ሠላም ጤና ይስጥልኝ ክቡራን አንባቢያን ፤ ከዚህ መካነ-ድር (ድረ ገፅ) ላይ የምትወስዱትን ማንኛውንም ፅሑፍም ይሁን ምስሎች ለአዘጋጆቹ እና ለፀሐፊዎቹ ክብር ሲባል በምትጠቀሙበት ቦታ ሁሉ ምንጩን ትጠቅሱልን ዘንድ በትህትና እናሳስባለን ፡፡

Friday, January 5, 2018

ኢብራሂም ሻፊ ፦ ነፍስህን በገነት ያኑራት!

ኢብሮ የአንተን ማረፍ ስሰማ እንዴት እንዳዘንኩ እንዴት ላሳይህ?  ለአንተ ያለኝ ክብር ደግሜ ደጋግሜ ብነግርህም አሁን ሳጣህ ደግሞ የምሆነው ጠፋኝ!
በመምህርነትህ ፣ በመጽሔት አምደኛነትህ ፣ በስፖርት ጋዜጤኝነትህ በሬዲዮ በጋዜጦች ፣ በማህበራዊ ገፆች ላይ የምታቀርባቸውን ጥልቅ እይታ ያላቸው ስፖርታዊ ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ ፅሑፎችህ አስተያየቶችህ ንግግሮችህ ስንቱን እንዳስተማርክ ስንቱን እንደለወጠ በምን ቃል ልግለፀው? ለምታምንበት ነገር ሟች እንደሆንክ ከሁሉ በላይ ለእናት ሀገርህ ያለህን ፍቅር ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ ብዙዎች አቋማቸው እየለዋወጡ ለሆዳቸው በሚኖሩባት ሀገራችን እንዳንተ ያለ በአቋሙ ፀንቶ እራሱንም ለአደጋ አጋልጦ የሚኖር ማግኘት ይከብዳል፡፡ መሰደድህን የሰማሁ ቀን አልቅሻለሁ፡፡ ሀገሬ እንደ አንተ ያሉ ወርቃማ ልጆቿን እስከመቼ እያጣች እንደምትኖር አላውቅም፡፡ አንተ የሆንከውን ስመለከት መጨረሻችን ሁሌም ያሳስበኝ ነበር፡፡
. . . .
እኔና ኢብራሂም ይበልጥ የተግባባነው ከሀገር ከተሰደደ በኃላ ነው፡፡ በሚገርም ሁኔታ ከሀገራዊ ስራዎቼ በተጨማሪ በሃይማኖታዊ ስራዎቼ ላይ እንኳን ሳይቀር አስተያየት ይሰጠኝ ነበር፡፡ ለስራዎቼ  ያለውን አድናቆት እና ክብር ብዙ ጊዜ ይነግረኝ ነበር፡፡ ብዙዎች ዕውቀት ሳያንሳቸው በስሜታዊነት እና በጨለምተኝነት በሚኖሩበት በዚህ ጊዜ(ዘመን) ማንም የእሱን ያህል ንፁህ አስተያየት የሰጠኝ ፤ ሃይማኖትህ ሃይማኖቴ ፣ እምነትህ እምነቴ ነው ! አንድ ነን !! ያለኝ የለም፡፡ በዓላት ሲመጡ የእንኳን አደረሰህ መልዕክቶቹ ፤ ሰው አክባሪነቱ ፣ ለሀገሩ ለወገኖቹ ያለውን ተሟጋችነት መቼም አልዘነጋም! ለኔ ዋጋቸው ትልቅ ነበር፡፡ ኢብሮ የዚህ የእብሪተኛው እና የአምባገነናዊ ስርዓት ተጠቂ በመሆንህ ደግሞ ይበልጥ ልቤ ይደማል! እንደ ሰው በሁለት እግርህ በመቆሚያህ ጊዜ በወጣትነትህ. . .
ምን ልበል ወዳጄ የምለው ጠፋኝ እኮ!
ፈጣሪ ነፍስህን ይማር
ሁሌም በልቤ ትኖራለህ!
. . . . .
ለቤተሰቦቹ ለጓደኞቹ ለወዳጆቹ ለጨርቆስ ሰፈር ልጆች ፈጣሪ መፅናናትን ይሰጣችሁ ዘንድ እመኛለሁ፡፡

No comments:

Post a Comment