አማኞች ግን በእግዚአብሔር ላይ ያላቸው እምነት ሊቀይረው አልቻለም፡፡  ቅጣቱንም በማሰብ እና በመፍራት ሁሉም እግዚአብሔርን በመካድ ለጣዖቱ ሰገዱ አረበረቡ፡፡ 
በዚህ ፈታኝ ዘመን ነበር አናንያ ፣ አዛርያን እና ሚሳኤል የተባሉ ሶስት ወጣቶች ግን ለእግዚአብሔር ያላቸውን መታመን አሳዩ፡፡ ለጣዖቱ ያልሰገደ ወደ እቶን እሳት ተጥሎ እንደሚሞት ቁርጥ ያለ ወሳኔ እንደሆነ ቢያውቁም ያለምንም ፍርሃት በአንሰግድም አቋማቸው በመፅናት "ንጉስ ሆይ የፈጠረንን አምላካችንን ክደን አንተ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም !" አሉት፡፡ 

በሶስቱ ወጣቶች ድርጊትና ድፍረት በጣም የተቆጣው ንጉስ ናቡክደነፆር አገልጋዮቹን ጠርቶ እሳቱ ሰባት እጥፍ እንዲነድ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ወደ እሳቱም እንዲከቷቸው አዘዘ፡፡ የንጉሱ አገልጋዮች ሶስቱን ወጣቶች አናንያን ፣ አዛርያን ፣ ሚሳኤልን እያንከበከቡ ወደ እቶን እሳቱ ወረወሯቸው፡፡ 

እሳቱ ከነበረው ኃይል የተነሳ ወላፈኑ አገልጋዮቹን እዛው እንደ ማገዶ አነደዳቸው፡፡ ሠለስቱ ደቂቅ ግን ከየት እንደመጣ ካልታወቀ እንግዳ ጋር በመሆን በዕቶን እሳቱ ውስጥ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በደስታ ይመላለሱ ጀመር፡፡ ይህም ተዓምር ንጉሱን እና መኳንንቶቹን እንዴት ሊሆን ቻለ ብለው ተገረሙ፡፡ ንጉሱም በዚህ ወቅት በመደነቅ
" እነሆ እኔ በእሳቱ መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች ይታዩኛል፡፡ እሳቱ ምንም አልጎዳቸውም ፡፡ አራተኛው ግን የአማልክትን(የእግዚአብሔርን) ልጅ ይመስላል፡፡ " አለ፡፡
ንጉስ ናቡክደነጾር በግልፅ ተመልክቶ  እንደመሰከረው የነደደውን እሳት በማብረድ ለሠለስቱ ደቂቅ ቤዛ የሆናቸው ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ስለ ሃይማኖታቸው መከራ የተቀበሉን የአግዚአብሔር ወዳጆችን በእምነት የሚያፀና ታላቅ መላዕክት ነው፡፡ ከነደደ እሳት ባልተናነሰ መከራና ችግር ውስጥ ገብተው በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ከሞት ስጋ ነፍስ ድነው በመልዓኩ ስም በፈለቀ ጸበል ተጠምቀው ደዌ በሽታ ጭንቀትና ሀዘን የራቀላቸው እጅግ ብዙዎች ናቸው፡፡ 

ይቆየን!!!


የመልዓኩ ቅዱስ ገብርኤል ጸጋ እና ምልጃ እንዲሁም ጥበቃ አይለየን፡፡

  
     

2 comments:

  1. Ebakachuh man endehone yetelakew meleak aberarulegn?

    1- Meleaku Kidus Gebriel
    2- Meleaku Kidus Mikael
    3- Meleaku Kidus Raguel?

    EBS TV ehud tahsas 19/ 2006 bediakon Birhanu yetesetew mabrariya gilets silalhone ebakachuh sefa yale mabrariya tisetugnalachuh.

    Egziabher yistelegn.

    ReplyDelete
  2. This might help you

    http://www.eotc.tv/?q=node/112

    ReplyDelete